ሰዎች መልካም ሢሠሩና ሲናገሩ ማመስገን፣ መጥፎ ሢሠሩና ሲናገሩ ደግሞ መምከርና መገሰጥ ተገቢ ነው። ምንጊዜም ሁሉም ሰው ሕይዎቱን ሙሉ ስሕተት ብቻ እየሠራ አይኖርም። መልካም ነገሮችም ይሠራል። ልዩነት የሚኖረው የትኛው ሥራው ነው የሚያመዝነው? መልካሙ ወይስ መጥፎ የሚለውን መመዘኑ ላይ ነው። በዚህ ረገድ የሻለቃ ዳዊትን ሥራዎች መዝኖ፤ የማሞገሱም ሆነ የመውቀሱ ተግባር፣ እርሳቸውን የሚያውቁ፣ አብረዋቸው የሠሩ፣ የትaምህርትና የሥራ ባልደረቦቻቸው ተግባር ይሆናል።
ሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት ለዐማራ ነገድ ድምፅ ለመሆን የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ላይ ያለ ድርጅት ነው። ስለዚህ ሻለቃውን በዚህ ንግግራቸው፣ ላለፉት 5 ዓመታት ሲጮኽባቸው የነበሩ አንኳር ጉዳዮችን እያነሱ፣ ዐማራውን ሲያወግዙ፣ በጠላትነት ፈርጀው የዘር ፍጅት በፈጸሙ ግለሰቦችና ስብስቦች ፊት በኩራት ቆመው በመናገራቸው ከልብ ልናመሰግናቸው እንወዳለን። ዳዊት ይህን የተናገሩት ከሞረሽ ሞገስና ምሥጋና ፈልገው አይደለም። ድርጊቱ ዕውነት ስለሆነ ብቻ ነው። በሌላም በኩል እርሳቸው «ኢትዮጵያዊ እንጂ፣ ዐማራ ሆኜ አስቤ አላውቅም» ቢሉንም፣ «ትንሽ ሥጋ እንደ መርፌ ትወጋ»፣ «ምንም ብጠላው በወንድሜ ግንባር ደም አልይበት» የሚለው የአባቶቻችን አባባል አስሮ የያዛቸው ብቻ ሳይሆን፣ እንደ ሰብአዊ ፍጡር በዐማራው ላይ የተፈጸመው የዘር ፍጅት የሰው ልጅ ሊገምተው ከሚችለው በላይ በመሆኑ እንደ ሰው፣ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ አስበው የደረሱበት ድምዳሜ እንደሚሆን ይታመናል። በሌላ በኩል ዘረኛው የትግሬ ወያኔ አገዛዝ ዓላማና በዐማራው ላይ እየፈጸመው ያለው የዘር ዕልቂት ማንም ሊሸፋፍነው ከሚችለው በላይ ሆኖ ገዝፎ የወጣ በመሆኑና ይህንንም ሕዝቡ በግልጽ በመቃወም እየተዋደቀለት በመሆኑ፣ አድበስብሰው ሊያልፉት ከማይችሉበት ደረጃ የደረሱ መሆኑን መገንዘባቸው እንደሆነ መረዳት ይቻላል። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
በለው! says
_፟ሻለቃ ዳዊት አልተሳሳቱም! አማራና ኢትዮጵያን ማጥፋት ሲያስተምሩ የነበሩ የኦነግ መሪዎች ከእሳቸው በላይ አማርኛና ታሪክ አወቀው እያስተማሯችው ዛሬ ጥሩ ወዳጆች ሆነዋል …የሜንጫ አብዮተኛው ወጣት የፖለቲካ ተንታኝ/በታኝ ኢሳት ላይ ሲያስተመር እንደኖረው..ተስፋዬ ግብረእባብ በየስብሰባ አዳራሹና ፓልቶኩ አበባ አስበትኖ እንድሚበተናቸው ማለት ነው።
… ዶ/ር ሌንጮ ባቲ እንዳሉት ” አንድነት እያልን እንዳንጨፈላለቅ ኤርትራን አስገንጥለናል፡ ኦሮሞም መጨረሻው ገና አልታወቀም እኛ ያስተማርናቸው ዛሬ አብረውን የሉም ወጣቱ ምን እንደሚፈለግ አላወቅንምና መዋሸት አንፈልግም” ታዲያ በብሔራዊ አንድነት ጽዋ መዳራቱ ምንና ማንን ተይዞ ነው!? የት ሆኖ ነው? ከማን ጋር ነው? ግርምታችን ይህ ነው።
ሻለቃ ዳዊት የመሰከሩት “የአገር ቤቱ ሕዝብ ከዲያስፖራው መቅደሙን፣ በውጭ ያለው ልዩነት በውስጥ አለመኖሩን፣ የወያኔ ጥንካሬ የተመሠረተው፣ በተቃዋሚው ድክመት እንደሆነ፣ የተቃዋሚው አለመተባበር እንጂ፣ ወያኔ የዐማራውና የኦሮሞው ሕዝባዊ እንቢተኝነት እንቅስቃሴ ተገፍቶ ከሚወድቅበት ደረጃ ላይ እንደነበር አስረድተዋል።የመገናኛ ብዙኃን ባለቤት የሆኑ ቡድኖች ፉከራና ዲስኩር ብቻ!!! ዝግጅት የለም!!» ግን «አለን! መጣን! ደርሰናል» በማለት በብዙኃን መገናኛ መሣሪያዎች የሚደነፉትን «ዝግጅት አልባ» ቡድኖችንና ድርጅቶችን ኮንነዋል፡ እንቅስቃሴውን የምንመራው እኛ ነን» እያሉ ለእንቅስቃሴው የተለያዩ ስሞች በመስጠት ሲዘገብ የነበረው ውሸት እንደነበር እንዲህ ሲሉ ዕውነቱን በፊታቸው ቆመው አጋልጠዋል።” ጭራሽም ለድሃ ልጅ መታሰር መደብደብ መገደልም ህወአት/ኢህአዴግን ተራድተዋል ተጠያቂ ናቸው!።
»..ሻዕቢያና ህወአት…የግንጠላ አቀንቃኝንቃኞች ሻንጣ ተሸካሚ ኦነግ፡ኦብነግ የአንድ ጥርብ ኮብል እስቶን እንጂ ልዩነት አላቸው ኢትዮጵያን ከማጥፋት ይመለሳሉ ብለህ፡ በኤርትራ በኩል ነጻነት ይመጣል ብለህ፡ ቪዢን፡ አንድነት ኅበረት፡ብሔራዊ ቱሪናፋ እጅህ እስኪቃጠል ብታጨበጭብ፡ላንቃህ እስኪደርቅ አዳራሽ ወስጥ ብትጮህና ብታፏጭ፡ ውክልና ያላቸውና የሌላቸው እያልክ ከመለስ ዜናዊ የጥናት ማዕከል/ፋውንዴሽን ጥናት ብትረጭ “አማራ የሚወከለው ጠፍቶ ምንም እንኳ የዚያ ነገድ/ብሔር ባይሆኑም አመለካከቱ እንዲወከል ከኤርትራ..ጋሞጎፋ..ከንባታ…አገው ሂርና በተውጣጡ የህወአት ምልምል ታጋይ ጓዶች ጎድጓድ ተቆፍሮለት ሲገረፍ፡ሲሳደድ፡ሲታሰር፡ሲፈናቀል፡ሲገደል ኖሯል፤ «ዐማራው እየተጠቃ ያለው በፖለቲካ አቋሙ ሳይሆን፣ በማንነቱ፣ በዐማራነቱ ነው። የዐማራው ትግል የመኖር ወይም ያለመኖር ነው።» በማለት የዐማራውን መደራጀት አስፈላጊነትና ለመደራጀቱ ምክንያቱም ምን እንደሆነ በግልጽ ቋንቋ አስረድተዋል። ይበል እንላለን ሻለቃ ዳዊት! አሁን በአማራው መደራጀት የሚሞጣሞጡ ዓላማቸው…
(፩) ህወአት እንዳደረገው ብሔራዊ አንድነቱ የእነሱን ጉዳይ አስፈጻሚ ለመቅጠር ታማኝ አሽከር ያፈላልጋሉ፡
(፪) ቀድሞ አማራ የለም! በሚሉና አማራ እንዳያንሰራራ የጎንዮሽ እየወጋነው የህወአት ተቃዋሚ ነን የሚሉ ለማዳ ተቋቋሚዎች ፵፮ ዓመት በሁለት እግራቸው ሁለት ዛፍ ላይ ተንጠልጥለው ቀርተዋል።
፫) ሌሎቹ ደግሞ አማራ ቢትዮጵያ አንድነት ላይ ማተኮሩ የሌሎችን ተገንጣይን አስገንጣይ ሐሳብ ማስከዳቱ አናዷቸዋል እንደምንም “በዲሞክራሲ ብሔርተኝነት” እንኳን አብሮ ሊያኖር አብሮ ኳስ ማጫወት ባልቻለ ጎሮኖ/ክልል አስጥምቀው ሁሉም ነጻ አውጪና/ወጪ ሲሆን ኢትዮጵያ መፍረሷን እርግጠኞች ሆነው አማራ ነኝ ላለውና የግንጠላና ክልላዊ መንግስት መስራች ነኝ ፎጋሪ ሁሉ ያጨበጭባሉ አበባ ይበትናሉ….ከክልሉ ወጪ የተገኘ እንስሳ ይገደልን ይሞጋገሱበታል።
**«የዐማራው ሕዝብ በንቅናቄው ውስጥ ካልተወከለ አገራዊ ንቅናቄው አለ ለማለት አይቻልም» እንግዲህ የዚህ ግንቦት ግም ባለ ቁጥር የሚደረግ የጋብቻ ፊርማ መስከረም ሳይጠባ ጉዱ ይሰማል። ድሮም ከጠላት የበላና የወገነ የተሞዳሞደ እውነታው እንዲህ ቁልጭ ብሎ ይታያል።
https://youtu.be/Ja527XeeG4I
___ ይህ በትናንሽ ውርጋጥና ጨቅላ ሕጻናት በድራማ መልክ የአደባባይ ላይ ትዕይንት ባልከፋ የሰው(የበሉበትን) ሰንደቅ በክብር አውርዶ፡ የራስን መስቀል ነውር የለውም(!?)(መረጋገጥና ማንገለታታቱ እንጂ) ኢሳያስ አፈወርቂ(ቅ)እዚህ ሰንደቅ ሥር አልዘመረም? አልተማረም? አልበላም? የእናት ጡት ነካሽ መሆንና “ለኢትዮጵያ ሕዝብ የቋንቋና የነገድ ፌደራሊዝምን አልመኝም” እያሉ የግንቦት ፯ ጭፍሮች፡ኢሳትንና ቅድመ ደርግ ኪስ አውላቂ እነ ካሳ ከበደን ማሞኘትና ማጃጃል ይቀላል ሁሉም እንደእነሱ ፋራና ጤባ ነው ማለት ግን እራስን ማስገመት ብቻ ሳይሆን ባንዳ/ሹምባሽ(የባዕድ ወገን ዶሮና እንቁላል አቅራቢነት ነው።)
___ እንግዲህ ይህ የሚሽነሪ የፋፋና የወተት ዱቄት በአፋቸው የሚበን ደግሞ ንጉስ በመዝለፍ፡ ነገድ በመሳደብ የኅብረትና አንድነትን “አንድ አደለንም ወያኔን ለመጣል አጋርነት/ትብብር እንፈልጋለን” የሚሉ ቱማታን የወደፊት የአማራን ዘር ማጥፋት ስብክታቸው ለራሳቸው ጋላ… በሱማሊኛ መጤ ጎረቤት ሃይማኖት አልባ ጨካኝ የሚለውን በሕግ አሰርዘው ሌላውን መጤ ፡ ሰፋሪ፡ነፍጠኛ ቆማጣ ለማለት በጫካው ማኒፌስቶ በከተማው የሕገ መንግስት ጥቅማጥቅም ሙሉ መብታቸው ተጠብቋል ህወአት ሲገርፍ ሲገድል የ፻፵ ዓመት ወሬ ይዘው በአማራ ላይ ይደነፋሉ ይዝታሉ ሜንጫ ይስላሉ…”ብልጥ ልጅ እየበላ ያለቅሳል” ይሉሃል ይህ ነው። https://youtu.be/-I52nc54wI4
… ይህ መረን የለቀቀ ጋጠወጥ የፖለቲካ ድሪያ ዘላቂውን መጪ ግዜ በከባድ ጥያቄ ውስጥ ይከተዋል ለአምጭው ይከፈላል! መንግስት ይወድቃል ሕዝብ ግን ይኖራል ለአብሮ መኖር መከባበር !! ሠላም ለሁሉም ይሁን
Mulugeta Andargie says
Guys!!! Nowadays, people are screaming as if they are worried and concerned for the people of Ethiopia. Among them, Major Dawit W/Giorgis could be pointed out as an example. Major Dawit was highly respected and official person during Mengistu’s regime. The Dergue regime was known as racist and one man dictatorship. Major Dawit was a right hand person for that regime. He now is a very close friend of Mr. Issayas Afeworki. This guy is running here and there for nothing, but to be seen, as if he is a very concerned man for his country. For Ethiopia. Not only him; Dr. Aregawi Berhie is the added one, besides, we don’t forget Dr. Berhanu Nega Bonger. These are the major drama players. The Editor of this magazine copied and showed us the useless speech of Major Dawit. More less, the truth will come out. Three of them betrayers. Their major ego was to fulfill the “boss” wishes. That is to make or paint wrong ideas on our present government. This must be known by anyone. Three of them are being chased by our government. They are guilty!!! They are criminals!!! Looters!
Ali says
Mr. Mulugeta Andargie (I would bet this is not your real name)
It’s nice that you came openly by saying “our government”, yes it’s “yours”; the Ethiopian people government, which would include all the people like, Lencho Bati, Birhanu Nega & more others you mentioned above, would be a reality in the new future.
Mulugeta Andargie says
Hey!!! “Ali!!!” Did you hear the day before yesterday’s new about Finffinee??? The House of The Ministers passed bill. It is our constitution!!! It is our government!!! It is our people!!! We proud of our government with practical workout!!! Did Berhanu Nega Bonger forced to do so???? Congratulation Ali!!! You should proud of the sudden bombs!!!!