* በሶስት ወራት ብቻ ከ6,600 በላይ ወጣቶች በህገ-ወጥ መንገድ ተሰድዋል" - የትግራይ የወጣቶች ጉዳይ ቢሮ በትግራይ ክልል ከተሞች በሚገኙ አውራ መንገዶች "ልጄ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ስደት ሲሄድ በአጋቾች ተይዞ ይህንን ብር ክፈል፣ ካልከፈልክ ትገደላለህ ብለውኛል እርዱኝ" የሚሉ በትልቅ ባነር በተቀመጠ የወጣቶች ፎቶ አስደግፈው እርዳታ የሚለሙኑ ወላጆች ተበራክተዋል። ከነዚሁ ወላጆች የአክሱም ከተማ ነዋሪዋ ወ/ሮ ኣስካለ ውብኣንተ አንድዋ ሲሆኑ፤ ይጦረኛል ብለው ኮስኩሰው አስተምረው ያሳደጉት ወንድ ልጃቸው ህገ-ወጥ ስደት የነጠቃቸው እናት ናቸው። "ልጄ በጦርነቱ ማግስት በአከባቢው የስራ እድል በማጣቱ በህገ-ወጥ መንገድ የተለያዩ ሃገራት ደንበር አቋርጦ ሊብያ ሲደርስ ለሰው ህይወት ቁብ በሌላቸው ሽፍቶ እጅ ወድቆ ቁም ስቅሉን እያሳዩት ነው" ብለዋል። "አካል … [Read more...] about በትግራይ ከሞትና ከአካላዊ ጉዳት የተረፉት ለስደት ተዳርገዋል
Archives for November 2024
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አሠራሩን እንዲያርም ጥብቅ መመሪያ ተሰጠው
* ኃላፊዋ በዕለቱ አለመገኘታቸው “ለወደፊቱ እንዳይደገም” ማሳሰቢያ ተሰጣቸው በዛሬው ዕለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የ2015 /2016 በጀት አመት የፓስፖርት አገልግሎት አሰጣጥና ውጤታማነትን በተመለከተ የተከናወነ የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት እንዲሁም የ2015 የሂሳብ ኦዲት ሪፖርት ላይ ለመወያየት ስብሰባ ጠርቶ ነበር። ነገር ግን የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ስብሰባው ላይ ሳይገኙ መቅረታቸው ቁጣን ፈጥሯል። የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የሺእመቤት ደምሴ (ዶ/ር) ምን አሉ? "በመሰረቱ ምክር ቤቱ ተመርምረው የቀረቡለትን የዋና ኦዲት ሪፖርቶችን ይፋዊ ውይይት የሚያደርግባቸው የመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ነው። “እኔ የመጣችሁትን የተመርማሪ … [Read more...] about የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አሠራሩን እንዲያርም ጥብቅ መመሪያ ተሰጠው
ደም ጠጥቶ “አልጸጸትም” – የጃዋር አዲስ መጽሐፍ
ራሱን ከሚገባው በላይ መካብ የማይበቃው ጃዋር ሲራጅ መሐመድ የ21ኛው ክፍለ ዘመን አህመድ ግራኝ ነኝ፤ ተጽዕኖ ፈጣሪ ነኝ፤ “የአማራ ብሔርተኝነት ማነሳሳታችን ትልቁ ስኬታችን ነው”፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለሥልጣን ያበቃሁት እኔ ነኝ፤ የምርጫውን ቀመር (ካልኩሌሽን ሠርቼዋለሁ)፣ ቁርአን ይዤ ዐቢይን ጅማ ላይ እንዳይመረጥ አደርገዋለሁ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት መንግሥት ነው ያለው - የዐቢይ እና የቄሮ መንግሥት፣ እኔ ከታሰርሁ ኦሮሚያ ድብልቅልቁ ነው የሚወጣው፣ የፖለቲካ ሳይንቲስት ነኝ፣ ብዙ ዕውቀት አለኝ፤ ብዙ ችሎታ አለኝ፤ ወዘተ በማለት ያለማቋረጥ ከመትፋት አልፎ “ተከበብኩኝ፤ ልገደል ነው” የሚል የሃሰት መረጃ በማውጣት፤ ከህወሓት ጋር በመመሳጠር ለመተግበር የሞከረውን ዕቅድ እንደፈለገ የሚነዳውንና ማሰብ የተሳነውን የቄሮ ኃይል በመጠቀም ለማስፈጸም ባደረገው ሙከራ እጅግ በርካቶች በግፍ … [Read more...] about ደም ጠጥቶ “አልጸጸትም” – የጃዋር አዲስ መጽሐፍ