አቶ ማሞ፣ የዘመናይና የእስከዳር አባት፣ የወ/ሮ ከልካይ ባለቤት፣ አንድ ወፍጮ ቤት አላቸው። እህልም ይነግዳሉ። ጤፍ፣ ስንዴ፣ ገብስ እዚያው ገዝተው እዚያው የሚያስፈጩ ደምበኞች ሞልተዋል። አቶ ማሞ በሰፈሩ ተወዳጅ ናቸው። ተወዳጅ ያደረጋቸው ደግሞ ምርቃታቸው ነው። ምርቃቶቹ በቄንጥ የተደረደሩ ቃላት ሳይሆኑ 50 ኪሎ ጤፍ ላይ ሁለት ወይም ሶስት ኪሎ መጨመራቸው ነው። “እጅ አጠረኝ ...” ላለ ጎረቤት ደግሞ መልሳቸው፤ “ምን ችግር አለ! ሲያገኙ ይከፍላሉ ...” ነው። የተበጠሰ ቺንጋ እየቀየሩ፤ መፋቂያ የተሰኩባቸውን ጉራማይሌ ጥርሶቻቸውን በፈገግታ ብልጭ እያደረጉ። አቶ ማሞ ሃብታም አይደሉም። ድሃም አይደሉም። የሚያገኙት ቤተሰባቸውን ለማስተዳደር ይበቃቸዋል። ያቶ ማሞ መኖሪያ ቤትና ወፍጮ ቤት የተያያዘ ነው። አጥር ነው የሚለየው። ሌሊት ወፍጮ ቤቱ ሲዘጋ እንዳይላሉ የሚባለው፤ ቀኑን … [Read more...] about “ባቡር ይሄድበታል”
Archives for October 2015
በንቁጣጣሽ! ምን ቀጠፈሽ?
ዘመን ፊትሽ ተከምሮ እየታዬ ስራሽ አምሮ እንቁጣጣሽ አንድ ብለሽ አርባ ድረስ እድሜ ቆጥረሽ እንደ ቤቶች የሳቅ ተውኔት እንደ ጨቤ ስካር ህይወት ሞት ራሱን ያሾፍሽበት ለምንድነው? በይ ንገሪኝ እባክሽን አደብቂኝ ባንቺው ቀዬ የተወለድኩ ፊደል በጄ እዛው የያዝኩ መስፍን ሜዳ የተራገጥኩ በጨበጣ ብይ ያስቆጠርኩ ቲቸር ታዬ ያስተማሩኝ ገብሬ ኩርኩም ያቀመሰኝ የሲሚንቶ ጭስ ያወዛኝ ቅዱስ ያሬድ ተሳልሜ ከሽፋ ቤት ተሰይሜ ያቶ ማሞን ኪኒን ቅሜ እዛው ኖሬ እዛው ያደኩ የቃጠሎው ቀን የተረፍኩ እኔ እማውቅሽ የማታውቂኝ የሰፈርሽ አንድ ስው ነኝ ይሄን ሁሉ ዘርዝሬልሽ ጥያቄዬን ስጠይቅሽ ዝም አትይም መቼም ከፍተሽ ፊት ለፊትሽ ተስፋሽ ሞልቶ እየታየ ዝናሽ ጎልቶ እንደጸደይ ባገር ፈክተሽ በህዝብ ፊት ደምቀሽ ታይተሽ በአዲስ አመት በንቁጣጣሽ በ´ለቱ ለት … [Read more...] about በንቁጣጣሽ! ምን ቀጠፈሽ?
ኢኮኖሚው [እንዳወራነው] አላደገም!
በነጻ አውጪ ስም ኢትዮጵያን እየገዛ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር - ህወሃት ሰሞኑን ዕቅድ ብሎ ባወጣው ዘገባ ላይ ለዓመታት ሲወራለት የነበረው የድርብ አኃዝ ዕድገት እንደተደሰኮረለት እንዳልሆነ እንዲያውም ኢኮኖሚው ውድቀት ላይ መሆኑን የሥራ አጥነት ሁኔታ አሳሳቢ ከመሆኑ የተነሳ በከተማዎች ብቻ ሳይሆን በገጠርም ችግር እየሆነ መምጣቱን ለራሱ ባመነበት የኢኮኖሚ ፕላን ላይ አትቷል፡፡ ነገረ ኢትዮጵያ/Negere Ethiopia በፌስቡክ ገጹ ላይ ያወጣው ዘገባ ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል፡- መንግስት ኢኮኖሚው ውድቀት ላይ መሆኑን አመነ • የኢኮኖሚ መዋቅሩ ከሳህራ በታች ከሚገኙ ሀገራትም ያነሰ ነው • የወጪ ንግድ ገቢ እና የገቢ ንግድ ክፍተት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል • ለውጭ ገበያ የቀረበው አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ቡና፣ ሰሊጥና … [Read more...] about ኢኮኖሚው [እንዳወራነው] አላደገም!
“እርዳታው እህል ተሽጦ ለ “አባይ” እንዲውል ተወስኗል”
ለ900ሺ አስቸኳይ እርዳታ የሚያስፈልገው ህዝብ የእርዳታ እህል የጫኑ መኪኖች ሰሙኑን መቀሌ ከተማ ደርሰዋል። አንድ ሚሊዮን ለሚጠጋ ተረጂ እስከ 350 መኪኖች እህል ጭነው በቀጥታ ከጅቡቲ ትግራይ ገብተዋል። መንግስት እንዳለው የጫኑት ኢትዮጵያ ውስጥ የተመረተ ሳይሆን ከውጭ በእርዳታ የገባ መሆኑ ጭነው የመጡት ሹፌሮች አውግተውኛል። "ድርቁ በቁጥጥር ስር ኣውለነዋል" የሚል የትግራይ መንግስት መግለጫ ተደጋግሞ እየተሰማ ባለበት ቅፅበት "ለእርዳታ የመጣው እህል እየተሸጠ ነው" የሚል ወሬ በስፋት እየተሰማ ነው። እህሉ መቀሌ ከተማ ወደሚገኙ የዱቄት ፋብሪካዎች እየተሸጠ መሆኑና ጥያቄ ላነሱ ሹፌሮች ደግሞ "ድርቁን በቀላሉ ስለተቆጣጠርነው ትርፉ ተሽጦ ለአባይ እንዲሆን ተወስኗል" ተብሎዋል። ከእኔ ጋር ሁኖ ጨዋታው ሲያዳምጥ የነበረው ወጣት "… የትኛው አባይ ነው? አባይ ግድብ፣ አባይ … [Read more...] about “እርዳታው እህል ተሽጦ ለ “አባይ” እንዲውል ተወስኗል”
ሠራተኛውን ማን አቃጠለው?
የጎልጉል እማኝ ዘጋቢ (ireporter) ከጥቂት ቀናት በፊት በአፋር ክልል ሃዳር ወረዳ ኤሊ ውሃ ከተማ ቅዳሜ መስከረም 22፤2008 ዓም ስለተፈጸመው ግድያ መረጃ ልከውልናል፡፡ ከመረጃ አቀባያችን ጋር በተደጋጋሚ በተላላክነውና ባቀረብነው በርካታ ጥያቄዎች መሠረት ያገኘነው መረጃ ይህንን ይመስላል፡- እጅግ ዘግናኝ የሚባለው ግድያ የተፈጸመው ከላይ በተጠቀሰው ሥፍራ በሚገኘው የቻይና መንገድ ሥራ ፕሮጀክት እየተባለ በሚጠራው ግቢ ውስጥ ነው፡፡ የእማኝ ዘጋቢው በራሳቸው አገላለጽ እንዲህ ዘግበውታል፡- (የላኩልን የእንግሊዝኛ ፊደላትን በመጠቀም ሲሆን ወዳማርኛው እንዲህ መልሰነዋል) “ወንጀሉ የተፈጸመው ቅዳሜ መስከረም 22፤2008 ዓም በአፋር ክልል ሃዳር ወረዳ በኤሊውሃ ከተማ ግቢ ተብሎ በሚጠራው የቻይና መንገድ ሥራ ፕሮጀክት ውስጥ ነው፡፡ የተቃጠለው ልጅ ወልዱ ይባላል፡፡ በ(ፕሮጀክቱ) … [Read more...] about ሠራተኛውን ማን አቃጠለው?
ነጻ አውጪ ግምባር አገዛዝ እንጂ መንግሥት አይመሠርትም
ላለፉት 25 ዓመታት በነጻ አውጪ ግምባር ስም ኢትዮጵያን እየገዛ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር "ኢህአዴግ" ብሎ በፈጠረው ስያሜ አገር በግፍ እየገዛ መሆኑ ሳያንስ በየአምስት አመቱ በሚያካሂደው "ምርጫ" የሚመሠርተው "መንግሥት" መፍትሔ ሊሰጥ እንደማይችል መድረክ አስታወቀ። ሰማያዊ ፓርቲ በበኩሉ በኢትዮጵያ ለተከሰተው ረሃብ የአገዛዙ ፓርቲ ተጠያቂ ነው ይላል። የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ "ኢህአዴግ ያቋቋመው መንግስት መፍትሄ አይሰጥም ተባለ" በሚል ርዕስ ያወጣው ዜና ከዚህ እንደሚከተው ይነበባል:- ኢትዮጵያ ውስጥ እየተስተዋለ ያለው ረሃብ የገዥው ፓርቲን ፖሊሲ ውድቀት ያሳያል ሲል ሰማያዊ ፓርቲ ከሰሰ፡፡ ኢህአዴግ ያቋቋመዉ አምባገነን መንግስት ለኢትዮጵያ መሰረታዊ ችግሮች መፍትሄ ሊሰጥ አይችልም ሲል ታቃዋሚዉ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ … [Read more...] about ነጻ አውጪ ግምባር አገዛዝ እንጂ መንግሥት አይመሠርትም
ቅጥ ላጣው ሙስና “ተጠያቂ ነኝ” – ህወሃት
ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም እየገዛ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር - ህወሃት በተለይ በአዲስ አበባ ቅጥ ያጣውን ሙስናና ዘረፋ በተመለከተ በጠራው ስብሰባ አስቀድሞ በመቀሌው "ተጠያቂ ነኝ" በማለት እንዳመነው አሁን ደግሞ ነዋሪው ችግሩን ራሱ እንዳመጣው ራሱ ይፍታው ማለቱ ተነግሮዋል:: የሪፖርተር ዘገባ እነሆ:- * ሙስና በአዲስ አበባ በኔትወርክ ተይዞዋል ሙስና፣ ኪራይ ሰብሳቢነትና የመልካም አስተዳደር እጦት ከወረዳ እስከ ከተማ አስተዳደሩ ድረስ በኔትወርክ የተያያዙ በመሆናቸው ሊፈታቸውም ሆነ ሊያስቆማቸው የሚችለው ድርጅቱ ኢሕአዴግ ብቻ መሆኑ ተጠቆመ፡፡ የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን መስከረም 20 ቀን 2008 ዓ.ም. በግዮን ሆቴል ለግማሽ ቀን አዘጋጅቶት በነበረው የውይይት መድረክ ላይ ከተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት፣ የሁሉም ክፍላተ ከተሞች፣ … [Read more...] about ቅጥ ላጣው ሙስና “ተጠያቂ ነኝ” – ህወሃት
ኑሮ በመፈክር
አቶ ዠ 57 አመታቸው ነው። መተዳደሪያ አላቸው። እንዴት ያለ ሙያ!! ባሥራ ሰባት አመታቸው የጀመሩት። አርባ አመት ሙሉ ያለማቋረጥ እየሰሩ ያሉት። ሰዉ ከሥራው በመንግሥት ለውጥ፣ በሰበብ ባስባቡ ሲባረር እሳቸው ሥራ አላጡም። ሥራቸው? መፈክር አድምቆ መጻፍ። መጀመሪያ በሁለት ቃላት ጀመሩ። በነጻ “ኢትዮጵያ ትቅደም!” ብለው አድምቀው ጻፉ። ከዚያ እየተከፈላቸው ደግሞ “ከቆራጡ መሪ ጋር ወደፊት!!” ብለው ቀጠሉ። ሰውየው ብቻቸውን ሲቀሩ። ወደ መጨረሻው ግድም ደግሞ “አብዮታዊት እናት ሃገር ወይም ሞት” ብለው ደጋግመው አድምቀው ጻፉ። “አብዮታዊት እናት ሃገር ወይም ዝምባብዌ!” ብለው አላፌዙም። አቶ ዠ ፕሮፌሽናል ናቸው። የከፈለ ያጽፋቸዋል። ጊዜው እየረዘመ ሲሄድ መፈክሮቹም መርዘም ጀመሩ። አንድ ገጽ የሚሆን መፈክር ጻፍ ሲባሉ እንኳን “እሺ፣ ሂሳቡ ይሄ ነው” ብለው … [Read more...] about ኑሮ በመፈክር
እነኚህ ሰዎች ማናቸው? – ፲፱ መልስ
ከአዘጋጆቹ፤ ከጥቂት ወራት በፊት በወዳጃችን ወለላዬ ለቀረበው የበርካታ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ አገዛዝ ዘመን የካቢኔ አባላት የነበሩ ባለሥልጣናትን ፎቶ ለያዘው ጥያቄ ምላሽ በመስጠት የተባበራችሁትን ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን:: ከተለያዩ ምንጮ ያሰባሰቡትን ምላሽ ወለላዬ አጠር ካለች ግጥም ጋር በቁጥራቸው ቅደም ተከተል አቅርበውታል፡፡ ከዘመኑ መብዛትና መረጃ መዛባት ምክንያት በምላሹ ላይ ስማቸው ወይም ማዕረጋቸው የተዛባ ቢኖር ማስተካከያ ለሚሰጡ ሁሉ አሁንም በቅድሚያ ምስጋናችን ይድረሳቸው፡፡ መልስ በዝርዝር ማስቀመጥ - በቁጥሩ በስሙ ለመግጠም የሚያስችል - ነበረኝ አቅሙ ነገር ግን ለአንባቢ - እዚህጋ ሲቀመጥ እንደዚህ ሲሆን ነው - የሚጥመው ይበልጥ በማለት አስቤ - የሁሉም ዝርዝር ከስር አስፍሬያለሁ - በስማቸው አንፃር መርዕድ መንገሻ (ሜ/ጄኔራል) … [Read more...] about እነኚህ ሰዎች ማናቸው? – ፲፱ መልስ