በሕገ-ወጥ መንገድ ገንዘብ ያዘዋወረ፣ በዝውውሩ የተሳተፈና ለአዘዋዋሪዎች ሽፋን የሰጠ 10 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራትና የገንዘብ ቅጣት እንደሚጠብቀው የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አስታወቀ። ባለፉት ሁለት ዓመታት በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በሕግ አስከባሪ አካላት ቁጥጥር ስር እየዋለ መሆኑ በአገሪቱ በሕገ-ወጥ መንገድ የሚዘዋወር ገንዘብ የመኖሩ አንድ ማሳያ ነው። በመሆኑም በዚሁ የሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ተግባር ላይ ተሳታፊ የሆነ ማንኛውም አካል በወንጀል ሕግ ከመጠየቅ እንደማይድንም ጠቅላይ አቃቤ ግህ ጠቁሟል። በኢትዮጵያ በ1996 ዓም በወጣው የወንጀል ሕግ መሰረት በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ውስጥ ተሳትፎ የተገኝ ማንኛውም አካል እስከ 10 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about በገንዘብ ዝውውር የተከሰሰ በ10 ዓመት ጽኑ እሥራት ይቀጣል
new currency
ከብር ለውጡ ጋር በተያያዘ ንብረትን በስጦታ ማስተላለፍ ታገደ
የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል እንዲሁም የብድር ውሎችን ሰነድ አረጋግጦ የመመዝገብ አገልግሎት ላይ የአሠራር ለውጥ ማድረጉን ተናገረ። እነዚህን አገልግሎቶች ለማግኘት የሽያጭ ዋጋ ወይም የብድሩ ገንዘብ አከፋፈልን በተመለከተ ክፍያው መፈጸም ያለበት፦ በሽያጭ ውል ጊዜ የሽያጭ ዋጋው ባንክ ከሚገኝ የገዢ ሂሳብ ተቀናሽ ሆኖ ወደ ሻጭ የባንክ ሂሳብ የተላለፈ (Transfer) መሆን አለበት፣በብድር ውል ጊዜ የብድሩ ገንዘብ ባንክ ከሚገኝ የአበዳሪ ሂሳብ ተቀናሽ ሆኖ ወደ ተበዳሪ የባንክ ሂሳብ የተላለፈ (Transfer) መሆን አለበት ሲል የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ለሸገር ነግሯል። ይህ አሰራርም ከነገ መስከረም 7፣2013 ይጀመራል ተብሏል። በተጨማሪም ህገወጥነትን ለመከላከል ሲባል … [Read more...] about ከብር ለውጡ ጋር በተያያዘ ንብረትን በስጦታ ማስተላለፍ ታገደ
“በጥቁር ገበያ” ምንዛሪ የተጠረጠሩ ሱቆች ታሸጉ
የኢትዮጵያ መንግስት አሁን በአገልግሎት ላይ የሚገኙትን የብር የገንዘብ አይነቶች እንዲሚቀይር በትላንትናው ዕለት ማስታወቁን ተከትሎ የ“ጥቁር ገበያ”ውን ለመቆጣጠር እርምጃ መውሰድ ተጀመረ። በአዲስ አበባ ከባንክ ውጭ የሚደረጉ የውጭ ሀገር ገንዘብ ግብይቶችን በድብቅ ያከናውናሉ ከተባሉ ሱቆች መካከል የተወሰኑት ከትላንት ጀምሮ እንዲታሸጉ ተደርገዋል። የእርምጃው ሰለባ የሆኑት በይፋ ከሚታወቁባቸው አገልግሎቶች ባሻገር የውጭ ሀገር ገንዘቦች ምንዛሬን በተደራቢነት የሚሰጡ ሱቆች ናቸው። በኢትዮጵያ ሆቴል እና ጋንዲ ሆስፒታል አካባቢ የሚገኙት እነዚህ ሱቆች “ታሽጓል” የሚል ጽሁፍ እና ማህተም የሰፈረባቸው ወረቀቶች በየበሮቻቸው ላይ መለጠፋቸውን ዛሬ ረፋዱን በቦታው የተገኘው የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዘጋቢ ተመልክቷል። በሱቆቹ አካባቢ የአዲስ አበባ ፖሊስ የደንብ ልብስ … [Read more...] about “በጥቁር ገበያ” ምንዛሪ የተጠረጠሩ ሱቆች ታሸጉ
ጭንቅላቱ የደረቀው ህወሓት ኪሱም ሊደርቅ ነው
የብር ኖቶች መቀየር በህወሓት ሠፈር መደናገጥ ፈጥሯል ኢትዮጵያ በአዳዲስ የብር ኖቶች እንደምትጠቀም ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ይፋ ካደረጉ በኋላ መቀሌ የመሸገው ህወሓት ችግር ውስጥ መግባቱ ተሰምቷል። አዳዲሶቹ ብሮች ሙስናን እና የኮንትሮባንድን ንግድ መቀልበስ ዓላማው ማድረጉ ተነግሯል። ላለፉት ሁለት ዓመታት መቀሌ መሽጎ የሚገኘው ህወሓት የተባለው የበረኻ ወንበዴዎች ስብስብ ላለፉት እጅግ በርካታ ዓመታት ኢትዮጵያን ያለገደብ ሲዘርፍ የነበረ ቡድን መሆኑን ራሱም የሚመሰክረው ሐቅ ነው። ከሁለት ዓመት ተኩል በፊት ከምኒልክ ቤተመንግሥት ከተባረረ ወዲህ መቀሌ በየሆቴሉ መሽጎ የሽብር ተግባራትን ሲፈጽም ቆይቷል። ይህንንም ተግባሩን ለማስፈጸም እንዲረዳው በሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር፤ ሐሰተኛ የብር ኖቶች በማተም ተግባር፤ በኮንትሮባንድ ንግድ፤ ገንዘብ ከአገር በማሸሽ፤ ወዘተ ሕገወጥ ተግባራት … [Read more...] about ጭንቅላቱ የደረቀው ህወሓት ኪሱም ሊደርቅ ነው