• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የጄራርድ ዲፓርዱ የሩሲያዊ ዜግነት ጥያቄና ሀገር ማለት

January 6, 2013 09:43 am by Editor Leave a Comment

በዓለም የተበተንነው ኢትዮጵያዊያን ቁጥር በጣም ብዙ ነው። አሁንም ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ ዓለም ለመውጣት ጥረት የሚያደርጉ ወገኖቻችን ቁጥር ቀላል አይደለም። በውጭ የምንኖረው፤ በየምንኖርበት ሀገር፤ የሀገሩን ዜግነት በተለያዬ ምክንያት የወሰድንና ያልወሰድን አለን። ይኼ ሁሉ እንዳለ ሆኖ ግን፤ እኔም ሆንኩ እኔ የማውቃቸው ኢትዮጵያዊያን፤ ሀገራችን በልባችን ቋጥረን ነው የምንጓዘው። እኔ ቁጥሬ፤ በንጉሠ ነገሥቱ ጊዜ ተወልደው አድገው፣ የንጉሠ ነገሥቱን አገዛዝ ኋላ ቀር ነው ብለው ተቃውመው፣ በደርግ ጊዜ ግብግብ ገጥመው፣ አሁንም የወያኔን የፖለቲካ ፍልስፍናና የአስተዳደር መመሪያ በመቃወም ከሀገር ውጪ ካሉት ወገን ነው። በአስተዳደጋችን ሆነ በእምነታችን፤ ሀገራችን ከማንም ሀገር አሳንሰን ተመልክተን አናውቅም።

የገዢዎቻችን ተግባር እንጂ፤ የሀገራችን ጉዳይ ላንዳፍታም እንኳ ጥያቄ ውስጥ አላስገባንም ነበር። በርግጥ በወያኔ አራጋቢነትና እንገንጠል ባይ ታጋዮች፤ ኢትዮጵያዊነት ባሁኑ ሰዓት ጥያቄ ውስጥ መግባቱን አልክድም። እስከ ጥቂት ዓመታት ድረስ፤ ቢያንስ እኔ ባለሁበት አካባቢ ያለን ኢትዮጵያዊያን፤ ከሞላ ጎደል ሁላችንም፤ ሻንጣችንን አዘጋጅተን ሀገር ለመግባት የተዘጋጀን ነበር የምንመስለው። ከመካከላችን አንዱ ቤት ንብረት ካዳበረ፤ ይኼ ሰው ተደላደለ በሚል ዓይን የሚመለከተው ቁጥሩ ቀላል አልነበረም። ይህ ደግሞ፤ በታጋይ ድርጅቶች ዙሪያ ያሉትንም ሆነ በድርጅት ያልታቀፉትን ያካትት ነበር።

ያጠናነው የትምህርት መስክ አስገድዶን፤ ከመንግሥት ጋር የተያያዘ የሥር መስክን የሚያክ በመሆኑ፤ የአሜሪካን የዜግነት መሐላ ለፈፀምነው፤ የነበረብን ፍጥጫ ቀላል አልነበረም። ይህ እንግዲህ፤ በአሜሪካ ብቻ የሚታይ አይደለም የሚል ግምት አለኝ። በአውስትራሊያም ሆነ በአውሮፓ፤ በአረብ ሀገሮችም ሆነ በአፍሪቃ፤ ተመሳሳይ ክንውኖች ይተገበራሉ የሚል ግምት አለኝ። የዚህ ሁሉ ድርደራ መልዕክቱ፤ እኔም ሆንኩ የማውቃቸው ኢትዮጵያዊያን፤ ሀገራችንን ከግል ኑሯችን ውጪ በልባችን ይዘን የምንጓዝ መሆናችንን ለማመልከት ነው። የእኔ የግል የኑሮ ሁኔታም ሆነ ያለኝ አመለካከት፤ ሀገሬን ከኔ እንዳወጣት መንገድ አይከፈትለትም። ስለከፋኝ ወይንም ስለደላኝ፣ ስለተራብኩ ወይንም ስለጠገብኩ፤ የፖለቲካ እምነቴ ግራ ስለገባ ወይንም ቀኝ ስለዘመተ፣ በአስተዳዳሪዎች በደል ስለተፈፀመብኝ ወይንም ስለተሾምኩ፤ የተሰደድኩበት ሀገር ስለደላኝ ወይንም ስለከፋኝ፤ የሀገሬ ሀገሬ መሆን አይለወጥም። እኔ ብቻ አይደለሁም። እኔ የማውቃቸው በሙሉ ማለቴ ነው።

በርግጥ ለኔ ይኼን ገፅ አሳይተውኝ እነሱ ሌላ እምነት ይዘው ቢገኙ ተጠያቂ አልሆንም። ታዲያ አደንቀው የነበር ፈረንሳዊ የኪነ ጥበብ ሰው፤ ጄራርድ ዲፓርዱ፤ ፈረንሣዊነቱን ትቶ ሩሲያዊ ሊሆን ሲወስንና ሲተገብረው፤ ደነገጥኩ። እንዲህ ነው።  ጄራርድ ዲፓርዱ የታወቀ ፈረሣዊ የኪነት ሰው ነው። በእንግሊዝኛና በፈረንሣይኛ ከሠራቸው ፊልሞቹ መካከል ጥቂቶቹን በማየት አወቅሁት፤ አደነቅሁትም። ታዲያ ደግሞ ጥሩ ብዬ፤ በዚያ ቦታ ካስቀመጥኳቸው የኪነት ሰዎች ጋር ሰቅዬ አስቀመጥኩት። ለዚህ ይመስለኛል መደንገጤ። የራሴው ግንዛቤ እንጂ ከሱ ጥፋት የለም። ወደ ራሴ ተመልሼ እኔና ሀገሬን ተመለከትኩ። ደገመችና ብሪጂት ባርዶ ተከተለችው። እሷም ሌላዋ ፈረንሳዊት ነች፡ የሱ ምክንያት፤ “ገንዘቤን እወዳለሁ፤ ግብራችሁ በዛብኝ!”  ነው። የሷ ደግሞ፤ “ሁለት ዝሆኖች ስለታመሙ ፤ ልትገድሏቸው ወስናችኋል። ለኔ ስጡኝና እኔ እጦራቸዋለሁ። አለበለዚያ ግን ሩሲያዊ እሆናለሁ።” ብላ ነው።

መቸም በስለላ ተግባር ተመድበው ወይንም ለሌላ መንግሥት ሲሰልሉ ሊደረስባቸው ሲል ሀገር ጥለው የሚጠፉና ዜግነትን የሚወስዱ መኖራቸው አዲስ አይደለም። በፖለቲካ አመለካከታቸው የተፈረደባቸውና ሀገራቸው የተወረረባቸውም ምርጭ ሲጠፋ ሌላ ዜግነት መውሰዳቸው ያለ ነው። ለኔ ይኼ ካልተደረገልኝ ወይንም በሀገሪቱ እኔ የምለው ካልተፈፀመ ሀገሬን ለቅቄ የሌላ ሀገር ሰው እሆናለሁ ብሎ መዛትና ይኼንኑ መፈፀም ግን ለኔ እንግዳ ሆኖብኛል። መቼም እድሜ ልኬን ተማሪ ነኝና፤ ይኼም አዲስ ትምህርት ሆኖልኝ እስክረዳው ድረስ ይቆረቁረኛል። ይኼም አለ ለካ የሚያሰኘው እንዲህ ዓይነቱ ነው።

ለኔ ይኼ ካልሆነ ወይንም እኔ ተበደልኩ የሚለው፤ ሀገርን የአሁን ክንውን ያደርገዋል። አሁን ደግሞ ከታሪክና ከባህል ያልተያያዘና ጊዜውን ጠባቂ ነው። ታዲያ የሀገርን ምንነት በአሁንና በአሁን የግል ግንዛቤያችን ካስቀመጥነው፤ ያለታሪክና ያለባህል፤ ሀገር የትም ይጣላል። የጄራርድ ዲፓርዱ እና የብሪጂት ባርዶ ውሳኔ ይኼው ነው። ግብሩን አበዛችሁት ወይንም እኔ የምላችህን ካልፈፀማችሁ ማለት ሌላ ትርጉም የለውም። በግለሰብ ደረጃ፤ ጄራርድን ወይንም ብሪጅትን ትክክል አይደሉም ማለቴ አይደለም። ለዚህ ያበቃቸው፤ አስተዳደጋቸው፣ ሀገራዊ እሴታቸው፣ የፖለቲካ አመለካከታቸውና ከገንዘብ ጋር ያላቸው ፍቅር ወይንም ባጠቃላይ የንብረታቸው ብዛት አስተዋፅዖዎች አሏቸው።

የኔ አስተዳደግ፣ የፖለቲካ አመለካከቴና ሀገራዊ እሴቴ ተቃራኒውን ያሳዩኛል። ለዚህም ነው መደንገጤ። ያስገረመኝ ደግሞ፤ ከሩሲያ እየወጡ በዓለም ዙሪያ የተለያዩ ሀገሮችን ጥገኝነት የሚጠይቁ ሰዋች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ ነው። ፈረንሳይ ጥገኝነት ከሚጠይቁባት ሀገሮች አንዷ ናት። ይህ ደግሞ የእስራዔል ዝርያ ያላቸውን ብቻ አይደለም የሚያካትተው። ጄራርድ፡ “ሀገራችሁን ሩስያን አደንቃለሁ። ሕዝባችሁ፣ ታሪካችሁ፣ ጸሐፊዎቻችሁ . . . ባህላችሁና የአስተሳሰብ ሂደታችሁ . . . ሩስያ የታላቅ ዴሞክራሲ ሀገር ናት።”  አለ። በሀገራችን “የሚጥምህንማ አንተ ታውቃለህ!”  ያለውን ገበያተኛ አስታወሰኝ። ነገሩ እንዲህ ነው። አንድ የደለበ በግ ይዞ ገበያ የወጣ ሺያጭ፤ አንድ ገዢ መጥቶ፡ “ዋጋው ስንት ነው ይኼ በግ?” ይለዋል። በዚያን ጊዜ እንዲህ ነበር ማለቱ እኔን ከነ አባ ክልል ቢያስገባኝም፤ (ያኔ አንድ የአሜሪካ ዶላር ሁለት የኢትዮጵያ ብር ነበር ምንዛሬው) “ሃምሳ ብር ነው።” ይለዋል ሺያጭ። “እንዴ ይኼማ የጠገበ አህያ ያስገዛኝ የለም።” ይላል ገዢ የገንዘቡ መብዛት አስገርሞት። “ጌታው፤ የሚጥምህንማ አንተ ታውቃለህ!” በማለት የልቡን ቁስል በሰውዬው ጅንን ራሱን የማክበር ሰቀላው ላይ አዶለበት። የጄራርድን ዴሞክራሲያ ፍለጋ ወደ ሩስያ መንጎድ፤ በዚህ ዓይን ነው ያየሁት።

ከሞላ ጎደል ሁሉም ኢትዮጵያዊያን አላቸው ብዬ ከምገምተው ነገር አንዱ፤ ሀገራችንን ወዳድ መሆናችንን ነው። ገዥዎቻችንን ከሀገራችን ለይተን ነው የምናየው። ገዥዎቻችን እንዲህ አደረጉን እንጂ፤ ሀገራችን እንዲህ አደረገጭን ብለን ሀገራችንን አንወነጅላትም። ይኼን ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁት፤ ኢሳያስ ኢትዮጵያን እንዲጠሉ፤ “ኢትዮጵያ መጣችባችሁ!” እያለ፣ አውሮፕላን በሰማይ ስትመጣ፤ ኤርትራዊያንን ሲያስፈራራቸው ነው። እኛ ከዚህ የተለይን ነን። አመለካከታችንም እንዲሁ። “እናንተ የፈለጋችሁትን የምታደርጉባት የግል ንብረታችሁ አይደለችም።”  በማለት። ለዚህም ነው ገዥዎቻችንን የምንታገለው። ሀገራችን የሁላችንም ናት።

ጥር ፳ ፮ ቀን ፳ ፻ ፭ ዓመተ ምህረት

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule