• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኢኮኖሚው [እንዳወራነው] አላደገም!

October 20, 2015 08:12 pm by Editor Leave a Comment

በነጻ አውጪ ስም ኢትዮጵያን እየገዛ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር – ህወሃት ሰሞኑን ዕቅድ ብሎ ባወጣው ዘገባ ላይ ለዓመታት ሲወራለት የነበረው የድርብ አኃዝ ዕድገት እንደተደሰኮረለት እንዳልሆነ እንዲያውም ኢኮኖሚው ውድቀት ላይ መሆኑን የሥራ አጥነት ሁኔታ አሳሳቢ ከመሆኑ የተነሳ በከተማዎች ብቻ ሳይሆን በገጠርም ችግር እየሆነ መምጣቱን ለራሱ ባመነበት የኢኮኖሚ ፕላን ላይ አትቷል፡፡ ነገረ ኢትዮጵያ/Negere Ethiopia በፌስቡክ ገጹ ላይ ያወጣው ዘገባ ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

መንግስት ኢኮኖሚው ውድቀት ላይ መሆኑን አመነ

• የኢኮኖሚ መዋቅሩ ከሳህራ በታች ከሚገኙ ሀገራትም ያነሰ ነው

• የወጪ ንግድ ገቢ እና የገቢ ንግድ ክፍተት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል

• ለውጭ ገበያ የቀረበው አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ቡና፣ ሰሊጥና የጥራጥሬ ሰብሎች መጠን በእቅዱ ከተያዘው በእጅጉ ያነሰ ነው

• ለውጭ ይቀርባል ተብሎ ከታቀደው ቡና የቀረበው ሩቡ ብቻ ነው

• መስራት የሚቻለውን ያህል የልማት ሥራ ሳይሰራ ቀርቷል

• ሥራ አጥነት በከተማ ብቻ ሳይሆን በገጠር አካባቢዎችም ሰፊ ችግር ሆኗል

ላለፉት 10 አመታት ኢትዮጵያ 11.2 በመቶ በማደግ በዓለም ፈጣን እድገት እያሳዩ ከሚገኙ ጥቂት ሀገራት መካከል አንዷ እንደሆነችና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት ጋር ልትመደብ እንደሆነ ሲናገር የነበረው ኢህአዴግ መራሹ መንግስት የኢኮኖሚ ውድቀት እንዳጋጠመው አመነ፡፡ የብሔራዊ የፕላን ኮሚሽን በመስከረም ወር 2008 ዓ.ም የሁለተኛውን አምስት አመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ (ከ2008-2012 ዓ.ም) ላይ ለመወያየት ያዘጋጀው ረቂቅ ሰነድ እንደሚያሳየው በተለይም መንግስት ለኢኮኖሚው አንቀሳቃሽ ሞተር ነው የሚለው የግብርና ዘርፍ፣ የውጭ ንግድና የማኑፋክቼሪንግ ኢንዱስትሪው ውድቀት አጋጥሞታል፡፡plan

“በአጠቃላይ በተጠናቀቀው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን የተመዘገበው የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር ከሚጠበቀው አንፃር ዝቅተኛ ነው፡፡ የኢኮኖሚው መዋቅር ለውጥ ከማረጋገጥ አንፃር የተመዘገበው አፈፃፀም ዝቅተኛ ነው” ያለው ሰነዱ የኢኮኖሚ መዋቅሩ ከሳህራ በታች ከሚገኙ ሀገራትም ያነሰ እና በጣም ዝቅተኛ መሆኑን አስምሮበታል፡፡ በኢኮኖሚው ችግር ምክንያትም ስራ አጥነት ከከተሞች አልፎ በገጠረ አካባቢዎችም ሰፊ ችግር እንደሆነም ተመልክቷል፡፡

ከሸቀጦች የወጪ ንግድ ይገኛል ተብሎ የተገመተው ገቢ በ2006 ዓ.ም ከነበረውም ያልተለየ፣ ከዚህ ገቢ የተገኘው የገቢ ንግድ (import) ወጪን የመሸፈን አቅሙም በ2007 ዓ.ም ከአለፈው ጊዜ ያነሰ ነው ያለው ሰነዱ፤ በወጪ ንግድ ገቢ (export) ወጪ እና በገቢ ንግድ ((import) ወጪ ያለው ክፍተትና ጉድለት እየሰፋ መጥቶ በ2007 ዓ.ም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ብሏል፡፡ የታየው ደካማ የውጭ ንግድ አፈፃፀም አስተማማኝ የውጭ ምንዛሬ በማግኘት ኢኮኖሚውን ለማሳደግ፣ ከውጭ ብድርና እርዳታ ጥገኝነት ለመላቀቅ ለሚደረገው ጥረት ማነቆ እንደሆነ በሰነዱ ላይ ሰፍሯል፡፡

የውጭ ንግድ መዳከም የውጭ ምንዛሬ ለሚፈልጉትና አቀድኳቸው ላላቸው የመሰረተ ልማት፣ የኢንዱስትሪና የማህበራዊ ልማት እንዳይሳኩ እየፈጠረው ያለው እንቅፋት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ብሏል፡፡ ለውጭ ገቢ ንግድ መዳከም በዋነኛነት የማምረት አቅም አለማደግ፣ የማኑፋክቸሪንግና የግብርና ሸቀጦች በመጠን፣ በአይነትም፣ በጥራት ማምረት አለመቻሉ እንደሆነ በሰነዱ ላይ ተገልፆአል፡፡

eprdfs economic policyበትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ መጨረሻ ለውጭ ገበያ ይቀርባል ተብሎ የነበረው ቡና ሩብ ያህሉን እንኳን ማቅረብ አልተቻለም ያለው ሰነዱ በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ መጨረሻ ለውጭ ገበያ ይቀርባሉ ተብሎ የነበሩት የአበባ፣ የጨርቃጨርቅና የቆዳ ምርቶችም በቡና ገበያ ላይ ከታየውም በላይ ክፍተት እንደነበረበት በዝርዝር አስቀምጧል፡፡

ሰነዱም “በግብርና ዘርፍ የኤክስፖርት ሰብሎች የሆኑት አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ቡና፣ ሰሊጥና የጥራጥሬ ሰብሎች ሲሆኑ ለውጭ ገበያ የቀረበው መጠን ይደረጋል ተብሎ ከታቀደው በእጅጉ ያነሰና በማኑፋክቼሪንግ ነባር ኢንዳስትሪዎችና በከፍተኛ አቅማቸውና በጥራት እንዲያመርቱ፣ በተጨማሪም አዳዲስ ኢንቨስትመንትን በስፋትና በጥራት መልምሎ ወደ ሥራ ማስገባት በታቀደው ልክ ሊፈፀም ባለመቻሉ ለወጪ ንግድ የማምረት አቅማችን ዝቅተኛ መሆኑን ዋና ምክንያቶች ነበሩ” ብሏል፡፡

መንግስት በታክስ አሰባሰብም ትልቅ ክፍተት እንዳለበት ያመነው ሰነዱ “ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት አማካይ አፈፃፀም ለመድረስ በታክስ አስተዳደርና አሰባሰብ ተጨማሪ ጥረት ማደረግ እንዳለብን ያመለክታል፡፡ መሰብሰብ የሚችለው የታክስ ገቢ አለመሰብሰቡ መስራት የሚቻለውን ያህል የልማት ሥራ በዛው ልክ ሳይሰራ ቀርቷል ማለት እንደሆ ከልብ ሊጤን ይገባዋል” ብሏል፡፡


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Filed Under: Opinions, Politics Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule