• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሠራተኛውን ማን አቃጠለው?

October 14, 2015 07:29 pm by Editor 2 Comments

የጎልጉል እማኝ ዘጋቢ (ireporter) ከጥቂት ቀናት በፊት በአፋር ክልል ሃዳር ወረዳ ኤሊ ውሃ ከተማ ቅዳሜ መስከረም 22፤2008 ዓም ስለተፈጸመው ግድያ መረጃ ልከውልናል፡፡

ከመረጃ አቀባያችን ጋር በተደጋጋሚ በተላላክነውና ባቀረብነው በርካታ ጥያቄዎች መሠረት ያገኘነው መረጃ ይህንን ይመስላል፡-

እጅግ ዘግናኝ የሚባለው ግድያ የተፈጸመው ከላይ በተጠቀሰው ሥፍራ በሚገኘው የቻይና መንገድ ሥራ ፕሮጀክት እየተባለ በሚጠራው ግቢ ውስጥ ነው፡፡ የእማኝ ዘጋቢው በራሳቸው አገላለጽ እንዲህ ዘግበውታል፡- (የላኩልን የእንግሊዝኛ ፊደላትን በመጠቀም ሲሆን ወዳማርኛው እንዲህ መልሰነዋል)

“ወንጀሉ የተፈጸመው ቅዳሜ መስከረም 22፤2008 ዓም በአፋር ክልል ሃዳር ወረዳ በኤሊውሃ ከተማ ግቢ ተብሎ በሚጠራው የቻይና መንገድ ሥራ ፕሮጀክት ውስጥ ነው፡፡ የተቃጠለው ልጅ ወልዱ ይባላል፡፡ በ(ፕሮጀክቱ) የላቦራቶሪ ሠራተኛ ነበር፡፡ ሟች ወጣት ወልዱ በላቦራቶሪ ክላስ ውስጥ ቤንዚን እየቀዳ ነበር፡፡ ብዛት ያላቸው የቤንዚን ጄሪካኖች ነበሩ፤ አለቃው ቻይናዊ ይመጣና ሲጋራ ወደ ቤንዚኑ ይወረውራል፤ ከዚያ በኋላ ምን እንደተከሰተ ግልጽ ነው፤ ሙሉ ቤቱ ነደደ፡፡ ቻይናዊው እየሮጠ ወጥቶ ቤቱን አውጭ ዘጋው፤ በቃ ወጣት ወልዱ አይሞቱ ሞት ሞተ፤ እርር፣ ክስል ብሎ በቁሙ ዓይኑ እያየ አንዳች እርዳታ ሳያገኝ ተቃጥሎ ሞተ፡፡ ከዚህ በኋላ ሬሳውን ይዘው ምርመራ ቤተሰብ ፍለጋ እያሉ ለ4 ቀን ካንከራተቱት በኋላ መልሰው እዚያው ኤሊ ውሃ ከተማ ቤተሰቦች በሌሉበት ተቀበረ፤ ወንጀሉን የፈጸመው ቻይናዊ ግን እስካሁን ለፍርድ አልቀረበም፡፡ ምክንያቱም የወረዳው መንግሥት ብቻ ነው የሚያውቀው፡፡”

ይህ ከደረሰን በኋላ የእማኝ ዘጋቢውን ተጨማሪ ዝርዝር ለማግኘት ጥያቄዎችን አንስተን ነበር፡፡ በጥያቄያችን መሠረትም የሟችን የተቃጠለ ምስልና ከመሞቱ በፊት ያለውን ምስሉን የሚያሳይ ሁለት ፎቶዎች ልከውልናል፡፡ የተቃጠለው ሬሣ እጅግ ዘግናኝ ከመሆኑ ባሻገር ማንነቱ ጠፍቶ ለመለየት በሚያስቸግርበት ሁኔታ ከሌላ ወገን ማረጋገጥ የሚቻል ባለመሆኑ ከሁሉ በላይ ግን መሞቱ በቤተሰቡ ዘንድ የታወቀ ባለመሆኑ ይፋ ከማድረግ ተቆጥበናል፡፡ ሆኖም አሁንም ይህ መረጃ አቀባዩ በራሳቸው አነሳሽነት የላኩት የእማኝ ዘገባ በመሆኑ ላቀረብናቸው ተጨማሪ ጥያቄዎች የላኩት ምላሽ በአጭሩ ይህንን ይመስላል፡-

“ወጣት ወልዱ የተባለው ሟች የአፋር አፈር (soil) ላቦራቶሪ ሠራተኛ ነው፡፡ ለላቦራቶሪ ሥራ የሚጠቀምበትን ማሽን የሚያንቀሳቅስው ቤንዚን በመጠቀም ነው፤ እሱን በዚህ ሥራ የተሰማሩ ባለሙያዎች የበለጠ ማብራሪያ መጠየቅ ይቻላል፤ እናም ለዚህ ሥራ የሚጠቀምበት የሚበቃውን ያህል ለመቅዳት በቤንዚን ክፍል ውስጥ እያለ ነው ይህ አረመኔ ቻይናዊ ወደሱ መጥቶ ወደ ውስጥ በመግባት ሲያጨስ የነበረውን ሲጋራ በመወርወር አደጋው የተፈጠረው፡፡ የቤተሰቡን ጉዳይ እስካሁን ለማወቅ አልተቻለም፤ የትግራይ ክልል ተወላጅ እንደሆነ ብቻ ነው የሚታወቀው፡፡ እናም ሬሣውን እስከ መቀሌ ከተማ ድረስ ወስደው ለማጣራት ሙከራ አድርገናል ነው የሚሉት ግቢው ውስጥ የሚገኙ የፌዴራል ፖሊሶች፡፡ ግን መሞቱን ለማሳወቅ ያደረጉት እንቅስቃሴ በጣም አነስተኛ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ከቻይናዎች አንድ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ሲጠፋቸው (ፖሊሶቹ) አሳድደው አዲስ አበባ ውስጥ ሊያዝ ችሏል፤ እና ይህንንም ጉዳይ ቢያስቡበት ቤተሰቦቹ ማግኘት ይችላሉ ብዬ እገምታለሁ፡፡”

ወንጀሉን የፈጸመው አለቃው ስም ማን እንደሆነ የእማኝ ዘጋቢው ሲናገሩ በራሳቸው አገላለጽ “wenjelun yefetsemew aleqaw yehoneaw Mr Waan yetebale chinawi neaw” (“ወንጀሉን የፈጸመው አለቃው ሆነው ሚስተር ዋን የተባለ ቻይናዊ ነው፡፡”) በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ይህ የእማኝ ዘጋቢው መረጃ ሲሆን ጎልጉል በሥፍራው ዘጋቢ ስለሌለው በቦታው የሚገኙትን ባለሥልጣናት በግምባር ለማነጋገር አልቻለም፡፡ ሆኖም ግን ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተውን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ምላሽ እንዲሰጥ ሞክረን ስልኩ ሳይነሳ በመቅረቱ መረጃ ለማግኘት አልተቻለም።

ሞተ የተባለውን ወጣት የሚያውቁ ቤተሰቦችም ሆኑ የቅርብ ወዳጆች በዚህ ጉዳይ ላይ ምላሽ እንዲሰጡ እንጠይቃለን፡፡ እንደሚዲያ እኛ ከእማኝ ዘጋቢ ያገኘነውን አቅርበናል፤ ዜናው የመረጃ አቀባዩ ነው፤ ሆኖም ግን በሰብዓዊ መብቶች ላይ የሚሠሩ ድርጅቶች እና የሕዝብ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ሁሉ ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ሁኔታውን ማጣራትና ዳር ማድረስ ይጠበቅባቸዋል፡፡ አሠሪ የተባለው መሥሪያቤትም ይህንን የመመርመርና የተባለው ቻይናዊ ወንጀለኛ ከሆነ ለፍርድ የማቅረብ ከፍተኛ ኃላፊነት አለበት፡፡ “ዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን” የዜጎችንም ህይወት የሚመለከት ይመስለናል፡፡

ጎልጉል የእማኝ ሪፖርተሮች ያሉት ሲሆን በነዚሁ ምንጮቹ አማካይነት መረጃ ለህዝብ ሲያቀርብ የቆየ መሆኑ የሚታወቅ ነው። ለዚህም ነው “ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ ነው” የምንለው፡፡ ይህ ዜና ክዘግናኝነቱ ባሻገር ከጀርባው ልዩ ሚስጥር እንደሚኖረው ስለሚታመን ዜናው የሚመለከታችሁ ወገኖች ምላሽም ይሁን ማስተባበያ እንዲሰጡ እንማጸናለን።


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News, Opinions, Social Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Abe says

    October 18, 2015 06:31 pm at 6:31 pm

    This is so shocking and terrifying news beyond one’s human absorb and imagination to live with. Never such type of crime committed in Ethiopia before except by the then Fascist Italy during its Colonial Invasion Attempt in 1935-1940. Are the Chinese our modern day colonizers and have the right to decide on our living and life beyond their economic involvement? Its great shame to our country, people, and above all, to our “Government”. How can a bilateral relationship with China continues while this type of atrocity is going on our citizens? What is the value of so called “Development” while you are exposing your people to such horrendous acts and dreadful situations.
    After all, the Chinese are not investing nor providing relief or development aid to Ethiopia. They are simply loaners of their surplus with steep interest rate and labour contract (hiring their citizens) attached to it.
    We have to rise, stand up , fight and speak louder for our rights (at least for our natural rights). We need to make and force our leaders to be accountable and responsible. Otherwise, we keep on living in such abominable situation and lead undignified life and death. We also lose our country slowly to “Chinese Imperialism”to use the words of Alberto Acosta, former Ecuador Energy Minister.

    Reply
  2. Belhu says

    November 29, 2015 07:39 pm at 7:39 pm

    በቤንሻንጉል ክልል በሐሰት የትምሕርት ማስረጃ በመያዝ (በተለየ ከሰሜን ኢትዮጲያ የመጡ) URRAP በሚባል የገጠር መንገድ ስራ ፕሮጀክቶች በመደራጀት ኢንጅነር በመባል ሚሊዮኖችን እየዘረፉ ይገኛሉ:: መረጃውን ለሚመለከተው አድርሱልን::

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “ዛሬ ‘ኃያል ነን’ የሚሉ ሀገራት ኢትዮጵያ ላይ በሚዲያ /በመረጃ/፣ በዲፕሎማሲ፣ በሳይበር እና በተልእኮ የተቀነባበረ ‘ግራጫ ጦርነት’ እያካሄዱባት ነው” ጠ/ሚ ዐቢይ July 7, 2022 10:03 am
  • የኦሮሞ ልሂቃንና ፖለቲከኞች በአማራ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለውን “የዘር ማጥፋት” ወንጀል እንዲያወግዙት አብን ጠየቀ July 6, 2022 01:38 pm
  • “አማራን ኦሮሚያ ውስጥ የመግደል እና የመጨፍጨፍ እቅድ የኦነግ ሳይሆን የኦሮሚያ ብልጽግና ነው” አቶ ሃንጋሳ July 6, 2022 01:53 am
  • “በኢትዮጵያዊያን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ሀገሪቱን ማተራመስ አለብን” አይማን አብድልአዚዝ ግብጻዊው ፖለቲከኛ July 5, 2022 12:57 pm
  • ባልደራስ የአገርን ደኅንነት አደጋ ላይ በመጣል ሊጠየቅ ይገባዋል ተባለ July 1, 2022 09:23 am
  • “ሚካኤል ችግኝ ነው። … ችግኝ ይተክላል” ቴዲ አፍሮ June 29, 2022 03:30 am
  • “የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች (22ቱንም) የቀበርኩት እኔ ነኝ” አቶ መሀመድ የሱፍ ከምዕራብ ወለጋ June 28, 2022 01:07 pm
  • የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ June 20, 2022 11:34 pm
  • “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል June 12, 2022 07:09 pm
  • የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው June 12, 2022 06:21 pm
  • ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል June 12, 2022 05:40 pm
  • የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ June 12, 2022 05:35 pm
  • በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ June 10, 2022 09:13 am
  • ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት June 8, 2022 12:59 pm
  • ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር June 8, 2022 11:53 am
  • እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ? June 8, 2022 05:59 am
  • ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ June 7, 2022 01:11 am
  • “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ” June 5, 2022 06:58 pm
  • በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ May 30, 2022 02:20 am
  • የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ May 29, 2022 04:01 pm
  • “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!” በሚል ቁጭት ነው እየሠራን ያለነው May 29, 2022 01:04 pm
  • “ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መርህ ለአማራ ገበሬዎች የግብርና ሜካናይዜሽን ተሰጠ May 29, 2022 02:02 am
  • ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል May 27, 2022 02:51 am
  • “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ May 27, 2022 01:40 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule