• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሞት የሰጠን ደስታ

September 22, 2017 02:02 am by Editor Leave a Comment

                         የታጨደው ሳር ድርቆሽ ነው የከብቶች መኖ በመሆን

                             በበሬ ጫንቃ ድካም ጠግቦ አደር ያደረገን፤

                             የሞተው የግጦሽ ሳር ነው ጮሌ ፈረስ አሳድጎ

                     በጦር ሜዳ የድል ብሥራት ያቀዳጀን ጀግና ተዋጊ አድርጎ፤

                             የበሬውን ቆዳ ከበሮ የበሬውን አንጀት ጅማት

                             የፈረሱን ሞት በደል የሸንበቆውን ያካል ስብራት፤

                             የእንስሳቱን ሞት ከእሳሩ ሞት ጋር ስናዋድደው

                       ከሞት ምንጭ ነው ለካስ የደስታ ጅረት የሚወርደው።

                             የሞተ በሬ አንጀት ነው፤የክራር ጅማት ሆኖ

                             ያሳለፍነውን ህይዎት ወደ ፊት አጠንጥኖ

                             መልሶ የሚያኖረን ያለፈውን ጊዜ ትዝታ

                             ሳናውቀው ለካስ ሞት ነው፤የሚለግሰን ደስታ።

 

                            የሞተ በሬ አንጀት ነው፤የክራር ጅማት ሆኖ

                            ልባችንን የሚያሸፍተው በቸበለው ቅኝት ፋኖ።

  

                            የሞተ በሬ ቆዳ ነው፤ከበሮ ሆኖ ተወጥሮ

                            ሲነረት ሲደበደብ ልዩ ቃና ድምጽ ፈጥሮ 

                            ባጀቡት ዜማዎች ግነት ቅላጼውን አጉልቶ

                            መድረኩን ሲነቀንቀው ንዝረቱ ስሜት ነክቶ፤

                            የተሰበረው ሸንበቆ ነው፤አካሉ ተበሳስቶ

                       በጣት ላይ ትንፋሽ ጨምሮ፤የዋሽንት ድምጽ አፍልቆ

                            አእምሮን የሚያብከነክን የሰውን ቀልብ ሰርቆ

                           የሞተ ፈረስ ጭራ ነው፤የአዝማሪ ጥበብ ማሲንቆ

                               ደስታ የሚዘራብን ስሜታችንን ሰርቆ።

 

                           ከተገደለ እሳር፣ከተገደለ በሬ፣ ከተሰበረ ሸንበቆ

                     ከሞተ በሬ አንጀት፣ከሞተ ፈረስ ጭራ መረዋ ድምጽ ፈንጥቆ

                           ከሞተው ክርስቶስ ህይዎት፣የምህረት ፀበል ፈልቆ

                           የአዳምን ልጆች ሁሉ በደሙ ዋጅቶ ያፀዳው

                           ከሞት ምንጭ ነው ለካስ፣የሰው ደስታ የሚቀዳው።

                                               መስከረም 2010

                             *መታሰቢያነቷ የሥነ ሃሳቡ ምንጭ ለሆነው ከያኒ እሱባለው ይታየው

                              አብርሃም በየነ

Filed Under: Literature Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule