አሸባሪው ትህነግ ትጥቅ ይፍታ ተብሏል። አባላቱና ደጋፊዎቹ ትጥቅ አንፈታም እያሉ ነው። እፈታለሁ ቢል እንኳን ትህነግ ትጥቅ ዘርፎ ሲደብቅ የኖረ ድርጅት ነው። የትህነግ ዋናው ትጥቅ ግን የጦር መሳርያ አይደለም። የትህነግ የነፍስ መከፍ፣ የቡድን፣ ከባድ መሳርያው ፀረ አማራ ጥላቻ ነው። እስካሁን የፈፀመው ውድመት በፀረ አማራ ትርክት የተፈፀመ ነው። 1) አሸባሪው ትህነግ ተመስርቶ፣ የጎለመሰው በአማራ ጥላቻ ነው። በግላጭ አማራን የሚረግም ማንፌስቶ አርቅቆ፣ አባላቱን ብቻ ሳይሆን ህዝብን ወዝ የጠገበ ጥላቻ አስታጥቋል። ይህን ትጥቅ መፍታት አለበት። ይህ ትጥቅ የሚፈታው የአማራን ህዝብ ይቅርታ በመጠየቅ ነው። 2) የትህነግ ፀረ አማራ ጥላቻ ለአማራ ህዝብ ብቻ የተወሰነ አይደለም። ፀረ ኢትዮጵያም ነው። የኢትዮጵያ ታሪክን ከአማራ ጥላቻ ጋር አጋምዶ ኢትዮጵያን ቅኝ ገዥ አድርጓ … [Read more...] about የአማራ ሕዝብ በይፋ ይቅርታ ሊጠየቅ ይገባዋል!
Archives for November 2022
ከ300 ሺህ ዶላር በላይ ወደ ውጭ ሃገር ለማስወጣት የሞከረ አሽከርካሪ ተያዘ
በአዳማ ከተማ ከ300 ሺህ ዶላር በላይ ወደ ውጭ ሃገር ለማስወጣት የሞከረ አሽከርካሪ መያዙን የከተማዋ ፖሊስ መመሪያ አስታወቀ። አሽከርካሪው የተያዘው ኮድ 3/89158 ኢ.ት በሆነ ሎቤድ መኪና ገንዘቡን ከአዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ በስውር ደብቆ ሲያጓጉዝ ነው።በአዳማ ከተማ ዳቤ ክፍለ ከተማ ዳቤ ሶሎቄ ልዩ ቦታው ኬላ ፍተሻ ላይ የተያዘው የገንዘብ መጠንም 302ሺህ 400 የአሜሪካን ዶላር መሆኑን 2015የመመሪያው የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ምክትል እንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ገልጸዋል።በብሔራዊ ደህንነትና በአዳማ ከተማ የፀጥታ ሃይሎች ትብብር በ23/2/2015 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ላይ የተያዘው ይሄ ገንዘብ ወደ ውጭ ሃገር በሚጓዝ የኮንቴይነር ጭነት ስር በስውር ቦታ ተደብቆ መሆኑንና አሽከርካሪውም በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን ነው ያስረዱት። (Tikvah) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ከ300 ሺህ ዶላር በላይ ወደ ውጭ ሃገር ለማስወጣት የሞከረ አሽከርካሪ ተያዘ
ባለፉት ሦስት ወራት የተያዘ ህገ ወጥ ሲሚንቶና ነዳጅ
በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በህገ ወጥ መልኩ ሲዘዋወር የነበረ ከ71 ሺህ ኩንታል በላይ ሲሚንቶ እና 500,153 ሊትር ነዳጅ ተይዟል። በዚህም መሰረት፦- በአዲስ አበባ 54,976 ኩንታል ሲሚንቶ- በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት 14,094 ኩንታል ሲሚንቶ፣ እና 49,520 ሊትር ነዳጅ- በአማራ ክልላዊ መንግስት 1,914 ኩንታል እና 39,8505 ሊትር ነዳጅ- በሶማሌ ክልላዊ መንግስት 530 ኩንታል እና 12,560 ሊትር ነዳጅ- በደቡብ ምዕራብ 39,568 ሊትር ነዳጅ በድምሩ 71,514 ኩንታል ሲሚንቶ እና 500,153 ሊትር ነዳጅ በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር ተገኘቶ በህገ ወጥ አካላት ላይም አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡ በዚህ ህገ-ወጥ ድርጊት ላይ ተሳተፎ ባደረጉ አካላት ላይ ድርጅት የማሸግ እንዲሁም ምርት የመውረስ … [Read more...] about ባለፉት ሦስት ወራት የተያዘ ህገ ወጥ ሲሚንቶና ነዳጅ
ክብር ለጀግኖቻችን!
ትህነግ አሸንፎ ቢሆን ኖሮ … ድርድሩ የተደረገው ትህነግ ደብረብርሃንን፣ ባህርዳርን፣ ጎንደርን ይዞ ቢሆን ኖሮ ትጥቅ ይፍታ ይባል የነበረው ጥምር ጦሩ ነበር። ክብር ለጀግኖቻችን ይሁንና ድርድሩ የተደረገው ባለፈው አመት ምዕራባውያን ዲፕሎማቶቻቸውን ባስወጡበት ወቅት ቢሆን ኖሮ ጥምር ጦሩ ያለ እንቅፋት ወደ መቀሌ ይግባ ሳይሆን፣ ትህነግ ወደ አዲስ አበባ ይግባ ነበር የሚባለው። ክብር ለጀግኖቻችን ይሁንና፣ አምና ትህነግ እንደወረረን የባሰ ገፍቶ ቢሆን ኖሮ የጊዜያዊ አስተዳዳሪ መዳቢው ትህነግ ነበር። ያውም እንደህዝብ እንድንኖር ከፈቀደልን። ክብር ለጀግኖቻችን ይሁንና እንደ ጠላቶቻችን ቢሆን ኖሮ የትህነግ ጀኔራሎች ነበሩ ትጥቅ አስፈችዎች። ክብር ለጀግኖቻችንና ወልዲያና፣ ላሊበላን፣ ጋሸናና ደባርቅን ይዘው አልተደራደሩም። ክብር ለጀግኖቻችን ይሁንና አላማጣ … [Read more...] about ክብር ለጀግኖቻችን!




