• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የሳውዲ የተራዘመ የምህረት አዋጅ እንዴት እንጠቀምበት?

June 29, 2017 11:34 pm by Editor Leave a Comment

* የተራዘመው የምህረት አዋጅ
* የ90 ቀኑ ምህረት አዋጅ አስተምሮቱ ..
* አጭሩን ጊዜ በአግባቡ ለመጠቀም ..
* የበረራ ፈቃድ እና የአሻራ አሰጣጡ ተጠያቂ ማነው?
* በቂ ድጋፍ ለማድረግ የሰው ሃይልን ስለማደራጀት ..

* ስራው በማን ነው የሚሰራው? የዲፕሎማቶች?

መኖሪያና የስራ ፈቃድ የሌላቸው ሳውዲን በ90 ቀን ውስጥ ለቀው እንዲወጡ የተሰጠው ቀነ ገደብ ለ30 ቀናት ተራዝሟል ። በሳውዲው ንጉሳዊ ቤተሰቦች አመራሮች ይሁንታ አግኝቶ በሀገር ውስጥ ሚኒስትሩ ትዕዛዝ ማምሻውን በፖስፖርት የበላይ ዳይሬክተር በሜጀር ጀኔራል ሱሌማን የህያ ይፋ የሆነው መረጃ ይፋ ይፋ ሆኗል። ይፋ የሆነው የምህረት አዋጅ የ90 ቀኑ የምህረት አዋጅ ካለቀበት እአአ ከሰኔ 25 ጀምሮ እስከ ቀጣዩ ሐምሌ 25 ቀን 2017 ድረስ የሚቆይ እንደሆነው ታውቋል። ፖስፖርት የበላይ ዳይሬክተር ሜጀር ጀኔራል ሱሌማን የህያ በተሰጠው ተጨማሪ አንድ ወር ህጋዊ መኖሪያና የስራ ፈቃድ የሌላቸው አስፈላጊውን መስፈ ርት አሟልተው ሳውዲን ለቀው እንዲወጡ አሳስበዋል።

የ90 ቀኑ ምህረት አዋጅ አስተምሮቱ …

በ90 ቀኑ የምህረት አዋጅ መኖሪያና የስራ ፈቃድ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ለመግባት ፍላጎት አለማሳያታቸው ይጠቀሳል። እውነታውን ለማስረዳት ዛሬ ላይ ቀላሉ ማሳያ 400 ሽህ ህገ ወጥ ኢትዮጵያውያን ባሉባት ሳውዲ ወደ ሀገር ለመግባት ሰነድ  በመውሰድ የተመዘገቡትና ሀገር የገቡትን ቁጥር ማየት በቂ ነው።  የምህረት አዋጁን ለመጠቀም መቶ ሽህ ያህል ኢትዮጵያውያን ሰነድ ወስደዋል። ከተመዘገቡት 100 ሽህ ዜጎች መካከል እስከ 50 ሽህ ወደ ሀገር ገብተዋል ። ይህ እንግዲህ ባሳለፍነው ሶስት ወር በተደረገው መጠነ ሰፊ ቅስቀሳ አይደለም። ከሚያስፈራ፣ ከሚያሸብር፣ ከሚያንቀጠቅጠው የመንግስታችን ምክርና ዝክር ቅስቀሳ በላይ የሳውዲና የኢትዮጵያ የሰራተኛ አቅርቦት ስምምነት የተመዘገነው ውጤት መገኘቱን መካድ የማይቻል እውነት ሆኗል።

አጭሩን ጊዜ በአግባቡ ለመጠቀም …

ዛሬ ላይ የሁላችንም ድጋፍ አግኝተው ወደ ሀገር መግባት የሚፈልልጉ ቢያንስ በግምት ተጨማሪ 150 ሽህ ዜጎች አይጠፉም። እናም ወደ ፈተናው ሳንገባ በመጨረሻዎቹ የምህረት አዋጅ ሳምንታት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ያልተጠበቀ የበረራ እጥረት በተሰናከልንበት አካሄድ መነታረኩ አይበጀንም። ከተሰጠው 30 ቀን የቀረን 25 ቀን ብቻ ነው። አጭሩን ጊዜ በአግባቡ ለመጠቀም 100 ሽህ ዜጋ ሊወጣ ቢዘጋጅ ማድረግ ስለሚኖርብን ማስላቱ ይበጅ ይመስለኛል።

የበረራ ፈቃድና የአሻራ አሰጣጡ ተጠያቂ ማነው?

የዚህ ስሌት ውጤት በ25 ቀን 100 ሽህ ዜጋ ለማስወጣት በቀን 400 ሽህ ዜጋን ለመሸኘት የአየር በረራ ዝግጅት ስለመኖሩ ማደራጀት ይገባል።  ኃላፊነቱን ለመሸከም የኢትዮጵያ አየር መንገድንም ሆነ የሳውዲንና የተቀሩትን አየር መንገዶች ማዘጋጀትና ማደራጀት ይገባል። ከዚሁ በተያያዥ ለአዳዲስ ተመዝጋቢዎችና አሻራ ግልጋሎት ጠያቂዎች የተሳለጠ አገልግሎት ለመስጠት ከሳውዲ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች  ደረጃ መመካከር ቀዳሚ ተግባር መሆን ይገባዋል። ይህን አድርጎ ማስተካከል ካልተቻለ ኃላፊነቱን መውሰድ ያለበት የሳውዲ መንግስት ስለመሆኑ ማሳወቁ ተገቢ ይመስለኛል። “ውጡ” በ90 ቀናት ያየነውን አይነት ቢሮክራሲ መውጫ በሩን ከዘጋጉት ለሚፈጠረው መጓተት ኃላፊነቱን ሊወድስዱ እንደሚገባ በማያሻማ ቋንቋ ሊነገራቸው ይገባል። ይህ ካልሆነ ሰው ሊወጣ ፈልጎ “የአየር ማረፊያ እጥረት አለ፣ አሻራ ማድረግ በኮታ ነው!” እያሉ ዜጋውን ማመስ  ከላይ የተጠቀሰውን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ዜጋ እንዳይቀጣ እክል መሆኑን ማስረዳት ይገባል።

ስራው በማን ነው የሚሰራው? የዲፕሎማቶች?

ከላይ ያነሳኋቸውን በሳውዲና በኢትዮጵያ መንግሰት በኩል መደረግ ያለባቸው ስራዎች ከወዲህ ከተሰሩ ቀጣዩ የእኛ የዜጎች ጉዳይ ይመስለኛል። ወደ ራሳችን ጉዳይ ስንገባ … ወደ ወቅታዊውና መደረግ ወዳለበት ገፊ ሀሳብ አተኩረን በተቀናጀ አሰራር እጅ ለእጅ ተያይዘን ወደ ሀገር ለመግባት ፍላጎት ያላቸውን ወገኖች ልንደግፋቸው ይገባል በሚለው መስማማት ይገባል። ስራውን በበቂና በተደራጀ የሰው ሀይል በማሳለጡ ጉዳይ የማከርኳቸው በስውር የማገኛቸው አንድ በሪያድ ኢንባሲ የሚሰሩ ዲፕሎማት ወዳጄ ዛሬም ከውጭ ጉዳይ ወደ ሳውዲ ረዳት ዲፕሎማቶች ይላካሉ ተብሎ እንደሚገመት አጫውተውኛል። ይህ አዋጭ አለመሆኑ ለማስረዳት ምክንያቴን ማስረዳት ጠቃሚና ግድ ይሆንብኛል።  ከዚህ ቀደም ከመጡትና ከቆዩት ከሳውዲ ባህልና ከቋንቋው ያልተዋሃዱት አዳዲስና ነባር ዲፕሎማቶች በየቦታው ተመድበው ሲሰሩ ስራውን የሚሰሩት የመጡት ዲፕሎማቶች አይደሉም። ይልቁንም ስራው የተሰራውና የሚሰራው ለዲፕሎማቶች በተመደቡተ ሹፊር፣ አስተርጓሚና ጉዳይ ፈጻሚዎች ቢሆንም የዲሎማቶች ሰራ ስራው ተሰርቶ ሲያልቅ ፊርማቸውን ማስቀመጥ ብቻ ነው ማለት ይቻላል። ዋነኛው ስራ በረዳቶቻቸው መሰራቱን በገሃድ ለምናውቅ ዜጎች የውጭ ጉዳይ የሰው ሃይል ጭማሪ አዋጭ አይመስለኝም። ይልቁንም ለእነሱ የሚወጣው ከፍተኛ ደመወዝና የበርሃ የወል አበል የሀገርና የህዝብን ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ ከማባከን ባለፈ ስራውን የሚሰሩትን ቅጥር ሰራተኞች ድጎማና ማነቃቂያ በመሆን የተሻለ ስራ መስራት እንደሚያስችል መጠቆም ግድ ይላል። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይህንን ጉዳይ ልብ ሊለው ይገባል።

በቂ ድጋፍ ለማድረግ የሰው ሃይልን ስለማደራጀት …

ነዋሪውን በምዝገባ፣ በሰነድ ዝግጅት፣ በስነ ስርአት ማስከበር፣ ትራንስፖርት በማቅረብ፣ አሻራ በማሰጠትና በመሳሰሉት ድጋፎች ነዋሪውን ጥሪ አድርጎ ማስተባበር ይቻላል። ሰውም ለዚህ መሰል ድጋፍ ቀናኢ መሆኑን ተመልክተናል። በነዋሪው መካከል አረብኛ አቀላጥፈው የሚናገሩትን ታዳጊና ጎረምሶች ልጆቻችን ቋንቋና ባህሉን አሳምረው ስለሚያውቁት የተሻለ ስራ መስራት ይችላሉ። ከሳውዲ መስሪያ ቤቶች ጉዳይ ማስፈጸም ቢመደቡም ዲፕሎማት የሚያስንቁ ተቆርቋሪ ዜጎችን ናቸውማ ተማሪዎቻችን በሰፊው በማደራጀት የተሻለ ስራ መስራት ይቻላል።

ማህበር፣ ድርጅት ሊግ ኮሚኒቲና ሌላም ሌላ ታማኝ አደረጃጀቶች ባሳለፍናቸው 90 የምህረት አዋጅ ቀናት የሰሩት ስራ የሚደነቅና የሚያስመሰግን ነበር። ያም ሆኖ በጉልበት ከተሰራው ስራ ራዕይ ይዞ አስልቶ መስራት የሚችሉትን ባለሙያ ኢትዮጵያውያን ባሉነት ሀገር የቀረውን ነዋሪ ማግለሉ አልጠቀመም ካለፈው እንማር።  ማህበር፣ ድርጅት እየተጠሩ የመጣውን ሰው አስታውሳችሁ የዜጋውን ፍላጎት የምትረዱ ይመስለኛል። በእርግጥም ሰው በጥሪው ባይሳተፍ አልፈርድበትም። እኔም የዚህ ህዝብ አካል ነኝና ለሀገራዊው ድጋፍ ጥሪ የማህበር፣ የድርጅት ጥሪ ተጠይፊው ነበር። በእርግጥም ስለ ትልቅ ህዝብና ሀገር እየሰሩ ግልጋሎቱን ማህበር፣ ድርጅትና ምንቴስ እያሉ መለየቱ አዋጭ እልነበረም። ይህን የተሳሳተ አሰራር ዛሬ ከተገነዘብነው ለነገ ይጠቅመናል። ካለፈው የጎላ ስህተት ከተማርነበት ከነዋሪው መካከል መፍትሔ አስልተው የሚያቀርቡ በጎ ፍቃደኞችን ማቅረብ ተገቢ ነው። ዜጎችን ሳይለያዩ  በኢትዮጵያዊ ባንዴራ ጥላ ስር በማደራጀት ወደ ስራ መግባት ጊዜው የሚጠይቀው መፍትሔ ነው ብዬ አምናለሁ።

አጭር ጊዜ ተሰጥቶ ለምን ጊዜ እናጠፋለን?

የስራ ሰአትን በሚመለከት የጅዳ ቆንስል እሁድ ሰነድ መስጠት እንጀምራለን ያለውን ውሳኔ በመከለስ በአስቸኳይ ቢቻል ከዛሬ አርብ ጀምሮ ምክክሩን ጀምሮ ከቅዳሜ ጀምሮ ሰነድ መስጠት መጀመር አለበት። የአሻራ መስጫው ጊዜ ከእሁድ ሲጀመር ወደ ቦታው ዜጎችን ለማመላለስ ከዚህ ቀደም እንደነበረው ኮሚኒቲው የትራንስፖርቱን ኃላፊነት አደራጅቶ ማስጀመር ተገቢ ይመስለኛል። እንደ አስፈላጊነቱ ከበጎ ፈቃደኛው ነዋሪ በተጨማሪ ለአጭር ጊዜ ጊዜያዊ ሰራተኛ በመቅጠርና ለቆንስል ለኢንባሲ ሰራተኞች ድካም ተገቢውን የላብ ዋጋ ከፍሎ ስራውን በፈረቃ በ24 ሰዓት የሚሰራበት መንገድ ማፈላለግ የተሻለ ውጤት ማምጣትና ወደ ሀገር የሚገቡትን ዜጎች በሰላማዊ መንገድ በክብር መሸኘት ይቻላል።  ለዛሬው መሰረታዊ በምላቸው ጉዳዮች ያደረግኩትን ዳሰሳ በዚህ አበቃለሁ!

በህብረትና በአንድነት በተቀናጀ አሰራር የተሻለ ለውጥ ማምጣት ይቻላል! አጭሩን የተራዘመ የምህረት ጊዜ ለመጠቀም ከላይ ያነሳኋቸውን ሀሳቦች ለመፍትሔው ገንቢ ሀሳብ ናቸው ብዬ አምናለሁ ። በተሻለ አሰራር የተሻለ ውጤት ለማምጣት የሁላችሁን ዜጎች ጥቆማ፣ ሀሳብና አስተያየት ስራውን ለማሳካት ከፍ ያለ ግብአት ይኖረዋልና የሚመስለንን ጠቃሚ ሀሳብ ማንሸራሸር የማስበው ከሁላችንም ይጠበቃል።

ይህ የግል ምልከታዬ ነው!
ቸር ያሰማን!
ነቢዩ ሲራክ
ሰኔ 22 ቀን 2009 ዓም


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule