በሁመራ ከተማ በአንድ ሆቴል በተደረገ ፍተሻ ለሁለተኛ ጊዜ 37 ኩንታል አደንዛዥ እፅ ተገኘ። በከተማዋ ህግን የማስከበር ግዳጅ እየተወጡ የሚገኙ የአማራ ክልል ፖሊስ አባላት ህገወጥ ድርጊቶችን ለማስወገድ እና የህዝብን ሠላም ለማስጠበቅ እየሠሩ መሆኑን የከተማዋ ፖሊስ መምሪያ ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮማንደር ሙላት ማሞ ገልፀዋል። ከአደንዛዥ እፁ በተጨማሪ በአንድ ሰው ስም የተመዘገቡ 11 የቤት ካርታዎች እና በዚሁ ግለሠብ ስም ከፍተኛ ገንዘብ የተዘዋወረበት ቼክ ተገኝቷል። ከዚህ በተጨማሪም ገጀራዎች፣ መጥረቢያዎች እና ሌሎች መሳሪያዎች እንደተገኙ መናገራቸውን አብመድ ዘግቧል። ጎልጉል የድረጽ ጋዜጣ … [Read more...] about በሁመራ ለሁለተኛ ጊዜ 37 ኩንታል አደንዛዥ እፅ ተገኘ
Right Column
“ህወሓት ተሸንፏል፤ መሸነፉንም ማመን አለበት” ኬሪያ ኢብራሂም
ከተፈላጊ የህወሓት ጁንታ አባላት አንዷ የሆነችው ኬሪያ ኢብራሂም ለመንግስት እጅ ሰጥታለች። ኬሪያ ኢብራሂም በህውሓት ከፍተኛ አመራርነት፣ በመንግስት ከፍተኛ ሃላፊነት እንዲሁም በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤነት አገልግላለች። ኬሪያ ኢብራሂም የህወሓት ጁንታው ጥቅም ይሻለኛል ብላ ወደ መቀሌ የሸሸች ሲሆን ሾፌሯ ግን የመንግሥትን ንብረት ለጁንታው አልሰጥም ብሎ እሷን መቀሌ አድርሶ ንብረቱን በሙሉ ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ ይዞት መምጣቱ ይታወሳል። ከዚህም ጋር ተያይዞ በሰላማዊ መንገድ እንደ ኬሪያ ኢብራሂም ሌሎችም የህወሓት አመራሮች እጅ እንዲሰጡ መንግሥት ጥሪ አቅርቧል። እሷም የጦርነቱ አስፈላጊነት አልታየኝም፤ ህወሓት ተሸንፏል፤ መሸነፉንም ማመን አለበት በማለት ተናግራለች በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ በሰፊው ተነግሯል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about “ህወሓት ተሸንፏል፤ መሸነፉንም ማመን አለበት” ኬሪያ ኢብራሂም
አምስት ቢሊየን (የሱዳን) ፓውንድ በሱዳን ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረ የወንበዴው አባል ተያዘ
የሱዳን ወታደሮች በሱዳን ግዛት ውስጥ ሲንቀሳቀስ የነበረ ኢትዮጵያዊ የሚሊሻ መሪ በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አስታወቁ። የሚሊሻ መሪ ነው የተባለው ግለሰብ በሱዳን ክልል ውስጥ ከህወሓት ወገን ሆኖ ሲዋጋ የነበረ መሆኑንም ሱዳን ትሪቢዩን ታማኝ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል። ማንነቱ ያልተጠቀሰው ግለሰብ ከቤተሰቦቹ እና በርካታ ቁጥር ካላቸው ወታደሮችና አጃቢዎች ጋር በገዳሪፍ ግዛት አልፋሻቃ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋሉም ነው የተገለጸው። በወቅቱም አምስት ቢሊየን ፓውንድ (የሱዳን ይሁን የእንግሊዝ ያልተጠቀሰ)፣ መጠኑ ያልተገለጸ ወርቅ፣ የእንጨት ስራ ውጤቶች እና ሁለት ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ጋር መያዙም ተገልጿል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about አምስት ቢሊየን (የሱዳን) ፓውንድ በሱዳን ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረ የወንበዴው አባል ተያዘ
በማይካድራ 18 ሰው በጉድጓድ ተጥሎ፤ 57 ደግሞ በጎርፍ ማፋሰሻ ቦይ ተገድለው ተገኙ
ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም በንጹኃን የአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ ዘርን መሠረት ያደረገ ጥቃት በማይካድራ ከተማ መፈፀሙ ይታወቃል። ይህን አስነዋሪ ተግባር የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በቦታው በመገኘት ባደረገው ጥናት እና ይፋ ባደረገው መረጃ የሟቾች ቁጥር በትንሹ 600 እንደሆነ ገልጾ ነበር። ግድያውም ዘርን መሠረት ያደረገና በተለይም የአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ጅምላ ጭፍጨፋ መሆኑን ገልጿል። ይሁን እንጂ የሟቾች ቁጥር በትንሹ 600 ነው ተብሎ የተገለጸው በማይካድራ ከተማ በየቤቱ ህይወታቸው አልፎ የተገኙ እና በቤተክርስቲያን ውስጥ የተቀበሩትን ብቻ መሠረት ያደረገ ነው። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጥናት አድርጎ ከተመለሠ በኃላ ከማይካድራ ከተማ ወጣ ባሉ የገጠር አካባቢዎች በርካታ የጅምላ መቃብሮች መገኘታቸውን የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ጋዜጠኞች በቦታው … [Read more...] about በማይካድራ 18 ሰው በጉድጓድ ተጥሎ፤ 57 ደግሞ በጎርፍ ማፋሰሻ ቦይ ተገድለው ተገኙ
በጎንደር ከተማ የሽብር ተግባር ለመፈፀም በዝግጅት ላይ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ
በጎንደር ከተማ የሽብር ተግባር ለመፈፀም በዝግጅት ላይ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለፀ። የከተማው ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ኮማንደር አየልኝ ታክሎ፤ የከተማው ፖሊስ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት ጋር ባደረጉት ክትትል ተጠርጣሪው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዋል። ግለሰቡ ለሽብር ተግባር ለመጠቀም ካዘጋጃቸው 35 ተቀጣጣይ ቁሳቁስ፣ 216 ማሰልጠኛ ማንዋል፣ ሶስት የተለያዩ ባንኮች ደብተር፣ 20 ገንዘብ ገቢና ወጪ ደረሰኝ እና ከአንድ ላፕቶፕ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉንም ተናግረዋል። በግለሰቡና በግብረ አበሮቹ ላይ የሚደረገው ምርመራ እንደቀጠለ መሆኑን የገለፁት ኮማንደር አየልኝ ስለጉዳዩ ዝርዝር መረጃ እንደሚሰጥም ጠቅሰዋል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about በጎንደር ከተማ የሽብር ተግባር ለመፈፀም በዝግጅት ላይ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ
ባለፉት 2ተኩል ዓመታት ትህነግ ስፖንሰር ያደረጋቸው ግጭቶች
ሰኞ ዕለት በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ትንታኔ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “መንግሥት ሥራ እንዳይሠራ በተቀናጀ መልኩ በየቦታው ሽብር ይፈጠርለት ነበር” በማለት ትህነግ/ህወሓት ስፖንሰር ያደረጋቸው 113 ግጭቶች እንደነበሩ ገልጸዋል - ዝርዝራቸውን በዚህ መልኩ ነበር ያቀረቡት በኦሮሚያ ውስጥ ብቻ 37 ግጭቶች ነበሩ፤በአማራ ክልል 23 ግጭቶች ነበሩ፤በቤባሻንጉል ጉሙዝ 15 ግጭቶች ነበሩ፤በአዲስ አባበ 14 ግጭቶች ነበሩ፤በደቡብ፣ በጋምቤላና በተቀሩት የአገሪቷ ክልሎች ግጭቶች ነበሩ፤በሁሉም ክልሎች ችግሮች አሉ፤ ትግራይ ብቻ ነው ሰላም የነበረው፤እነሱም አያፍሩም እኛ ብቻ ነን ሰላም ይሉ ነበር፤ ዋናው የችግሩ ባለቤቶች እነሱም ነበሩ፤አሠራራቸው ተራ አልነበረም፤ ገንዘብ፣ ስልጠና ስምሪት ሚዲያም ነበራቸው፤ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ባለፉት 2ተኩል ዓመታት ትህነግ ስፖንሰር ያደረጋቸው ግጭቶች
ሁለት ሻንጣ ሙሉ ብር ተያዘ
ሁለት ሻንጣ ሙሉ ብር ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዋሉ። ዋና ሳጅን ታከለ እሸቴ ይባላል የምዕራብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ባልደረባ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ደግሞ በሁመራ ከተማ ሰላም እያስከበረ ይገኛል። በቀን 19/03/2013 ዓ.ም ሰላም እያስከበረ በሚገኝበት ሁመራ ከተማ ላይ በአንድ በባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) ላይ ሁለት ግለሰቦች ሁለት ሻንጣ ይዘው በመጓዝ ላይ ሳሉ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አኳያ ፍተሻ በሚያደርግበት ጊዜ ሁለቱም ሻንጣ ሙሉ ብር ሆኖ ተገኝቷል። በወቅቱ ግለሰቦች አንዱን ሻንጣ ሙሉ ብር እንስጥህና ልቀቀን ቢሉትም ቃል የገባለትን ህዝብ እና ሙያውን በማስበለጥ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል። በአሁኑ ሰዓት በሁለቱም ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል። (ምንጭ፤ አማራ ፖሊስ) ጎልጉል የድገጽ … [Read more...] about ሁለት ሻንጣ ሙሉ ብር ተያዘ
በጋምቤላ ክልል ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ይዘው ለማምለጥ በሞከሩ አዘዋዋሪዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ
በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች ከጸጥታ አካላት ለማምለጥ ባደረጉት የተኩስ ልውውጥ እርምጃ እንደተወሰደባቸው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ኮማንደር ኡማን ኡጋላ ለኢዜአ እንዳሉት እርምጃው የተወሰደው ግለሰቦቹ ትናንት ምሽት አራት ስዓት ላይ ከኑዌር ዞን ወደ ኢታንግ ልዩ ወረዳ ጦር መሳሪያዎችን በሸክም ለማስገባት ሲሞከሩ ነው። እነሱን ለመያዝ በተደረገው የተኩስ ልውውጥም ሁለት ጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች መሞታቸውንና አንዱ ደግሞ ቆስሎ መያዙን ተናግረዋል። በግለሰቦቹ እጅ የነበሩት 19 ታጣፊና ዘጠኝ ባለሰደፍ በድምሩ 28 የክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል። ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች በእጃቸው ይዘዋቸው የነበሩትን ሌሎች መሳሪያዎች እየተታኩሱ ይዘው ማምለጣቸውን ጠቁመው "እነሱን … [Read more...] about በጋምቤላ ክልል ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ይዘው ለማምለጥ በሞከሩ አዘዋዋሪዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ
ዐቃቤ ሕግ በ167 የህወሃት ሰዎች ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣቱን አስታወቀ
በትግራይ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር በተያያዘ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በ167 ሰዎች ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣቱን ይፋ አደረገ። ይህ የተባለው የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ትናንት በጋራ በሰጡት መግለጫ ነው። ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ በመግለጫው ላይ በህውሓት ኃይሎች የተፈጸሙት ተግባራት በአገሪቱ የወንጀል ሕግ አንጻር በከፍተኛ ወንጀል የሚያስጠይቁ ናቸው ብለዋል። በአገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የተፈጸመው ጥቃት 'የመንግሥትን አገሪቱን የመከላከል ኃይል ለማዳከም' በተፈጸመ ወንጀል በሚል የሚያስጠይቅ መሆኑን ጠቁመዋል። በባሕር ዳር እና ጎንደር ከተሞች ላይ የተፈጸሙትን የሮኬት ጥቃቶች በተመለከተም፤ ድርጊቱ በሽብር ወንጀል … [Read more...] about ዐቃቤ ሕግ በ167 የህወሃት ሰዎች ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣቱን አስታወቀ
የትግራይ ክልል መዋቅር ዳግም ይደራጃል
የትግራይ ጊዜአዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሙሉ ነጋ በጊዜአዊ አስተዳደሩ የሚሰሩ ስራዎችን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል። ዶ/ር ሙሉ በመግለጫቸው የትግራይ ክልል መዋቅር ዳግም እንደሚደራጅ ተናግረዋል። የክልሉ ካቢኔና የዞን አስተዳደርም እንደአዲስ እንደሚዋቀርም የተናገሩት ዶ/ር ሙሉ የወረዳና የቀበሌ ምክር ቤቶች እንዳሉ ይቀጥላሉ ብለዋል። መንግስት የጀመረውን የህግ ማስከበር እርምጃ እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ይሰራልም ብለዋል። ከፅንፈኛው ህወሓት ቡድን ነፃ የወጡ አካባቢዎች ላይ መዋቅሮችን በመዘርጋት ህዝቡ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴው እንዲመለስ እንደሚሰራም ተናግረዋል። የህወሓት ፅንፈኛ ቡድን ላለፉት ሁለት ዓመታት ተኩል በክልሉ ምንም አይነት የልማት ስራ አልተሰራም ያሉት ዶክተር ሙሉ ህግ የማስከበሩ ስራ … [Read more...] about የትግራይ ክልል መዋቅር ዳግም ይደራጃል