ሰኞ የሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ከተጠናቀቀ በኋላ ኢህአፓ እንደሚሰነጠቅ ተነገረ። አሁን ላይ ፓርቲው በተለይ አመራሩ ኹለት ሊባል በሚችል ጎራ ተከፋፍሎ ውስጥ ለውስጥ እየተናቆረ እንደሆነ ተገልጿል። ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ከተጠናቀቀ በኋላ ለምርጫ በጥምረት ስም የገባው ኢህአፓ እንደሚሰነጠቅ ለጎልጉል የደረሰው መረጃ ይጠቁማል። በተለይ በአመራር ደረጃ ያለው መለያየትና መከፋፈል ፓርቲውን ለመሰንጠቅ አደጋ እንዳበቃው ከመረጃው ለመረዳት ተችሏል። የፓርቲው መሪ አቶ አብርሃም ሃይማኖትም የክፍፍሉን ኹኔታ በሚዲያ ቀርበው የተናገሩ ሲሆን በተለይ በአመራሩ መካከል ከምርጫ ጋር በተያያዘ የተከሰተው አለመግባባት የከረረና እርሳቸውንም ከኃላፊነት እንዲወጡ እያስገደዳቸው መኾኑን ተናግረዋል። አንከር ከተባለ ዩትዩብ ጋር የተነጋገሩት አቶ አብርሃም በርካታ የፓርቲውን ምሥጢሮች ይፋ … [Read more...] about “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል”
Archives for May 2026
ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ
የፌዴራል ፖሊስ በሪፖርተር ላይ ያወጣው መግለጫ የሪፖርተርንና የባለቤቱን ማንነት እንዲሁም ስሑት ሥራውን ያጋለጠ ነው። እንደ ፌዴራል ፖሊስ መግለጫ ሪፖርተር “ስውር ተልዕኮ የተንፀባረቀበት ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ፈፅሟል”። የመግለጫው ሙሉ ቃል ከዚህ በታች ይገኛል። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሪፖርተር ጋዜጣ “ከፍተኛ ባለስልጣናትና ታዋቂ አርቲስቶች ከ98 ቢሊየን ብር በላይ መዝረፋቸው በኦዲት ምርመራ መረጋገጡ ተነገረ" በሚል የዘገበው መረጃ የተዛባ መሆኑን አስታወቀ ሪፖርተር ጋዜጣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም የዘጠኝ ወር የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ለተከበረው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና የፍትህ ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት ሪፖርቱን ለማስረዳት በማስታወሻነት የተጠቀመበትን ጥቅል መረጃ መነሻ በማድረግ፣ ጠቅላላ ይዘቱን በአግባቡ … [Read more...] about ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ


