• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

Opinions
የኔ ሃሳብ

ከ33ቱ የአዳማ ፔቴሽን ፈራሚ ፓርቲዎች የተሰጠ መግለጫ

January 10, 2013 04:33 pm by Editor Leave a Comment

ከ33ቱ የአዳማ ፔቴሽን ፈራሚ ፓርቲዎች የተሰጠ መግለጫ

በምርጫ አስፈፃሚው፣ ከምርጫ አስተዳደርና በምርጫው ሂደት ላይ የሚታዩ መሠረታዊ ችግሮችን በማንሣት ችግሮቹ ስለሚፈቱበት መንገድ የውይይት /ምክክር/ መድረክ እንዲመቻች ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድና ለመንግሥት አካላት ጥያቄአችንን ማቅረባችን ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የማያሣምኑ ምክንያቶች በመስጠት ጥያቄዎቻችንን ሙሉ በሙሉ ውድቅ ማድረጉን በቃል የገለፀልን ሲሆን ለመንግሥት ላቀረብነው ጥያቄ ምላሹን እየተጠባበቅን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የተጣለበትን የአገርና የሕዝብ ኃላፊነት ወደጐን በመግፋት ምርጫውን ሠላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊ፣ ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ ለማድረግ የመወዳደሪያ ሜዳውን ከማስተካከል ይልቅ የገዢው ፓርቲ ወገንተኝነቱንና ጉዳይ ፈፃሚነቱን ባረጋገጠበት አቋሙ በመግፋት ወደ ምርጫ እንቅስቃሴ መግባቱን በይፋ አውጇል፡፡ እኛ በያዝነው … [Read more...] about ከ33ቱ የአዳማ ፔቴሽን ፈራሚ ፓርቲዎች የተሰጠ መግለጫ

Filed Under: Opinions Tagged With: Middle Column

ይድረስ ለፈጣሪ!

January 10, 2013 09:07 am by Editor 2 Comments

ይድረስ ለፈጣሪ!

ተጣፈ ተኔ «ወተህ ወርደህ የላብህን ወዝ ትበላለህ» ብለህ ወደ መሬት ከላከው የአዳም የልጅ፤ ልጅ፤ ልጅ፤ ልጅ፤ ልጅ፤ … አንዱ፤ ላንተ በሰማዬ ሰማያት ላለኸው አምላክ:: እነሆ ይችን ደብዳቤ በመልክተኛህ በመላኩ ገብርኤል በኩል ላንተ ስልክ፤ ካገኘህ ለራስህ በእጅህ እንዲሰጥ፤ ካጣህም ለእናትህ ለወላዲት አምላክ፤ እንዲሰጣትና እሷ እንድትሰጥህ አደራ ብዬዋለሁ:: አምላክ ሆይ ! ከጭቃ አድቦልቡለህ የፈጠርከው ሰውን ያህል ጨካኝ ፍጡር አንቱ እያልኩ፤ አንተን አንቱታ በመንፈጌ ከድፍረት እንደማትቆጥርብኝና ቁጣህ እንደማይበረታ አውቃለሁ፤ አንተታዬ የመውደዴና ላንተ ያለኝ የክበር መግለጫ መሆኑን አንተው ታውቃለህና! ይኸውልህ ጉዳዩ እንዲህ ነው: ፈጣሪ በጆሮው ላይ ተኝቶ የሕፃናትን ለቅሶ፤ የዕናቶችን ዋይታ፤ ያባቶችን ጣር፤ አልሰማ ብሏል፤ … ሕዝብ መከራው በዝቶ፤ የበደል ገፈቱ ገንፍሎ … [Read more...] about ይድረስ ለፈጣሪ!

Filed Under: Opinions

የተቃዋሚ ፖለቲካ ኃይሎች የተግባር ድክመት ወይንስ የግብና እቅድ ልዩነት

January 10, 2013 08:51 am by Editor 2 Comments

የተቃዋሚ ፖለቲካ ኃይሎች የተግባር ድክመት ወይንስ የግብና እቅድ ልዩነት

“የተቃዋሚ ፖለቲካ ኃይሎች በድረ-መለስ ኢትዮጵያ፣ ርዕዩተ ዓለምና የትግል ግብና ዕቅድ ሁኔታዎች”  በሚል ርዕስ አቶ ጋሻው ዓለሙ ጥሩ የመወያያ ሃሳብ አቅርበውልናል። ማለፊያና ብዙ የምስማማባቸውን ነጥቦች የያዘ በመሆኑ፤ ላመሰግንና ድጋፌን መስጠት እፈልጋለሁ። መቼም ብዕሬን ያነሣሁ ተስማምቻለሁ ለማለት ብቻ አይደለም። የተስማማሁባቸውን መደረቱም አንባቢን ማድከም ነው። የማቀርበው ለየት ያለ አቀራረብ ሊኖረው ይገባ ነበር ያልኳቸውን ላመላክት ነው። በመጀመሪያ ደረጃ በኔ በኩል ድክመት ሳይሆን ልዩነት ነው ያለው። በርግጥ በተለያዬ መልክና ቦታ ይኼ ጉዳይ በጽሑፉ ውስጥ ተጠቅሷል። ነገር ግን ማዕከላዊ ቦታ መያዝ የሚገባው ጉዳይ ተለጣፊ በመሆን ቀርቧል ባይ ነኝ። እንዲህ ነው። የተቃዋሚ ፖለቲካ ኃይሎችን አንድ ተግባር እንዲፈፅሙ እንፈልጋለን። ይኼም ተግባር የዘረኛውን አምባገነን የወያኔ … [Read more...] about የተቃዋሚ ፖለቲካ ኃይሎች የተግባር ድክመት ወይንስ የግብና እቅድ ልዩነት

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

The role of higher education and Ethiopia

January 9, 2013 01:39 pm by Editor Leave a Comment

The role of higher education and Ethiopia

My beautiful and brilliant niece graduated from college a few days ago. We are all proud and happy with her accomplishment. It gave the whole family an opportunity to get together. Believe me the festival was preserved on video and camera, posted on Facebook, published on Instagram and micro blogged on tumblr. That is how important it was. No question it was a proud moment for her parents and an early Christmas present to the whole clan. We were lucky and our daughter was strong and focused and … [Read more...] about The role of higher education and Ethiopia

Filed Under: Opinions

አቶ መለስ ዜናዊ የ2012 ታላቅ ኢትዮጵያዊ ይሁኑን?

January 6, 2013 11:30 am by Editor 2 Comments

በ2012 በኢትዮጵያውያን ትዝታ ውስጥ በጉልህ የሚታወሰው የአቶ መለስ ዜናዊ ህልፈተ ህይወት ነው። አቶ መለስ በጠና ታመዋል የሚለው ዜና ተንጠባጥቦ መሰማት ከጀመረበት ከጁላይ 15 ጀምሮ በኢትዮጵያ የፓለቲካ ምህዳር ውስጥ ከፍተኛ መናወጥ ተጀመረ። ነዉጡ አላቆመም። አሁንም ቀጥሏል። (ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል) … [Read more...] about አቶ መለስ ዜናዊ የ2012 ታላቅ ኢትዮጵያዊ ይሁኑን?

Filed Under: Opinions

የጄራርድ ዲፓርዱ የሩሲያዊ ዜግነት ጥያቄና ሀገር ማለት

January 6, 2013 09:43 am by Editor Leave a Comment

የጄራርድ ዲፓርዱ የሩሲያዊ ዜግነት ጥያቄና ሀገር ማለት

በዓለም የተበተንነው ኢትዮጵያዊያን ቁጥር በጣም ብዙ ነው። አሁንም ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ ዓለም ለመውጣት ጥረት የሚያደርጉ ወገኖቻችን ቁጥር ቀላል አይደለም። በውጭ የምንኖረው፤ በየምንኖርበት ሀገር፤ የሀገሩን ዜግነት በተለያዬ ምክንያት የወሰድንና ያልወሰድን አለን። ይኼ ሁሉ እንዳለ ሆኖ ግን፤ እኔም ሆንኩ እኔ የማውቃቸው ኢትዮጵያዊያን፤ ሀገራችን በልባችን ቋጥረን ነው የምንጓዘው። እኔ ቁጥሬ፤ በንጉሠ ነገሥቱ ጊዜ ተወልደው አድገው፣ የንጉሠ ነገሥቱን አገዛዝ ኋላ ቀር ነው ብለው ተቃውመው፣ በደርግ ጊዜ ግብግብ ገጥመው፣ አሁንም የወያኔን የፖለቲካ ፍልስፍናና የአስተዳደር መመሪያ በመቃወም ከሀገር ውጪ ካሉት ወገን ነው። በአስተዳደጋችን ሆነ በእምነታችን፤ ሀገራችን ከማንም ሀገር አሳንሰን ተመልክተን አናውቅም። የገዢዎቻችን ተግባር እንጂ፤ የሀገራችን ጉዳይ ላንዳፍታም እንኳ ጥያቄ ውስጥ … [Read more...] about የጄራርድ ዲፓርዱ የሩሲያዊ ዜግነት ጥያቄና ሀገር ማለት

Filed Under: Opinions

የተቃዋሚ ፖለቲካ ኃይሎች በድረ-መለስ ኢትዮጵያ፣ አይዲዮሎጂካል እና ስትራተጂካዊ ሁኔታዎች

January 5, 2013 11:19 am by Editor 1 Comment

1. መግቢያ የጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊን ህልፈተ-ህይወት ተከትሎ በኢህአዴግ እና በተቃዋሚ ኃይሎች የሚታየው የመረበሽና ትርምስምስ በመሰረታዊነት ምንጮቹ ፖለቲካዊ፣ ወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ቢሮክራሲያዊ ስልጣኖችን በአጠቃለለ ሁኔታ ጠ/ሚ መለስ በእጃቸው ማስገባታቸውና በእሳቸው ህልፈተ-ህይወት ምክንያት የተከፈተውን የስልጣን ክፈተት የሚሞላ ተቋማዊ አቅም አለመገንባቱና ሁለተኛ ግለሰብ በስርአቱ ውስጥ አለመኖር ናቸው:: ስለዚህም በእርሳቸው ህልፈተ-ህይወት የተፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት... (ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል) … [Read more...] about የተቃዋሚ ፖለቲካ ኃይሎች በድረ-መለስ ኢትዮጵያ፣ አይዲዮሎጂካል እና ስትራተጂካዊ ሁኔታዎች

Filed Under: Opinions

የማፍረስ አባዜ

January 1, 2013 11:24 am by Editor 3 Comments

የማፍረስ አባዜ

በአለፉት ሃያ አንድ ዓመታት፣ በተለይም ከ1997 ዓ.ም. ወዲህ፣ የወያኔ/ኢሕአዴግ አገዛዝ ልዩ መታወቂያው ያደረገው  እያፈረሱ መገንባትን ነው፤ ማፍረስ ቀላል ሥራ ነው፤ ጭንቅላትም፣ ማሰብም አይጠይቅም፤ ልብም፣ ስሜትም አይጠይቅም፤ የሚጠይቀው የዝሆን አካልና ጉልበት ብቻ ነው፤ አንድ ቤተሰብ ስንት ዓመት በዚያ ቤት ውስጥ ኖረ? ጎረቤቶች ምን ዓይነት ትስስር አላቸው? በማኅበር፣ በእድር፣ በዝምድና በቤተ ክርስቲያን ወይም በቤተ መስጊድ፣ በመቃብር፣ በሥራ፣ በአጠቃላይ የእያንዳንዱ ሰው ኑሮ ከልደት ጀምሮ የተፈተለበትና የተደራበት ውስብስብ የኅብረተሰብ አካል መኖሪያ ነው፤ ይህንን አካል ለማፍረስ ትንሽ ጭንቅላትና ግዙፍ ጡንቻ ያለው አይቸግረውም፡፡ መኖሪያ ቤቶችን ማፍረስ፣ መቃብሮችን ማፍረስ፣ የንግድ ድርጅቶችን ማፍረስ፣ ትምህርት ቤቶችን ማፍረስ፣ … ማፍረስ… ማፍረስ… ማፍረስ! ሳያለቅሱ … [Read more...] about የማፍረስ አባዜ

Filed Under: Opinions Tagged With: Full Width Top, mesfin, Middle Column

አክሱምን ወላይታ አገኘሁት!!!

December 31, 2012 04:43 am by Editor 1 Comment

አክሱምን ወላይታ አገኘሁት!!!

ኅዳር 12 ቀን 2005 ዓ.ም በሥራ ጉዳይ ወደ ጋሞ ጎፋ ዞን ዋና ከተማ አርባ ምንጭ መሄድ ነበረብኝ፡፡ ለሁለት ቀን ተኩል የሚበቃኝን  ሸክፌ ከመሥሪያ ቤቴ በተመደበልኝ መኪና ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ለሚነሳው በረራ ለመድረስ ወደቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ጉዞ ጀመርኩ፡፡ በቅዱስ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን በኩል ወደ ቦሌ የሚወስደውን መንገድ ይዘን ስንጓዝ ከመንገዱ ግራ እና ቀኝ ላይ የተደረደሩት የፌደራል ፖሊስ አባላት አቀባበል ወይንም ሽኝት የሚደረግለት ባለሥልጣን/እንግዳ እንዳለ ስለጠቆመኝ መንገዱ ሳይዘጋ ቦሌ ለመድረስ ጥረት እንዲያደርግ ለሹፌሩ ጠቆምኩት፡፡ ብዙም ሳንጓዝ አትላስ ሆቴል የትራፊክ መብራት ላይ ስንደርስ በስፍራው የነበሩት የትራፊክ ፖሊሶች ወደ ቺቺንያ ወይንም ወደ ቦሌ ሩዋንዳ የሚወስደውን መንገድ እንድንጠቀም አስገደዱን፡፡ ወዲያውኑ ሰዓቴን ተመለከትኩ፤ ለሰባት … [Read more...] about አክሱምን ወላይታ አገኘሁት!!!

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

የተመሠቃቀለውን የፖለቲካ ውጥንቅጣችንና ነፃነታችን።

December 30, 2012 04:26 am by Editor Leave a Comment

በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ የወያኔን ቡድን ከሥልጣን ለማውረድ የሚደረገው ትግል አሁንም ቀጥሏል። ይህ ትግል አንድነት የለውም። ይህ ትግል አንድ ማዕከል የለውም። ይህ ትግል አንድ መሪ የለውም። ያለንበትን መርምረን ወደፊት እንዴት እንደምንሄድ መወያየት አለብን። ለዚህ ይረዳ ዘንድ፤ በኔ በኩል መደረግ አለባቸው የምላቸውን እጠቁማለሁ። ይቺ ሀገር ያንቺም፣ ያንተም፣ የነሱም፣ የኛም የሁላችን የኢትዮጵያዊያን ሀገር ናት። ስለሆነም ሁላችንም ለወደፊቷ እኩል ባለጉዳዮች ነን። ማንም የነገዋን ሀገራችን እድል ሲወስን፤ እኛ የበይ ተመልካች መሆን አይገባንም። “ከወያኔ የተሻለ እስከመጣ ድረስ እኔ ምን ቸገረኝ!” ብለን ለሌሎች ጉዳዩን የምንተወው ሊሆንም አይገባም። አዎ የሚሻል ይኖራል። ያባሰም አለ። የሚሻለውም ሆነ የባሰው ሲመጣ የራሱን አጀንዳ ይዞ ስለሆነ የሚመጣው፤ እኛም ሆነ የሀገራችን ጉዳይ … [Read more...] about የተመሠቃቀለውን የፖለቲካ ውጥንቅጣችንና ነፃነታችን።

Filed Under: Opinions

  • « Previous Page
  • Page 1
  • …
  • Page 159
  • Page 160
  • Page 161
  • Page 162
  • Page 163
  • …
  • Page 166
  • Next Page »

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule