“አከ’ሲ” አለ ያገሬ ሰው፣ ከሰሞኑ ‘አጃኢብ’ ያሰኘውን የአዜብ መስፍን ወሬ ሲሰማ። አዜብ ልምድ ያላት ውሸታም እንጂ ልምድ ያላት ኮሜዲያን አትመስልም ነበር። ከሚሚ ስብሃቱ ጋር በያዝነው ሳምንት የተወኑት ድራማ ግን ጦሽ አርጎ ያስቃል። መቼም ጥርስ እንጂ ልብ አይስቅ። ፈንድሻም’ኮ ልቧ እየተቃጠለ ነው ፊትዋ ሚፈካው።
ሴትየዋ አይኗን ሳይሆን ቅንድቧን በጨው አጥባ “ምንም የለኝም ግን ይወረስ” ነው የምትለው። መለስ የባንክ ደብተር ይቅርና መንጃ ፈቃድ እንኳ የለውም ስትል የቀለደችበት ወቅት ሩቅ አይደለም። እርግጥ ነው አዜብ በራስዋ ስም እንኳን ሕንጻ፣ ሲም ካርድም ሊኖራት አይችልም። ጥሩ ጋዜጠኛ አልገጠማትም እንጂ፣ ቢገጥማት፣ “እመኑኝ ልጃገረድ ነኝ!” ብላ እያለቀሰችም ቢሆን ለማሳመን ትሞክር ነበር። ልጆቼን እየተበደርኩ ነው የማስተምረው ብላ በተናገረች ሰሞን ኤ.ቢ.ሲ ኢንተርናሽናል የተባለው የማድሪድ ጋዜጣ ወ/ሮ አዜብ መስፍን በአንድ ቀን የግል ግብይት ብቻ 1.5 ሚሊዮን ዶላር እንዳወጣች ዘግቦ ነበር።
የወዲ ስብሃቱ ልጅ አላማ ‘የሙስናዋን ንግስት’ ነጻ ለማውጣት መሞከር ባይሆን ኖሮ፣ በነካ እጅዋ ሰሞኑን በወደቀ ሂሳብ እየተቸበቸቡ ስላሉ የአዲስ አበባ ሕንጻዎች ጉዳይ ታነሳ ነበር።
የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ጠቅልሎ የያዘው ኤፈርት አናት ላይ ቁጭ ብላ “ምንም የለኝም” የሚል ነጠላ ቀልድ የለቀቀችው አዜብ 30 ሚሊዮን ብር ከኪስዋ መዝዛ ለመቀሌ ስፖርት ክለብ መለገስዋን እንኳ ረስታዋለች። ግብር የማይከፍልና የኦዲት ቁጥጥር የማይነካው ደጀና የተባለው የማፍያ ኩባንያ ከኤፈርት ጋር ተጣምሮ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ እኩሌታ ይዟል። ካፒታሉ አፍሪካ አንደኛ የሆነው የዚህ ጥምር ዋና ሥራ አስፈጻሚ (CEO) ነኝ ብላናለች አዜብ። ሰማይ አይታረስ፣ ንጉስ አይከሰስ፣ ደሞዝ አይነገር … ደሞዝ አይጠየቅ! በዛሚ!
“ዛሚ ኤፍ.ኤም” ተብሎ በሚጠራው የነሚሚ ስብሀቱ ራዲዮ ጣቢያ ከዚህ ቀደም የሞራል ቀውስ ውስጥ ገብተው የሚዋኙ ትናንሾችን እያቀረበ፣ በደረቀ ፕሮፓጋንዳ ብቻ ብዙ መጓዝ ባለመቻሉ፣ የፕሮግራም ለውጥ ያደረገ ይመስላል። እንደ አዜብ መስፍን አይነቱን ጥያቄና መልስ እያስጠና ተከታታይ ድራማ ማቅረብ ጀምረዋል። የመጀመርያው ሾው በቴዲ አፍሮ ተጀመረ ። ገድለው ሃውልት መስራት ለነሱ አዲስ ነገር አይደለምና ጸሃይ የሞቀውን “እርምጃው ፍትሃዊ አይደለም” እንቶፈንቶ ደጋገመችው። የቴዲ አፍሮን የአልበም ምረቃ ያገደውን ስውር እጅ አደባብሳ አለፈችው። ስለማታውቀው ፍትህ እና መብት መለፈፍዋ ግን ብዙዎችን ሳያስደምም አልቀረም።
አዜብ በተከታዩ ክፍል ብቅ ብላ፣ “የምተዳደረው በዶሞዝ ነው። መለስም፣ እኔም፣ ልጆቼም ሃፍት የላቸውም” አለችን።
“ውልና ማስረጃ የሌለው ሃፍት ካላኝ ቦታውን ያሳዩኝ እና ለኢትዮጵያ ህዝብ ልመልሰው” የሚለው ሕጻን ልጅን እንኳ የማያሳምን አባባልዋ ትንሽ ያስቃል። ሕዝብ በደቦ ወጥቶ የአዜብና ዘመዶችዋን ያልተመዘገበ ንብረት እንዲያፈላልግላት መጠየቅዋ ነው ወይንስ የእሷም ህንጻዎች እንደ ኮንዶሚኒየሙ “ጠፍተዋል” ብለው ነገሯት? ከሠበታ የወሰደችው 1200 ሄክታር መሬት የቀብርዋ ስፍራ መሆኑ ነው። ይህ ደግሞ በነሱ ቋንቋ ሙስና አይባልም። ሙስናም ቢሆን ለከባባድ ሚዛን የህወሃት አባላት የአገልግሎት ስጦታ ነው። አቶ አያሌው መንገሻ፣ የቀድሞው የደህንነት መ/ቤት ሹም ህብር ሬዲዮ ላይ ቀርበው በሰጡት ቃለ ምልልስ “በሕወሃት ሙስና ወንጀል አይደለም” ብለውናል።
ኮሜዲያን ወደ ውጭ ሲሰደዱ፣ ፖለቲከኞቹ ቦታቸውን ይዘዋል ልበል? ከሰሞኑ የህወሃት ካድሬዎች እንደጉድ መቀለድ ጀምረዋል። አዜብ እና ከሚሚ ተደራጅተው የሰሩት ይህ እየሳቁ-ማንባት ተውኔት ግን ከኮሜዲ መስመር ወጣ ይላል።
ቃለ-ምልልሱ የተጠና ላለማስመሰል እንኳ አለመሞከራቸው፣ ለአድማጭ ያላቸውን ንቀት ያሳያል። “መኖርያ ቤት ሰርተሻል?” የሚለው የመጀመርያ ጥያቄ ሲቀርብላት ነበር፣ አዜብ “ከሌላው ጋር አብሬ ልመልሰው” ስትል ተከታዩን ጥያቄም እንደምታውቀው ያስፎገረችው። መዋሸት አንድ ነገር ነው። ውሸት ለማስመሰል መቻል ደግሞ ማወቅን ይጠይቃል። ይህንን እንኳን ማድረግ አልቻሉም። የዛሚዋ ካድሬ ሚሚ ስብሃቱ አዜብን ለማንጻት ብዙ የታከከች ይመስላል – ለዛሬ ባይሳካም።
አዜብ እውቀት ነጻ ትሁን እንጂ፣ በጣም ደፋር ናት። የእንግሊዝን መንግስትንም ሆነ የአውሮፓ ህብረትን ብትጠይቁ ምንም የሌለኝ ድሃ መሆኔን ይነግሯችኋል ትለናለች። አዜብ ሃብታም ግን የምትሆነው ህወሃት ወይንም ኤፈርት ሲለቅቃት ብቻ ነው። “ድርጅቴ ሲለቅቀኝ በግሌ ከጉልት ንግድ በመጀመር ሃብታም ሆናለሁ” ስትል አስቃናለች።
ይህንን ያድርግልሽ ብለናል!
ክንፉ አሰፋ
በለው ! says
——– ታጋይቷ አልሰሙም ? “ኀይለመለስ ከአማራ ክልል በስተቀር ሁሉም ክልሎች ወርቅ በሰፌድ ይነጠራል ” በወይልቃይት አማራነትዎ አንድ ሰፌድ አልሰፉም ? ወይስ ሰፌድ መግዣ የለዎትም? አለዚያም ጥሩ ጎረቤት የለዎትም ? ምን አልባት የመለስ ወንድም ጢቢኛ ሲሸጥ፡ እህቱ ጠላ ስትሸጥ ፡እርስዎ ጉልት ቸርቻሪ መሆን ያማረዎት ፓርቲዬ አለቅም አለኝ ትወና ህወሃት ሥራ አይንቅም ድልድይ ማፍረስ፡ ባንክ መዝረፍም፡ የዕርዳታየለዎትም፡፡፡፡ሙስናም የተካነበት ፍጥረቱ አደለም እንዴ? ዋሸሁ?
______ “የምተዳደረው በዶሞዝ ነው። መለስም፣ እኔም፣ ልጆቼም (ሃፍት )የላቸውም አለችን። ኤ.ቢ.ሲ ኢንተርናሽናል የተባለው የማድሪድ ጋዜጣ ወ/ሮ አዜብ መስፍን በአንድ ቀን የግል ግብይት ብቻ 1.5 ሚሊዮን ዶላር እንዳወጣች ዘግቦ ነበር።”
” አዜብ እውቀት ነጻ ትሁን እንጂ፣ በጣም ደፋር ናት። የእንግሊዝን መንግስትንም ሆነ የአውሮፓ ህብረትን ብትጠይቁ ምንም የሌለኝ ድሃ መሆኔን ይነግሯችኋል ትለናለች። አዜብ ሃብታም ግን የምትሆነው ህወሃት ወይንም ኤፈርት ሲለቅቃት ብቻ ነው። “ድርጅቴ ሲለቅቀኝ በግሌ ከጉልት ንግድ በመጀመር ሃብታም ሆናለሁ”… ይህንን ያድርግልሽ ብለናል!
_____ “የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ጠቅልሎ የያዘው ኤፈርት አናት ላይ ቁጭ ብላ “ምንም የለኝም” የሚል ነጠላ ቀልድ የለቀቀችው አዜብ 30 ሚሊዮን ብር ከኪስዋ መዝዛ ለመቀሌ ስፖርት ክለብ መለገስዋን እንኳ ረስታዋለች። ግብር የማይከፍልና የኦዲት ቁጥጥር የማይነካው ደጀና የተባለው የማፍያ ኩባንያ ከኤፈርት ጋር ተጣምሮ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ እኩሌታ ይዟል። ካፒታሉ አፍሪካ አንደኛ የሆነው የዚህ ጥምር CEO ነኝ ብላናለች አዜብ። ውልና ማስረጃ የሌለው ሃፍት ካላኝ ቦታውን ያሳዩኝ እና ለኢትዮጵያ ህዝብ ልመልሰው” ስትል አስቃናለች።” ሕዝብ የወርቆቹ ሲሆን ቦርቃቃው ብሔር ብሔረሰብ ግን ለጭፈራ እንጂ ለሀፍት ውርስ እንኳ ቦታ የለውም ማንነቱን የጣለ ሀፍት ይጠይቃልን? ወ /ሮ አዜብ ቤት አለዎት?ከአስረኛ እና ጎላ ከጥሊያን ወረራ ግዜ በሹምባሽነት የተሸለሙት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው ሀፍት በገዢውና አውራው ፓርቲ ተራራውን ላንቀጠቀጡ በውልና ማስረጃ አፀደቀላቸው!?
*************!
“ቀዳማዊት እመቤት አትበሉኝ ” ! ያ …ማለት የአቶ እከሌ ሚስት ለማለት ነው ። ታጋይ አዜብ መስፍን( ጎላ ) በሉኝ ሲሉ ለዚህ ኮራጅ ትውልድ ማረሚያ ሰጡ ምንስ ቢሆን ወልቃይት ተከዜን ሳይሻገሩ ለአማርኛ አይቀርብምን!?
“ተመዝግቦ በነፃ የታደላችሁ ሀብትና መሬት ስንት ነው ? ብሎ የሚጠይቅ የለም፡ ይህ ሕዝባቸው ማንነቱን ያወቀው እና የተፈጠረው በሕወሓት መልካም ፈቃድ ነው ። ” ከውጭ ይዘነው የመጣነውን ገንዘብ ሌላ ሀገር ኢንቨስት ከማድረግ ለአማራና ኦሮሞ ትንሽ ትንሽ በጭቀንላቸዋል ። ለመሆኑ የኢፈርትን ገንዘብ የሚጠይቀው ምን ሰው ? ማለቴ ሰው ስል የተማረ ማለቴ ነው”ዶክተር ስብሃት ነጋ
** የሚደግፋቸው ፹ከመቶ ገበሬ ስላልተማረ ሰው አደለም !። ማንነትህን በፍቃደኝነት ለቀህ ሀገርህን በክልል ለውጠው የበይ ተመልካች ፡ቤተ ሙከራ፡ ሆነህ ለጭፈራ ተጠራርቶ ተገፋትሮ የሚመጣ፡ የልዩ ጥቅማጥቅም ምርኮኛ ሕዝብ፡ የእርዳታ ንፍሮ እየነፋ በተውሶ ልብስና የፀሐይ መነፅር ተወጥሮ የአዞ ዕንባ :ልሃጭና ንፍጡን ባዶ ሳጥን ላይ ሲያዝረከርክ ቤተመንግሥት ቁጭ ብለው አድርባይ ! እያሉ ተሳልቀዋል አሁን ቢኮምኩ ብርቅ ነው ? ጠቅላዩ ባለቤታቸው የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦችን ቀልድና ተረት ጨርሰው የቻይና ተረትና አባባል ፓርላማ መኮመክ ሲጀምሩ ጠቀለሏቸው።ህወሓት ኢህአዴግና ኢፈርት በመለስ ዜናዊ ቤተሰብ ጭንቅላት ብቻ እየተመራ ሌላው ሎሌ መሃይም ነው ማለት አደለምን ?ለመሆኑ የመንገድ ላይ ነዋሪ ልጆች እና ባለቤታቸውን ተማምነው ሀፍት ንብረታቸውን ገጠር ተነጥቀው ቤተመንግሥት መንገድ ዳር የወደቁትን ብሔር ብሔረሰቦች እንደምን አደረጓቸው ? እነሱ ሀፍት አካብተው መለስ ቤተሰብ ላይ የተነሱትን ሥም አጥፊ፡ የሙሰኞች ቡድን እንዳለ አያወቁ እስከ ዛሬ ለኢትዮጵያ ሕዝባቸው ለምን አላጋለጡም ? አስገደ እና ገብረመድህን የተባሉትን ዛር ቀስቃሽ አስጓሪ ይላክባቸው !!።
ዘይገርም…
balcha says
Azeb and aba sebhat nega are clue less but clue givers. Lie is there moto and arrogance is there identity. They are all lucky because they are in Ethiopia, if they were some where else, it could have been a different story.