“ፍርድ ቤቶች በነጻነት እንዲሠሩ ከተለቀቁ ፍትሕ ይበየናል” “ሁለቱም ተወዳዳሪዎች ውሳኔውን በመቀበል ለአገራቸው አኩሪ ተግባር ፈጽመዋል” ኦባንግ ሜቶ “ዛሬ በአፍሪካ ታላቅ ፍትኅ ተፈፀመ” ራይላ ኦዲንጋ በኬኒያ በቅርቡ የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በርካታ ችግሮች የገጠሙትና በአገሪቱ ሕግጋት መሠረት ያልተካሄደ ነው ሲል የኬኒያ ጠቅላይ ፍርድቤት ውጤቱን ውድቅ አድርጎታል፡፡ ከምርጫው ከመጀመሩ በፊት የኬኒያን ፖለቲካ በቅርቡ የሚከታተሉት ኦባንግ ሜቶ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በማድነቅ “ፍርድ ቤቶች በነጻነት እንዲሠሩ ከተደረጉ በምዕራቡ ዓለም ብቻ ሳይሆን አፍሪካም የሕግ የበላነይትና ፍትህ ይሰፍናል፤ ሁለቱም ተወዳዳሪዎች፤ ራይላ ኦዲንጋ ከአመጽ ይልቅ በሥርዓት ጥቄያቸውን ለፍትሕ አካል በማቅረባቸው፤ ኡሁሩ ኬኛታ ደግሞ ለፍርድ ቤቱ ውሳኔ እገዛለሁን ማለታቸው የሚደነቁ ናቸው፤ … [Read more...] about ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን በፍርድቤት ውድቅ በማድረግ ኬኒያ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆነች!

