* ኃላፊዋ በዕለቱ አለመገኘታቸው “ለወደፊቱ እንዳይደገም” ማሳሰቢያ ተሰጣቸው በዛሬው ዕለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የ2015 /2016 በጀት አመት የፓስፖርት አገልግሎት አሰጣጥና ውጤታማነትን በተመለከተ የተከናወነ የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት እንዲሁም የ2015 የሂሳብ ኦዲት ሪፖርት ላይ ለመወያየት ስብሰባ ጠርቶ ነበር። ነገር ግን የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ስብሰባው ላይ ሳይገኙ መቅረታቸው ቁጣን ፈጥሯል። የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የሺእመቤት ደምሴ (ዶ/ር) ምን አሉ? "በመሰረቱ ምክር ቤቱ ተመርምረው የቀረቡለትን የዋና ኦዲት ሪፖርቶችን ይፋዊ ውይይት የሚያደርግባቸው የመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ነው። “እኔ የመጣችሁትን የተመርማሪ … [Read more...] about የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አሠራሩን እንዲያርም ጥብቅ መመሪያ ተሰጠው