• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

እምቢተኝነት በተግባር!

September 27, 2017 12:02 pm by Editor 1 Comment

“ሕዝቡን ካፈንከው እና ከመቃወም ሌላ አማራጭ ካሳጣኸው ይፈነዳል፤ ወጣቱ በሙሉ ዓመጽ ላይ ነው፤ ትውልድ አምጿል”። የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጠኛ JEFFREY GETTLEMAN በኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ በተነተነበት ጽሁፍ ላይ ከተናገረው። ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ።

ዛሬ በተከበረው የመስቀል በዓል ላይ የህወሓትን ማስፈራሪያና ዛቻ ከምንም ባለመቁጠር የውቅሮ፣ ዓዲግራት፣ መቀሌ፣ ጎንደር፣ ደሴና ሌሎች አካባቢዎች ህዝብ “ባለኮከቡን ባንዲራ አይወክለኝም” በማለት ኮከብ አልባውን ሠንቀድ ዓላማ ይዞ በመውጣት እምቢተኝነቱን አድፍረት አሳይቷል።

ሃይለኪሮስ ታፈረ (Hailekiros Tafere) በፌስቡክ ገጹ የዘገበውን አስመልክቶ አምዶን ገብረሥላሴ ይህንን ብሏል፤

“ፖሊስ “ኮከብ የሌለው ባንዴራ ዳሜራ ሸፍናቹሃል” በሚል ሰበብ ዛሬ መስቀል በዓል እያከበረ የነበረው የውቅሮ ከተማ ህዝብ ላይ ድብደባ ፈፅመዋል። የውቅሮ ፖሊስ የመስቀል ዳሜራ በኮከብ የሌለው ባንዴራ ሸፍናቹሃል በማለት በህዝቡ በተለይ በወጣቶችና ህፃናት ላይ ድብደባ ፈፅመዋል። ህወሓት በስመኮከብ ህዝበ ክርስትያን ድብደባ ፈፅማለች።”

በጎንደር፣ በደሴ፣ በመቀሌ፣ በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ሕዝቡ በተመሳሳይ እምቢተኝነቱን ኮከብ አልባውን ሠንደቅ ይዞ በመውጣት አሳይቷል።

በአዲስ አበባ ከበሮውን በባለኮከቡ ጠቅልለው የወጡትን አስመልክቶ እሸቱ ሆማ ቀኖ Eshetu Homa Keno) ይህንን በማለት ተሳልቋል፤

“የሰንደቅ አላማ አዋጁ አንቀፅ 23(9) ደግሞ ሰንደቅ አላማን የህንፃ ወይም የሌሎች ቁሳቁሶች መሸፈኛ ማድረግ የተከለከለ ነው፣ እስከ 3 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ ወይም እስከአንድ አመት እስር ያስቀጣል ይላል፤ ያው ለማስታወስ ያህል ነው”

ይህንኑ ፎቶ በቅድሚያ በፌስቡክ ገጹ በመለጠፍ ስዩም ተሾመ (Seyoum Teshome) የሚከተለውን አስፍሯል፤

“እዩ እስኪ፣ #የባንድራው_ኮከብ ካሜራው ውስጥ “ገባ-አልገባ” ብለው የተጨነቁ አይመስልም? ታዲያ በእነዚህ ምዕመናን አዕምሮ ውስጥ እየተመላለሰ ያለው #የአምላክ ሥራ ወይስ #የመለስ ሥራ ነው?”

አፍቃሪ ህወሓት የሆነው የፌስቡክ “አርበኛ” ዳንኤል ብርሃኔ በዛሬ በጎንደርና ደሴ ከተሞች በተካሄደው የመስቀል በዓል አከባበር ላይ ኮከብ የሌለበት ባንዲራ ጥቅም ላይ መዋሉን አስመልክቶ በቀጣይ ቀናት አንዳንድ ውዝግቦች ሊነሱ ስለማለቱ ስዩም ይህንን ምላሽ ሰጥቷል።

“ይህ ባለ ኮከቡ ባንዲራ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እንደሆነ የተደነገገው የኢፊድሪ ሕግ-መንግስት ላይ ነው። ነገር ግን፣ ሕገ-መንግስቱን በመጣስ ግንባር ቀደሙ #የኢህአዴግ_መንግስት ራሱ ነው። “ባለቤቱ የናቀው አሞሌን ማንም አይፈልገውም!” እንዲሉ ኢህአዴግ የናቀውን ሕገ-መንግስት #የጎንደርና_ደሴ ህዝብ የሚያከብረው በምን ዕዳው ነው?! ሀገሪቱ እየተመራች ያለው #በፀረ_ሽብር አዋጁ እንጂ በሕገ-መንግስቱ አይደለም። እሱ ደግሞ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላም ላይ ያለው አንባሻ ይሁን ኮኮብ አይደነግግም! ስለዚህ የጎንደርና ደሴ ህዝብ ከፈለገ #የራስተፈራያን ባንዲራ ይዞ መስቀልን ማክበር ይችላል!!!”

ስዩም በጽሁፉ መጨረሻ ላይ ከላይ የጠቀስነውን ሃሳብ ብዚህ መልኩ ደግሞታል፤

“የታፈነ ሕዝብ ያምፃል!” የጎንደር፥ ደሴ፥ ዓዲግራትና ውቅሮ ከተማ ነዋሪዎች የመስቀል በዓል አከባበርን ኮከብ የሌለበትን ባንዲራ መጠቀማቸው ከላይ ከጠቀስኩት ጋር ተመሳሳይ ነው። አመፅና ተቃውሞ አደባባይ ወጥቶ ድንጋይ መወርወር ብቻ አይደለም። የመንግስትን ቅቡልነት ሊያሳጣ የሚችል ማንኛውም ዓይነት ነገር መፈፀም ነው።”

የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁንም በሁሉም አቅጣጫ የህወሓት/ኢህአዴግን አገዛዝ አልቀበልም እያለ በሚያገኘው አጋጣሚ ሁሉ እምቢተኝነቱን እየገለጸ ነው! ትውልድ አምጿል! ሕዝብ እምቢ ብሏል!

ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ ከማኅበራዊ ገጾች ያጠናቀረው።

Filed Under: News, Social Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Mulugeta Andargie says

    September 28, 2017 09:04 pm at 9:04 pm

    ኢህኣድግ! ኢህኣድግ!ኢህኣድግ!!
    ምነው ብትጠርግልን ይህን እንኩቶ! እንደ ደርግ??
    በበዓል ቀን በመስቀል!
    ስዕሉ ሌላ ወሬው ለየቅል
    እንግዲህ ምን እንበል??
    የስርዓት ለውጥ ዝም ብሎ
    በተመኘሁ ወይ አባብሎ
    ይመጣ መሰለው ጓዙን ጥሎ??
    ምነው ኢህድግ ይህን ኮተት
    በምርጫ ይሻላል ብለህ ከተትክ?
    አልጫ ኮነው ፍርክርክ!!!!
    ጭብጥ የማይሉ በመድረክ??
    ስድባቸው መረረን ያለልክ!
    ምነ ወጀብ ቢኖርህ
    መጥረግ ነበር!እንዲያ እንድንልህ!!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule