በሕገ-ወጥ መንገድ ገንዘብ ያዘዋወረ፣ በዝውውሩ የተሳተፈና ለአዘዋዋሪዎች ሽፋን የሰጠ 10 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራትና የገንዘብ ቅጣት እንደሚጠብቀው የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አስታወቀ።
ባለፉት ሁለት ዓመታት በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በሕግ አስከባሪ አካላት ቁጥጥር ስር እየዋለ መሆኑ በአገሪቱ በሕገ-ወጥ መንገድ የሚዘዋወር ገንዘብ የመኖሩ አንድ ማሳያ ነው።
በመሆኑም በዚሁ የሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ተግባር ላይ ተሳታፊ የሆነ ማንኛውም አካል በወንጀል ሕግ ከመጠየቅ እንደማይድንም ጠቅላይ አቃቤ ግህ ጠቁሟል።
በኢትዮጵያ በ1996 ዓም በወጣው የወንጀል ሕግ መሰረት በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ውስጥ ተሳትፎ የተገኝ ማንኛውም አካል እስከ 10 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply