• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ቅጥ ላጣው ሙስና “ተጠያቂ ነኝ” – ህወሃት

October 8, 2015 07:28 am by Editor 1 Comment

ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም እየገዛ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር – ህወሃት በተለይ በአዲስ አበባ ቅጥ ያጣውን ሙስናና ዘረፋ በተመለከተ በጠራው ስብሰባ አስቀድሞ በመቀሌው “ተጠያቂ ነኝ” በማለት እንዳመነው አሁን ደግሞ ነዋሪው ችግሩን ራሱ እንዳመጣው ራሱ ይፍታው ማለቱ ተነግሮዋል:: የሪፖርተር ዘገባ እነሆ:-

* ሙስና በአዲስ አበባ በኔትወርክ ተይዞዋል

ሙስና፣ ኪራይ ሰብሳቢነትና የመልካም አስተዳደር እጦት ከወረዳ እስከ ከተማ አስተዳደሩ ድረስ በኔትወርክ የተያያዙ በመሆናቸው ሊፈታቸውም ሆነ ሊያስቆማቸው የሚችለው ድርጅቱ ኢሕአዴግ ብቻ መሆኑ ተጠቆመ፡፡

የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን መስከረም 20 ቀን 2008 ዓ.ም. በግዮን ሆቴል ለግማሽ ቀን አዘጋጅቶት በነበረው የውይይት መድረክ ላይ ከተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት፣ የሁሉም ክፍላተ ከተሞች፣ ወረዳዎች ተወካዮችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተው ነበር፡፡ ተሳታፊዎቹ እንደተናገሩት የመልካም አስተዳደር እጦት፣ ሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነት በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ በከፍተኛ ሁኔታ ተባብሶ ቀጥሏል፡፡

በመጠናቀቅ ላይ ካለው መስከረም ወር አጋማሽ ጀምሮ በሁሉም ክፍላተ ከተሞች ሊባል በሚችል ሁኔታ ከግንባታ፣ ከመሬትና ቤቶች ጋር በተገናኘ ነዋሪዎች እያለቀሱ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የመድረኩ ተሳታፊዎች በተለይ በአዲሱ የሥራ ዘመን ከኃላፊነታቸው እንደሚነሱ ያወቁ፣ የጠረጠሩና ሹክሹክታ የሰሙ የክፍላተ ከተሞችና የወረዳዎች ተሿሚዎች “የሚፈርስ የማይፈርስ፣ መንገድ የሚወጣበት የማይወጣበት፣ ክርክር ያለበት የሌለበት፣ ግንባታ የተፈቀደለት ያልተፈቀደለት…” በማለት በሥራ ሰዓትና ከሥራ ውጪ የነዋሪዎችን ግድግዳና የውጭ በር ቀለም ሲቀቡ እንደሚውሉ ጠቁመዋል፡፡ ያለምንም ማስጠንቀቂያ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ኅብረተሰቡን ሰላም እየነሳው በመሆኑ፣ የአስተዳደሩና የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎች ትኩረት ሰጥተው ሊያስቆሟቸው ወይም ዕርምጃ ሊወስዱባቸው እንደሚገባ ተሳታፊዎቹ አሳስበዋል፡፡

በመቀሌ ከተማ በተደረገው የገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ አሥረኛ ጉባዔ በመጀመሪያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ጥሩ ሥራ መሠራቱ የተገለጸ ቢሆንም፣ በመልካም አስተዳደር በኩል ግን ከፍተኛ ችግር እንደነበር መታመኑንና ፓርቲው “ተጠያቂ ነኝ ማለቱን”፣ የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዓሊ ሱሌይማን ለተሳታፊዎች አስታውሰዋል፡፡ በመቀጠልም ይህንን ምቹ ሁኔታ ሕዝቡ መጠቀም ስላለበት ከመንግሥት ጎን በመቆም ብልሹ አሠራርን፣ ሙስናንና ሌሎች ለሕዝቡም ሆነ ለአገር የማይጠቅሙ አሠራሮችንና ድርጊቶችን ማጋለጥ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

በየስብሰባው በመወዳደስና በጭብጨባ በመደጋገፍ መንቀሳቀስ መቆም እንዳለበትና ሕዝብ ያስቀመጠው ኃላፊ ለሕዝብ ማገልገል እንዳለበት መንገር ያለበት ኅብረተሰቡ መሆኑን የገለጹት ኮሚሽነሩ፣ በየስብሰባው የጉንጭ ጅምናስቲክ ሠርቶ መለያየትን ቆም አድርጎ ባለሥልጣኑ የሚጓዝበት ተሽከርካሪ፣ የሚኖርበትና የሚከፈለው ደመወዝ ሕዝቡ በሚከፍለው ታክስ መሆኑን በመግለጽ፣ በአግባቡ እንዲያገለግለው መናገር እንዳለበት አስታውቀዋል፡፡

የኮሚሽነሩን ማብራሪያ ተከትሎ የመድረኩ ተሳታፊዎች እንደገለጹት፣ ኮሚሽኑ የመንግሥት ተሿሚዎች የሕዝብ ሀብት በሙስናና በኪራይ ሰብሳቢነት እንዳይበዘብዙና መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን በማለት የሕዝብ ተሿሚዎች ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ማድረጉ ትልቅ ነገር ነበር፡፡ ነገር ግን በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ የመንግሥት ተሿሚዎች መመዝገባቸው ከመገለጹ ውጪ ለሕዝቡ ይፋ አልተደረገም፡፡ ተመዝግቦ በድብቅ መያዙ ትርጉም ስለሌለው የትኛው ባለሥልጣን ምን ያህል ሀብት እንዳስመዘገበ ለሕዝብ ይፋ መደረግ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ ለሕዝብ ይፋ መደረጉ ሕዝቡ የሚያውቀውን ያህል ማስመዝገቡንና ያላስመዘገበም ከሆነ ተጨማሪ መረጃ በመስጠት እውነቱ ላይ እንዲደርስ እንደሚረዳ ተሳታፊዎች አውስተዋል፡፡

ሀብታቸውን ያስመዘገቡ ባለሀብቶች ይፋ እንዲደረጉ በተነሳው ጥያቄ ላይ ምላሽ የሰጡት ኮሚሽነር ዓሊ፣ መሥሪያ ቤታቸው ለማንም ክፍት መሆኑንና ማንም መጥቶ የሚፈልገውን ማስረጃ ማግኘት እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ መረጃ የሚፈልግ ማንኛውም ዜጋ ደብዳቤ ጽፎ፣ “የእከሌን ባለሥልጣን ሀብት ማወቅ እፈልጋለሁ?” ካለ ወዲያውኑ እንደሚገለጽለት ተናግረው፣ በመገናኛ ብዙኃን ግን “የእከሌ ባለሥልጣን ሀብት ይህንን ያህል ነው፤” ብሎ ይፋ ማድረግ ከሕግ አንፃርም እንደሚያስኬድና ነውር መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡ በዓለም ደረጃም ከሲንጋፖር በስተቀር የሁሉንም ዜጎች ሀብት መዝግቦ ይፋ ያደረገ አገር አለመኖሩን አክለዋል፡፡ በቅርቡ በኮሚሽኑ ድረ ገጽ በኢሜይል መጠየቅና መረጃ ማግኘት እንደሚቻልም ጠቁመዋል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊዎች በርካታ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን፣ በተለይ በሙስና ተጠርጥረው ስለሚታሰሩና ስለሚፈረድባቸው ተከሳሾች ተናግረዋል፡፡ አንድ በሙስና የተጠረጠረ ሰው በርካታ ገንዘብ በሙስና ካገኘ በኋላ ዘመዶቹ ዘንድ በታትኖ በማስቀመጥ፣ ሲፈተሽ የሚገኝበት ጥፋት በጣም ትንሽ ስለሚሆን የተወሰነ ዓመት ታስሮ እንደሚፈታ ገልጸዋል፡፡

ከእስር እንደተፈታ ለተወሰኑ ወራት ቀድሞ ከሚኖርበት አካባቢ በመልቀቅ ከቆየ በኋላ አስመጪና ላኪ ሆኖ እንደሚታይ የገለጹት ተሳታፊዎቹ፣ ይህንን የሚያዩ ተሿሚዎች የተወሰኑ ዓመታት ታስረው ለራሳቸውና ለቤተሰባቸው እንደሚተርፉ ራሳቸውን በማሳመን ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ ሀብትን እየበዘበዙ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይህንን ተግባር የሚመለከተው አካል ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ዕርምጃ ሊወስድበት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ሙስናን የሚፀየፍ ትውልድ ለመፍጠር ትምህርቱ ከአምስት ዓመት ሕፃን እንዲጀምር በኮሚሽኑ የቀረበውን ሐሳብ የውይይቱ ተሳታፊዎች ድጋፍ ሰጥተውታል፡፡

በመቀሌው ጉባዔ የተደረገው ስምምነት እንዳለ ሳይቀነስ ወደ ታች መውረድ እንዳለበት ያሳሰቡት የውይይቱ ተካፋዮች፣ በተለይ ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ዕጦት በሚታይባቸው ግብር አስከፋይና ንግድ ፈቃድ አዳሽ መሥሪያ ቤቶች የማይተገበር መመርያ እያወጡ የንግዱን ኅብረተሰብ ሳይወድ በግድ ወደ ሙስና እንዲገባ የሚያደርጉበት አሠራር ትኩረት እንዲሰጥበት ጠይቀዋል፡፡ የመልካም አስተዳደርና የፍትሕ ዕጦት ቢስተካከል ለውጥ ሊመጣ እንደሚችልም አክለዋል፡፡

“ድርጅቱ ይታማል” ያሉ አንድ አስተያየት ሰጪ፣ ተሿሚው እንክት አድርጎ ከበላ በኋላ እሮሮ ሲበዛበት ከነበረበት ቦታ ወይም ክፍለ ከተማ ተነስቶ ወደ ሌላ ክፍለ ከተማ ወይም ማዘጋጃ ቤት እንደሚሾም ገልጸው፣ “እርስዎ (አቶ ዓሊን) ለድርጅቱ ቅርብ ስለሆኑ ቢወያዩበትና መፍትሔ እንዲመጣ ቢያደርጉ የተሻለ ነው፤” ማለታቸው የስብሰባውን ተሳታፊዎች አስፈግጓል፡፡ ከድርጅቱ ውጪ ማንም ሊፈታው እንደማይችልም አክለዋል፡፡ የብሔር ብሔረሰቦችን ችግር የሚፈታ መንግሥት እንዴት የሙስናን ችግር መፍታት እንዳቃተው እንዳልገባቸውም ተናግረዋል፡፡

ገዢው ፓርቲ ብቻውን የሚያደርገው ነገር እንደሌለ የገለጹት አቶ ዓሊ፣ የኅብረተሰቡ ተሳትፎ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ በእርግጥ አንዳንድ ድርጊቶችን ማስፈጸም እንዳልተቻለ የገለጹት አቶ ዓሊ፣ የማይገባ ድርጊት መፈጸሙ እየታወቀ ዞር ተደርጎ በከፍተኛ ደረጃ የሚሾም ተሿሚ መኖሩንም ጠቁመዋል፡፡ (ሪፖርተር)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News, Politics Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. በለው ! says

    October 9, 2015 08:48 am at 8:48 am

    ‹‹በየስብሰባው እየተወዳደሱና በጭብጨባ እየተደጋገፉ መለያየት ይቁም››
    >>> ማነው ያለው? ገና ከጥላቻ ፖለቲካ የፀዳ በመደናነቅና በማወደስ ላይ የተመሠረተ ከተደጋፊ/ደጋፊ፣ አጋር ፓርቲዎች፣ ሌላ በተለየ መልኩ ሶስተኛ አማራጭ ተፈጥሮ የለምን!?
    በቀድሞው የደርጋዊ ስሟ ከትልቅ የኩታ ጋቢ፣ እስከ ስልቻ እህልና ፭ሺህ ብር የማትሞላ ጉቦ ትባል ነበር። በልማታዊው ህወአት/ኢህአዴግ ሙስና ሺህ ቤትን ዘላ ሚሊየን ድርስ የገባች ዘመነኛ ትስስር ፈጣሪ በልቶ ማባላት ናት! ይኸው ሙስና መር አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት “ኪራይ ሰብሳበቢ” የተሰኘ ሚኒስትር መ/ቤት ዘርፍ አበጀለት ለመሆኑ ምንድነው?
    ይቺ የሚዘመርና የሚዜምላት ክራይ ሰብሳቢ ማናት? ሕዝቡ ቃል እንደበቀቀን የሚደግመው ፈሊጥ ሆኖ ነው?
    (ሀ)የሚከራይ ነገር (የገንዘብ ምንጭ)መኖር አለበት (ለ) አከራይ ጉዳዩ የሚመለከተው ቡድን(መንግስት ፓርቲ)አለ (ሐ) የሚከራየው ቦታ/ዕቃ/በቡድንም(ብሔርም ሊሆን ይችላል) (መ) የሚከራየው ባለቤት (በቡድንም ይሁን በሥልጣን)የተሳሳረ ይኖረዋል (ሠ) የሚከራየውን ነገር/ቦታ (አስተዳዳሪ/ጠባቂ) አለ (ረ) ይህንን ለማከራየት ደላላ (ጠቋሚ)ያስፈልጋል (ሠ) የአከራይ ተከራይ አዋዋይ(ጥቅማጥቅመኛን የሚያበላ) አለ (ረ) የውል ፊርማ ታዛቢ (አስፈፃሚ ባለድርሻ) አለ (ሰ) ተከራይ/አካራይ ግብር(ለሌላው ማብላት) ስለመክፈሉ ማረጋገጫ ሰጪ አካል አለ (ሸ) የተከራይነት ማስረጃ ከበላይ አካል (እውቅና)ስለማግኘቱ ምልክት ሰጪ አለ፡ ወ.ዘ.ተ ይሀና ሌሎችንም ደፍኖ ኪራይ ሰብሳቢ ይባልልኛል!?….አለበለዚያ በጥቅም ተጋሪ በአንድ ጥላ ሥር በተሰባሰበ ሞኖፖል ተይዟል ማለት ነው።
    ፩)ለምሳሌ ቀጥሎ ያለው ኪራይ ሰብሳቢ አደለም! (የሥራ አስፈጻሚው)አካል ነው።
    “በአዲሱ የሥራ ዘመን ከኃላፊነታቸው እንደሚነሱ ያወቁ፣ የጠረጠሩና ሹክሹክታ የሰሙ የክፍላተ ከተሞችና የወረዳዎች ተሿሚዎች ‹‹የሚፈርስ የማይፈርስ፣ መንገድ የሚወጣበት የማይወጣበት፣ ክርክር ያለበት የሌለበት፣ ግንባታ የተፈቀደለት ያልተፈቀደለት…›› በማለት በሥራ ሰዓትና ከሥራ ውጪ የነዋሪዎችን ግድግዳና የውጭ በር ቀለም ሲቀቡ እንደሚውሉ ጠቁመዋል፡፡”
    ፪) ያልተተነተነው ‘ኪራይ ሰብሳቢ’ በሞኖፖል ደረጃ በፓርቲው ጥላ ሲዋቀርና ሲታቀፍ፡
    “አንድ በሙስና የተጠረጠረ ሰው በርካታ ገንዘብ በሙስና ካገኘ በኋላ ዘመዶቹ ዘንድ በታትኖ በማስቀመጥ፣ ሲፈተሽ የሚገኝበት ጥፋት በጣም ትንሽ ስለሚሆን የተወሰነ ዓመት ታስሮ እንደሚፈታ ከእስር እንደተፈታ ለተወሰኑ ወራት ቀድሞ ከሚኖርበት አካባቢ በመልቀቅ ከቆየ በኋላ አስመጪና ላኪ ሆኖ እንደሚታይ የገለጹት ተሳታፊዎቹ፣ ይህንን የሚያዩ ተሿሚዎች የተወሰኑ ዓመታት ታስረው ለራሳቸውና ለቤተሰባቸው እንደሚተርፉ ራሳቸውን በማሳመን ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ ሀብትን እየበዘበዙ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
    ፫) መንግስታዊ እውቅና የተሰጠው ‘ኪራይ ሰብሳቢ’ የቡድን መሪ ሲሆን ስለልማታዊ መንግስት በባዶ ሜዳ ሲያስጮህ ፡
    “ተሿሚው እንክት አድርጎ ከበላ በኋላ እሮሮ ሲበዛበት ከነበረበት ቦታ ወይም ክፍለ ከተማ ተነስቶ ወደ ሌላ ክፍለ ከተማ ወይም ማዘጋጃ ቤት እንደሚሾም ይደረጋል። አዲስ አባባን በሙስና ኔትወርክ(በሞኖፖል)የሚያስተዳድረው ህወአት/ኢህአዴግ “ተጠያቂ ነኝ!”ብሎ አምኗልና እራሱ እንደፈጠራቸው እራሱ ጅቦቱን ይሰር!ያጥፋ! ይቺ ናት’ ያዢ ያጣች ሀገር’ ዘመነኛው ደርግ ጉቦና ሙስና!ከርሞ ጥጃ በጣም ያሳፍራል! ያሳዝናል!ያስቆጫል !። ለሁሉም ግዜ አለው በለው!በቸር ይግጠመን

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ባልደራስ የአገርን ደኅንነት አደጋ ላይ በመጣል ሊጠየቅ ይገባዋል ተባለ July 1, 2022 09:23 am
  • “ሚካኤል ችግኝ ነው። … ችግኝ ይተክላል” ቴዲ አፍሮ June 29, 2022 03:30 am
  • “የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች (22ቱንም) የቀበርኩት እኔ ነኝ” አቶ መሀመድ የሱፍ ከምዕራብ ወለጋ June 28, 2022 01:07 pm
  • የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ June 20, 2022 11:34 pm
  • “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል June 12, 2022 07:09 pm
  • የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው June 12, 2022 06:21 pm
  • ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል June 12, 2022 05:40 pm
  • የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ June 12, 2022 05:35 pm
  • በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ June 10, 2022 09:13 am
  • ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት June 8, 2022 12:59 pm
  • ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር June 8, 2022 11:53 am
  • እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ? June 8, 2022 05:59 am
  • ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ June 7, 2022 01:11 am
  • “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ” June 5, 2022 06:58 pm
  • በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ May 30, 2022 02:20 am
  • የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ May 29, 2022 04:01 pm
  • “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!” በሚል ቁጭት ነው እየሠራን ያለነው May 29, 2022 01:04 pm
  • “ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መርህ ለአማራ ገበሬዎች የግብርና ሜካናይዜሽን ተሰጠ May 29, 2022 02:02 am
  • ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል May 27, 2022 02:51 am
  • “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ May 27, 2022 01:40 am
  • ትግራይን አገር እናደርጋለን፤ “በውይይት እና በጦርነት” ሁሉንም ጉዳይ እንቋጫለን – የወንበዴው መሪ ደብረጽዮን May 26, 2022 09:18 am
  • “ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ተዋጊ ዶክተሮች” May 26, 2022 08:19 am
  • ወደ ትህነግ ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ May 25, 2022 01:57 am
  • የጦርነቱ ስትራቴጂያዊ እውነታዎች May 19, 2022 09:37 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule