ኢትዮጵያችን ታማለች። ኢትዮጵያችን ተወጣጥራለች። ኢትዮጵያችን በአደገኛ መርዝ ተበክላለች። ኢትዮጵያችን ውስጧ ነፍሯል። ኢትዮጵያችን እየቃተተች ነው። ቆዳዋ ሳስቷል። የሚሰማትና የሚደርስላት ስላጣች የያዘችውን ይዛ ልትነጉድ ከጫፍ ላይ ነች። እናም ቅድሚያ ለመቀመጫ፤ ቅድሚያ ለእምዬ ኢትዮጵያ!! ማጣፊያው ሳያጥር ሁሉም መንገዱን ይመርምር!! ኢትዮጵያ በጭንቀት ጣር ውስጥ ስለመገኘቷ ማብራሪያ የሚጠይቁ ዜጎች ያሉ አይመስለንም። ምናልባት ሳያውቁ እየተፈረደባቸው ያሉ ህጻናት ካልሆኑ በስተቀር፤ ችግር ፈጣሪውም፣ የችግሩ ሁሉ ሰላባ የሆነው ህዝብ፤ ሁሉም ከበቂ በላይ መረጃ አላቸው። ኢትዮጵያ ህመሟ ወደ "ሚድን ካንሰርነት" መቀየር የሚችል ስለመሆኑ ዜጎች ያለ "ሰበር ዜና" ይረዱታል። የሚድን ስንል በቀላል አገላለጽ ችግር ፈጣሪው ኢህአዴግ፣ የኢህአዴግ ሾፌር ህወሃት፣ የህወሃት አገልጋዮች፣ … [Read more...] about የሚፈራው መጣ!!
Left Column
ግመል ሰርቆ ማጎንበስ አይቻልም
የአሜሪካ የውጭ ዕርዳታ ድረገጽ መረጃ እንደሚለው ከሆነ ከሰሃራ በታች ከሚገኙ አገራት መካከል የአሜሪካንን ዕርዳታ በመቀበል ቀዳሚነቱን ሥፍራ የያዘችው ኢትዮጵያ ነች፡፡ (http://www.foreignassistance.gov/) የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ ወይም በጀት ከተደረገው ውጪ የሚሰጠውን ተጨማሪ ዕርዳታና ድጎማ ሳይጨምር ከ2009 - እስከ 2012 ባሉት ዓመታት ብቻ ኢትዮጵያ ከ3.3ቢሊዮን ዶላር በላይ (በወቅቱ ምንዛሪ ከ60ቢሊዮን ብር በላይ) ዕርዳታ ተቀብላለች፡፡ ገንዘቡ የሚሠጠው ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ፤ ለዴሞክራሲ፣ ሰብዓዊ መብቶችና መልካም አስተዳደር፤ ለጤና፤ ለትምህርትና ማኅበራዊ አገልግሎቶች፤ ለኢኮኖሚ ልማትና ለአካባቢ ጥበቃ እንደሆነ ድረገጹ ያስረዳል፡፡ (በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የተቀናበረ - AP Photo/Steve Parsons/pool) … [Read more...] about ግመል ሰርቆ ማጎንበስ አይቻልም
በህዝብ አቆጣጠር አሁን ጨዋታው ተጀመረ!
ሙስናው ላይ የተጀመረው ዘመቻ ሙስናን በስንጥር የሚያሰኝ ቢሆንም አቶ መለስ ያልደፈሩትን ሰፈር አቶ ሃይለማርያም ነክተውታልና በኢህአዴግ ታሪክ የሙስናን ሰፈር በማንኳኳት ግንባር ቀደሙ ሰው ያደርጋቸዋል። እኛም ጅምሩ መልካም ነው እንላለን። ግን ጥያቄም ማሳሰቢያም አለን። ለማንኛውም በህዝብ አቆጣጠር አሁን ጨዋታው የተጀመረ ይመስለናል። በሙስና የተጠረጠሩ ነጋዴዎች፣ ደላሎች፣ አቀባባይ የተባሉና የመንግስት ሃላፊዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ከተሰማ ጀምሮ ህዝብ በስፋት እየተቸ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ የተደላደለውን ሙስና ህዝብ ጠንቅቆ ከነባለቤቶቹ ያውቃል። ይረዳል። ያሸታል። ባለፈ ባገደመ ቁጥር ለድህነቱ ማስታገሻ ያላምጣቸዋል። ሙስና ሲባል ሙስና ነው። ወንጀል ሲባል ወንጀል ነው። ህግ መተላለፍ ያስጠይቃል። አሁን እንደሚታየው ግን የጸረ ሙስናው ዘመቻ ሰፈር የለየ ይመስላል። ዋናዎቹ … [Read more...] about በህዝብ አቆጣጠር አሁን ጨዋታው ተጀመረ!
“መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ…”
ይህንን ቃለምልልስ ያደረግነው ለበርካታ ዓመታት ለኢህአዴግ ሲሰራ ከነበረና በአሁኑ ወቅት ለከፍተኛ ትምህርት ውጪ አገር ከሚገኝ ኢትዮጵያዊ ጋር ነው፡፡ ለደኅንነት ሲባል ስሙን ከመጥቀስ ተቆጥበናል፡፡ ጎልጉል ፦ የጠ/ሚኒስትር መለስ መታመም ድንገተኛ ነው የሚሉ አሉ፤ አሟሟታቸውም ድንገት ነው የሚሉ አሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ አጋጣሚው መልካም እንደሆነ የሚጠቁሙ አሉ አንተ ከየትኛው ወገን ነህ? መልስ፦ ቅድሚያ አቶ መለስ ድንገት አልታመሙም። በሽታቸው የቆየ እንደሆነ ይታወቃል። ምስጢርም አይደለም። ለዚሁ እኮ ነው ቤተ መንግስት ውስጥ በአዋጅ የተፈቀደላቸውን ቤት አሰርተው በቅርብ ርቀት እየተቆጣጠሩ ለመኖር ቅድመ ዝግጅት ሲያደርጉ የነበረው። በዚህ ቢስተካከል ለማለት ነው። መለስ ለኢህአዴግ አጋር ድርጅቶች ሁሉ የጋራ ነጠብ ናቸው። በድልድይም ይመሰላሉ። በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች፣ በተለይም … [Read more...] about “መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ…”
ደፋርና ጭስ መውጫ አያጣም! (ክፍል አንድ – ስድስት)
ስድስት:- ቃል ኪዳን፤ ደፋርና ጭስ መውጫ አያጣም! የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቪዢንና ራድዮ እንግዲህ ኢሳት በነገረኛነትም ሆነ በጠመንጃ-ያዥነት በኩል ከሎሌነት ጠባይ ጋር የተያያዘውን ኢትዮጵያውያን ያለንን አጉል ባህል ሁሉ እየነቀስን እየጣልን በዘመናዊና ሳይንሳዊ አስተሳሰብ መሠረት ለመጣል ዋና መሣሪያ ሊሆነን ይችላል ብሎ ማመን መነሻ ይሆናል፤ ይህ እምነት ከሌለ የእምቧይ ካብ ነው፤ ይህ እምነት ራስን ማጽዳትንም ይጠይቃል። ማክሸፍ እንደምንችልበት ከማመን እንጀምር፤ ስለዚህም ኢሳት ሊከሽፍ የሚችልበትን እያንዳንዱን መንገድ ማጥናትና በቅድሚያ ፈውሱን ማዘጋጀት የሚጠቅም ይመስለኛል፤ ይህንን ጉዳይ በትጋት ለመከታተል የኢሳትን አማራጭ የማይገኝለት የአገር ጥቅም በእውነትና በትክክል መገንዘብ ያሻል፤ ዘመን-አመጣሽ ነገር ብቻ አድርጎ መመልከቱ ለወረት ይዳርገዋል፤ ወረትን ማክሸፍ ቀላል … [Read more...] about ደፋርና ጭስ መውጫ አያጣም! (ክፍል አንድ – ስድስት)
ስለ አባይ ግድብ “አድርባይ” እንሁን?
ሰሞኑን ኢህአዴግ ጉባኤውን ሲጨርስ “አድርባይነት አሰጋኝ” ብሎናል። አባላቶቼ አድርባይ ሆነዋልና በዚህ ከቀጠልኩ እሰምጣለሁ የሚል ስጋት እንዳለበትም አስታውቆናል። ከፍርሃቻው ብዛት የተነሳ አድርባይነትን ለመዋጋትና “መድረክ ላይ ለመጥለፍ” በቁርጠኛነት እንታገላለን ብለው አቋማቸውን ነግረውናል። የሚገርመው ግን አድርባይነትን የፈጠረና ያነገሰው ራሱ ኢህአዴግ መሆኑን መዘንጋቱ ነው። ኢህአዴግ አድርባይ ሚዲያዎች አሉት። አድርባይ ባለሃብቶች አሉት። ኢህአዴግ አድርባይ የኔቢጤዎች አሉት። ኢህአዴግ አድርባይና የማደናገሪያ ፕሮጀክቶች አሉት። ኢህአዴግ አድርባይ ድርጅቶች እንጂ ነጻ ድርጅቶች የሉትም። ኢህአዴግ አድርባይ ባለስልጣናት እንጂ ነጻ አመራሮች የሉትም። ሁሉም አድርባዮች ተጠሪነታቸው ለህወሃት ስለሆነ ተጠያቂውም ራሱ የኢህአዴግ ሾፌር ህወሃት እንጂ ሌሎች ሊሆኑ አይገባም። “ፈጣሪያቸው” … [Read more...] about ስለ አባይ ግድብ “አድርባይ” እንሁን?
ዕውን ኢትዮጵያን የሚመሯት ኢትዮጵያውያን ናቸው?
የኢትዮጵያ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽ ኮሚቴና ባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር በመሆን ያዘጋጁት ሰላማዊ ሰልፍ አላማ ለፋሺስቱና ለጦር ወንጀለኛው ግራዚያኒ በጣሊያን ሀገር የተገነባውን መናፈሻ ስፍራና ሀውልት ለመቃወም ነው፡፡ ይህ ግለሰብ ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈፀመውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ ታሪክ አይዘነጋውም፡፡ ግራዚያኒ በመርዝ ጋዝ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ጨፍጭፏል፤ ከየካቲት 12 ጀምሮ ለቀናት በዘለቀው የበቀል ጭፍጨፋም በአካፋ ሳይቀር በአዲስ አበባና በአካባቢዋ ያሉ ኢትዮጵያውያንን በግፍ ጨፍጭፏል፡፡ ግራዚያኒ በወቅቱ በሰጠው ትዕዛዝ የፋሺስት ወታደሮች ህይወት ያለውን ተንቀሳቃሽ ፍጥረትን ሁሉ ገድለዋል፡፡ ይህ እሩቅ በማይባል ጊዜ የተፈፀመ ድርጊት ነው፡፡ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ለእንዲህ አይነቱ ጨፍጫፊ የተገነባን ሀውልት ለመቃወም በወጡ ዜጎች ላይ የወሰዱት … [Read more...] about ዕውን ኢትዮጵያን የሚመሯት ኢትዮጵያውያን ናቸው?
የትግራይ ህዝብ ስማ!!
ሰሞኑን በውዴታም ይሁን በግዴታ በመቀሌ እጅግ ከፍተኛ የሚባል ቁጥር ያላቸው የትግራይ ተወላጆች ሲጨፍሩ፣ ሲዘሉ፣ ከበሮ እየመቱ የባህላቸውን ዘፈንና ውዝዋዜ ሲያወርዱ አይተናል። ምክንያቱ በግልጽ ባይነገርም ሲደበቅ የነበረው የህወሃት ሃብትና ንብረት ውጤት የሆኑ፣ በልዩ የመንግስት ድጋፍ የተከናወኑ ግዙፍ ተቋሞች በጎዳና ለህዝብ ሲቀርቡም ተስተውሏል። ልማቱ መልካም ነው። ደስ ይለናል። ምንም ተቃውሞ የለንም። ግን መልዕክት አለን። ለማን? ምሬትን፣ ጭቆናና መንገፍገፍ ሲበዛ በፍቃደኛነት በቦንብ ላይ እንደሚያስሮጥ ለሚያውቀው የትግራይ ህዝብ!! የትግራይ ህዝብ ስማ!! ሰሞኑን ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ሪፖርት የትግራይ ክልል በትምህርት፣ በኤሌክትሪክ፣ በመንገድ፣ በእርሻ፣ በደን፣ በኢንዱስትሪ፣ በጤና፣ ወዘተ ከሌሎች ክልሎች ሁሉ ርቃ መሄዷን ይፋ አድርጓል። … [Read more...] about የትግራይ ህዝብ ስማ!!
ቤት መኖሩን እንመን፤ ከዚያ እንግባ!
በአውሮጳውያኑ አቆጣጠር በ1960ዎቹ በአሜሪካ የተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ጠንካራ ፉክክር የተደረገበት ነበር፡፡ ጆን ኤፍ ኬኔዲና ሪቻርድ ኒክሰን እጅግ ከፍተኛ ውድድር ካደረጉ በኋላ ኬኔዲ አሸነፉና ሥልጣኑን ተቆናጠጡ፤ ኒክሰን የሽንፈትን ጽዋ ጠጡ፡፡ ከኒክሰን ደጋፊዎች መካከል ቀዳሚ የነበረው የፊልም ተዋናይ ጆን ዌይን ነበር፡፡ የካው ቦይ ጫማውን አጥልቆ፤ ፈረሱ እየጋለበ፤ ሽጉጡ እያሽከረከረ፤ ጠላቶቹ በፊልም ይረፈርፍ የነበረው ጆን ዌይን ከሚከተለው የጸና የፖለቲካ አመለካከት አኳያ ሪቻርድ ኒክሰንን በመደገፍ ለማሸነፍ እንዲችሉ የተቻለውን እገዛ ያደረገ ነበር፡፡ ሆኖም ያሰበው አልተሳካም፤ የተመኘው መሪ ነጩ ቤተመንግሥት አልገባም፤ በሕገመንግሥቱ መሠረትም የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ አልሆነም፡፡ ጆን ዌይን ኬኔዲ ማሸነፋቸውን በተረዳ ጊዜ ግን አገር ወዳድነቱንና አርበኝነቱን … [Read more...] about ቤት መኖሩን እንመን፤ ከዚያ እንግባ!
ኢህአዴግ ሌላ፤ ኢትዮጵያችን ሌላ!!
ሚዲያ ከስሜታዊነት፣ ከስጋና ደም ድምር፣ ከችኩል ውሳኔና ግብታዊነት ነጻ ለመሆን ሌት ተቀን መስራት እንዳለበት ባለሙያዎች አበክረው የሚናገሩት ዓቢይ ጉዳይ ነው። ሚዲያ ስንል ደግሞ ሁሉንም ነው - የኅትመት፣ የምስል፣ የድምጽ፣ የድረገጽ፣ የዲጂታል፣ የማኅበራዊ ድረገጽ፣ … ። ሁሉም ሚዲያዎች አሻግሮ በማየት ህዝብንና አገርን የመጠበቅ ኃላፊነት አለባቸው። ጋዜጠኞች ወይም እንደ ጋዜጠኛ የሚሠሩ ሁሉ ከየትኛውም ሙያተኛ በላይ ሃላፊነት ሊሰማቸውም ግድ ነው። ለዚህም ነው በጋዜጠኝነት ሙያ "አመጣጥን፣ አሁንም አመጣጥን፣ አሁንም አመጣጥን … “ባላንስ” አድርግ" የሚባለው!! ከኢህአዴግ ዓይነ ያወጣ ውሸትና ዝግነት የተነሳ ሁሉንም መረጃዎች የማመጣጠኑ ሙያዊ ሃላፊነት ለመወጣት ፈተና ቢያጋጥምም በከፍተኛ ደረጃ ጥንቃቄ ልንወስድባቸው የሚገባን ጉዳዮች አሉ። ከነዚህ ጉዳዮች መካከል አንዱና ዋናው … [Read more...] about ኢህአዴግ ሌላ፤ ኢትዮጵያችን ሌላ!!