Following the publication of 'Soft Skills That Make or Break Your Success' book, the author has been interviewing successful professionals to share their take on soft skills. In this interview, Obang Metho, Executive Director of Solidarity Movement for New Ethiopia (www.solidaritymovement.org) shared which soft skills helped him the most, which soft skill he is working on, and the soft skills that are very vital to Ethiopians in the Diaspora. You can get the book, Soft Skills That Make or Break … [Read more...] about Interview with Obang Metho on Soft Skills
Archives for September 2017
የዘረኛው ህወሐት የምስረታ ሰነድ በቁጥር አንድ ጠላትነት ያስቀመጠው ህዝብ
ህወሐት በትግል ፕሮግራሙ የአማራን ያክል የሚጠላው ሌላ ህዝብም ሆነ አካል እንደሌለ በግልጽ ያስቀመጠ ድርጅት ነው። የአማራ ህዝብ መሬት እያረሰ የሚኖር ደሀ ህዝብ ቢሆንም በህወሐት የምስረታ ሰነዶች እንደ ገዥ ብሄር ተፈርጆአል። አስገራሚው ነገር አማራ ንጉሱንም ሆነ ደርግን በማስወገድ ትግል ከሌሎች ህዝቦች እኩል ድርሻ የነበረው ህዝብ ነው። እንደ ህዝብ በህወሐት የሚጠላው በተጨበጠ ምክንያት አይደለም። ህወሐት የአማራን በሌሎች እንዲጠላ ካደረገባቸው የተደራጁ ስብከቶች በተጨማሪ የብሄረሰቡን ማንነት የሚያዳክምባቸው ልዩ ልዩ እርምጃዎችንም ወስዶአል። አንዱ ሴቶች ፍላጎታቸው ሳይጠየቅ የረጅም ግዜ የወሊድ መከላከያ መርፌ እንዲወጉ ማድረጉ ነው። በዚህም እኤአ 2007 የህዝብ ቆጠራ የህዝብ ቁጥሩ ከሚጠበቀው በ3 ሚሊዮን የቀነሰ ብቸኛ ህዝብ ሆኖአል። ሌላው በትግራይ ክልል የልዩ … [Read more...] about የዘረኛው ህወሐት የምስረታ ሰነድ በቁጥር አንድ ጠላትነት ያስቀመጠው ህዝብ
ሐተታና ግምገማ፤ የማለዳ ድባብ [የአዳዲስ ግጥሞች መድብል]
የማለዳ ድባብ [የአዳዲስ ግጥሞች መድብል]፤ 2009ዓ.ም፤ አ/አ፤ አታሚ አልተገለጸም፤ 10ዶላር፣ 100 ገጽ የማለዳ ድባብ፣ ለ በዕውቀቱ ሥዩም አራተኛ የግጥም ሥራው ነው። መጽሐፉ ሦስት ክፍሎች አሉት፤ “ግጥምና የዘመን መንፈስ” [ገጽ 5-9]። ግጥሞች [ገጽ 17-91]። “ጉደኛ ስንኞች” እና “ሙሾና ባለቅኔ” [ገጽ 93-100]። መድብሉ፣ ቀድሞ ካስነበባቸው ላይ አዳዲሶች ተጨምረውበት የተዘጋጀ ነው [ገጽ 9]። የትኞቹ አዳዲሶች እንደሆኑ አልተገለጸም። ግጥም ከስድ ንባብ ይልቅ የግል እይታዎችን፣ ማህበራዊ ትረካዎችን ለመቋጠርና ለማስታወስ ይረዳል። ቅኝቱና አወራረዱ ለጆሮና ለዐይን ይጥማል። ግጥም ማህበራዊ እሴት አለው፤ በሥልጣን ለሚባልጉ እርምት ለመስጠት [“ይድረስ ለጥም ሚኒስትር”፣ ቁ.71]፣ የሕይወትን አጭርነት ለማሳሰብ፣ ከሚታየው ውጭ የላቀ ተስፋ እንዳለ ለማወጅ፣ የግለሰብ … [Read more...] about ሐተታና ግምገማ፤ የማለዳ ድባብ [የአዳዲስ ግጥሞች መድብል]
በዓለም ዙሪያ ለሚኖሩ የዐማራና የቅማንት ነገድ ተወላጆች የቀረበ ጥሪ!
ወደ ነበረው የአባቶቻችን ፍቅርና አብሮነት እንመልከት! የትግሬ-ወያኔ የሚያራምደው ዘርን መሠረት ያደረገ ፖለቲካ፣ የቋንቋ ልዩነት ያላቸውን ሰዎች ብቻ ሳይሆን፣ ከተለያዩ ነገዶች የተወለዱ እህታማቾች፣ ወንድማማቾች እና አንድ አካልና አምሳል የሆኑ ባልና ሚስቶችን እያለያየ እንደሆነ ባለፉት 26 ዓመታት የታዘብነው ጉዳይ ነው። ወያኔ ይህን ቋንቋን መሠረት ያደረገ የማለያየት ሥራ የሚሠራው ደግሞ፣ አንዳንድ የዋሆች እንደሚሉት ለነገዶችና ጎሣዎች ዕኩልነት አስቦ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያን የማፍረሻውና ለዘመናት ሲያልሙት የኖሩትን የትግራይ ረፐብሊክ ለመመሥረት አቋራጩና ቀላሉ መንገድ ይህ ሆኖ ስላገኙት ነው። «አባቶቻችን፣ ሁልህም ወደ ወገነህ ተጠጋ ቢባል፣ ዳዊት ወደ ቁርበት፣ አክንባሎ ወደ በረት ተጠጋ» ያሉት ኅይው ሆኖ፣ የተፋቀው፣ የለሰለሰው፣ በአያሌ ቀለሞች የተዋበው፣ ውብና መንፈሣዊ ሥዕሎች፣ … [Read more...] about በዓለም ዙሪያ ለሚኖሩ የዐማራና የቅማንት ነገድ ተወላጆች የቀረበ ጥሪ!
እምቢተኝነት በተግባር!
“ሕዝቡን ካፈንከው እና ከመቃወም ሌላ አማራጭ ካሳጣኸው ይፈነዳል፤ ወጣቱ በሙሉ ዓመጽ ላይ ነው፤ ትውልድ አምጿል”። የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጠኛ JEFFREY GETTLEMAN በኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ በተነተነበት ጽሁፍ ላይ ከተናገረው። ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። ዛሬ በተከበረው የመስቀል በዓል ላይ የህወሓትን ማስፈራሪያና ዛቻ ከምንም ባለመቁጠር የውቅሮ፣ ዓዲግራት፣ መቀሌ፣ ጎንደር፣ ደሴና ሌሎች አካባቢዎች ህዝብ “ባለኮከቡን ባንዲራ አይወክለኝም” በማለት ኮከብ አልባውን ሠንቀድ ዓላማ ይዞ በመውጣት እምቢተኝነቱን አድፍረት አሳይቷል። ሃይለኪሮስ ታፈረ (Hailekiros Tafere) በፌስቡክ ገጹ የዘገበውን አስመልክቶ አምዶን ገብረሥላሴ ይህንን ብሏል፤ “ፖሊስ "ኮከብ የሌለው ባንዴራ ዳሜራ ሸፍናቹሃል" በሚል ሰበብ ዛሬ መስቀል በዓል እያከበረ የነበረው የውቅሮ … [Read more...] about እምቢተኝነት በተግባር!
የህወሃት አጀንዳ + የዘር ፖለቲካ + የሜንጫ ፖለቲካ – መጨረሻው ተያይዞ …
የኢትዮጵያ ህወሓት ሰራሹ “ፌደራሊዝም” ወደ ተፈራው ቀውስ እየተንደረደረ መሆኑንን የሚያሳዩ የዜና ዘገባዎች የተሰሙት ገና ከጅምሩ ነበር። በርካታ ባለሙያዎችና የተቀናቃኝ ፖለቲካ መሪዎች በተደጋጋሚ ስጋታቸውን ቢገልጹም ተቀባይነት ሊያገኙ ባለመቻላቸው የጎሣና የብሄርተኛነት በሽታ እያደር ኢትዮጵያን እየበላት አሁን ያለችበት ደረጃ አድርሷታል። ችግሩ አለመስማትና አለማወቅ ብቻ ሳይሆን ዓላማ ያለው፣ በቅጥረኝነት አገሪቱን የማፈራረስ ተልዕኮ የማሳካት ጉዳይ በመሆኑ የመከሩ፣ የዘከሩ፣ ያስጠነቀቁ፣ ስጋታቸውን አደባባይ ያወጡ ዜጎች ወንድ ሴት ሳይባል ተፈጅተዋል። አገሪቱ ምትክ የሌላቸውን ልጆቿን እንድትከስር ተደርጋለች። ግድያውና አፈናው ብቻ ሳይሆን መላውን የአገሪቱን ህዝብ እርስ በእርስ ጎሣና ጎጥ ለይቶ እንዲናከስ እየተወተወተና እየተገፋ አገሪቱ ቆዳዋ በልጆቿ ደም እንዲለወስ ሆኗል። ዛሬ … [Read more...] about የህወሃት አጀንዳ + የዘር ፖለቲካ + የሜንጫ ፖለቲካ – መጨረሻው ተያይዞ …
ድንበር: “ድንበር ሲፈርስ፤ መሐሉ ዳር ይሆናል”
ስለኢትዮጵያ ድንበር መፍረስ፤ መገሰስና መጠገን በተደረጉበት ዘመናት ሁሉ የነበረች አሁንም ታፍና በመታዘብ ላይ ያለች፤ ወደፊትም የምትኖር ይህች ጥንታዊት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፤ አሁን ህዝቧ ስለሚነጋገርበት ስለ ድንበር ምን ትላለች? የሚለውን ለመዳሰስ ይህችን ጦማር ሳዘጋጅ በውስጧ የተሸከመቻቸውን ሀሳቦች በተጻፉባቸው ቋንቋዎች እንዳሉ አቅርቤያቸዋለሁ። ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚሰነዘረውን አፈና ለመከላከል የጠቀስኳቸውን ሀሳቦች በተጻፉባቸው ቋንቋዎች እንዳሉ በማቅረቤ (ግእዙን ግን ትርጉሜዋለሁ) ይቅርታ በመጠየቅ ያጎደልኩትን እየሞላችሁ፤ የተሳሳትኩትን እያረማችሁ ታነቧት ዘንድ በታላቅ ትህትና አቀረብኩላችሁ። መግቢያ “ድንበር ሲፈርስ፤ መሐሉ ዳር ይሆናል” በሚል ርእስ ይህች ጦማር የፈለቀችበት ዘመን፤ ኢትዮጵያን ከጎረቤት አገር የሚያዋስኗት ድንበሮችና፤ በውስጥም ዜጎቿ … [Read more...] about ድንበር: “ድንበር ሲፈርስ፤ መሐሉ ዳር ይሆናል”
‘አጃኢብ’ ያሰኘው የአዜብ መስፍን ወሬ
"አከ’ሲ" አለ ያገሬ ሰው፣ ከሰሞኑ ‘አጃኢብ’ ያሰኘውን የአዜብ መስፍን ወሬ ሲሰማ። አዜብ ልምድ ያላት ውሸታም እንጂ ልምድ ያላት ኮሜዲያን አትመስልም ነበር። ከሚሚ ስብሃቱ ጋር በያዝነው ሳምንት የተወኑት ድራማ ግን ጦሽ አርጎ ያስቃል። መቼም ጥርስ እንጂ ልብ አይስቅ። ፈንድሻም'ኮ ልቧ እየተቃጠለ ነው ፊትዋ ሚፈካው። ሴትየዋ አይኗን ሳይሆን ቅንድቧን በጨው አጥባ "ምንም የለኝም ግን ይወረስ" ነው የምትለው። መለስ የባንክ ደብተር ይቅርና መንጃ ፈቃድ እንኳ የለውም ስትል የቀለደችበት ወቅት ሩቅ አይደለም። እርግጥ ነው አዜብ በራስዋ ስም እንኳን ሕንጻ፣ ሲም ካርድም ሊኖራት አይችልም። ጥሩ ጋዜጠኛ አልገጠማትም እንጂ፣ ቢገጥማት፣ "እመኑኝ ልጃገረድ ነኝ!" ብላ እያለቀሰችም ቢሆን ለማሳመን ትሞክር ነበር። ልጆቼን እየተበደርኩ ነው የማስተምረው ብላ በተናገረች ሰሞን ኤ.ቢ.ሲ … [Read more...] about ‘አጃኢብ’ ያሰኘው የአዜብ መስፍን ወሬ
ሞት የሰጠን ደስታ
የታጨደው ሳር ድርቆሽ ነው የከብቶች መኖ በመሆን በበሬ ጫንቃ ድካም ጠግቦ አደር ያደረገን፤ የሞተው የግጦሽ ሳር ነው ጮሌ ፈረስ አሳድጎ በጦር ሜዳ የድል ብሥራት ያቀዳጀን ጀግና ተዋጊ አድርጎ፤ የበሬውን ቆዳ ከበሮ የበሬውን አንጀት ጅማት የፈረሱን ሞት በደል የሸንበቆውን ያካል ስብራት፤ የእንስሳቱን ሞት ከእሳሩ ሞት ጋር ስናዋድደው ከሞት ምንጭ ነው ለካስ የደስታ ጅረት የሚወርደው። የሞተ … [Read more...] about ሞት የሰጠን ደስታ
ሹፌሮችን ያስቆጣ መመሪያ ተሻሻለ ተባለ
የአማራ ክልል መንግስት የመንግስት ተሸከርካሪ አያያዝ፣ አጠቃቀምና የንብረት አስተዳደር መመሪያ ሰሞኑን ማሻሻሉን ይፋ ቢያደርግም የከፍተኛ አመራሮች ሹፌሮች በበኩላቸው የተሻሻለው መመሪያ የኛን ሕልውና የሚፈታተን ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ገለጡ። የክልሉ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ሰሞኑን ለክልሉ ቢሮዎች በላከው ደብዳቤ ከመስከረም 1 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ወይም የሥራ ኃላፊዎች ለሥራ ጉዳይ ክልሉን ለቀው ወደ አዲስ አበባ ሲሄዱ የሚመሩትን ተቋም ተሸከርካሪ ይዘው እንዳሄዱ እያሳሰበ በተማከለ መንገድ በከተማው በሚዘጋጁ ተሸከርካሪዎች መጠቀም እንደሚችሉ አብራርቷል። በተማከለ መንገድ በሚዘጋጁ ተሸከርካሪዎች መጠቀም የሚችሉ የሥራ ኃላፊዎች ብሎ የተሻሻለው መመሪያ የጠቀሳቸው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር፣ ም/ርዕሰ መስተዳድርና በዚህ ደረጃ ያሉ ኃላፊዎች፣ የክልሉ … [Read more...] about ሹፌሮችን ያስቆጣ መመሪያ ተሻሻለ ተባለ