ሰው በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ነው፤ ሕይወቱ ክቡር ነው፤ ክቡር ሕይወቱን ለመጠበቅ ብዙ ፍላጎቶቹን ማሟላት አለበት፤ አንዳንዶቹ ፍላጎቶች በየዕለቱ የሚከሰቱና የሚጎተጉቱ ናቸው፤ ስለዚህም ወዲያው ካልተስተናገዱ በጤንነት ላይ መጥፎ ውጤትን ያስከትላሉ፤ምግብና መጠጥ ግዴታዎች ናቸው፤ ልብስና መጠለያም ግዴታዎች ናቸው፤ ሰው ሁሉም ነገር ከተሟላበት ከገነት ከተባረረ በኋላ በግንባርህ ላብ ብላ ተብሎ ተረግሟል፤ በሰላም በሕግ ጥላ ስር የመተዳደር ፍላጎትም አለ፤ በአለው አቅምና ችሎታ አነዚህን ፍላጎቶች ለማሟላት ይጥራል፤ ይህ ቀላል አይደለም፤ ቀላል የማያደርጉት ብዙ ምክንያቶች አሉ። አንደኛ፣ የሰውም፣ የእንስሳም፣ የእጸዋትም ሁሉ መኖሪያና መመገቢያ ምድር አንድ ነች፤ ስለዚህ ውድድሩ ከባድ ነው፤ በዚች ምድር ላይ እየኖሩ፣ ምድር የምታፈራውን እየተመገቡ፣ ውሀዋን እየጠጡ በሰላም መኖር … [Read more...] about ሰውና ልማት
Archives for July 2014
በውጭ ያለነው ኢትዮጵያዊያን ምርጫዎች አሉን
ዛሬም እንደሳምንቱ መብታችንን እያሉ ኢትዮጵያዊያን በየመስጊዱ ተሰብሰበዋል። በየቀኑ በየቤተክርስትያኑ ጸሎታቸውን ያደርሳሉ። በየትምህርት ቤቱ በራቸው ተንኳኩቶ እንዳይወሰዱ ተደብቀው ያጠናሉ። መምህራን በፍራቻ፤ ለተማሪዎቻቸው ሳይሆን ለካድሬዎቹ ይሽቆጠቆጣሉ። አርሶ አደሮች ለሚያርሱበት መሬት፣ ለማዳበሪያና ለካድሬ ሲሉ አንገታቸውን ደፍተዋል። ላብ አደሮች የሥራ ዋስትና አንገታቸውን አንቆ ወገባቸውን አጉብጦታል። ነጋዴዎች ከኤፈርት ጋር ውድድሩ ራቁታቸውን አስቀርቷቸዋል። ጋዜጠኞች ዓይኖቻችሁን ጨፍናችሁ እኔ የምላችሁን ካላደረጋችሁ ተብለው እስር ቤቱን ሞልተውታል። ማን ተርፎ? የፖለቲካ ምኅዳሩን ማነቆ የጨበጠው መንግሥት አምልኩኝ ብሏል። ሀገራችን ባለችበት የፖለቲካ ሀቅና እኛ አሁን ባለንበት ድንዘዛ፤ አንድ የሚያነቃ ብራቅ ብልጭ ሊልብን ይገባል። የአንድነት ውይይት የግድ ነው። ይቺ ሀገራችን … [Read more...] about በውጭ ያለነው ኢትዮጵያዊያን ምርጫዎች አሉን
ምርቃት ወዲህ ሥራ ወዲያ
አሁን ላይ በሐገራችን የተገነቡና እየተገነቡ ያሉ ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ደረጃዎች የሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶች ቁጥር ጨምሯል፡፡ በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርትን በነባርና አዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች በኩል ትምህርታቸውን ተከታትለው እየተመረቁ የሚወጡ ተማሪዎች (ምሩቃን) ቁጥር በዚያው ልክ እያደገ ይገኛል፡፡ በዚህ አመት ብቻ እንኳ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የተመራቂዎች ቁጥር ከ60 ሺህ በላይ እንደሆነ ይፋ ሆኗል፡፡ ይህ ቁጥር በግል ኮሌጆችና በተለያዩ መለስተኛ የትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን የተከታተሉትን አይጨምርም፡፡ የትምህርት ተቋማትም ሆነ በእነዚህ ተቋማት ገብተው ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ተማሪዎች ቁጥር መጨመሩ ይበል የሚያሰኝ እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ዳሩ ግን እነዚህ ተማሪዎች በምን ሁኔታ ትምህርታቸውን ተከታትለው እንደሚወጡ ሲታይና ከምረቃ በኋላም ያለውን የሥራ ጊዜ … [Read more...] about ምርቃት ወዲህ ሥራ ወዲያ
ተሰባሪ መንግሥታትና የመሰበራቸው ምክንያቶች
በዓለማችን የመክሸፍ አደጋ የሚታይባቸውን አገራት ዝርዝር በየዓመቱ በማውጣት የሚታወቀው የውጭ ፖሊሲ መጽሔት ሰሞኑን አደጋው የሚታይባቸውን አገራት በዝርዝር አውጥቷል። በዚህ የ178 አገራትን ዝርዝር በያዘው ዘገባ መሠረት ቁጥር አንድ የአደጋው ተጋላጭ ደቡብ ሱዳን ስትሆን ኢትዮጵያ ደግሞ 19ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ጠቁሟል። ባለፈው የአውሮጳውያን ዓመት 2013 መረጃ ላይ ተመርኮዙ የወጣው ዘገባ 12 መስፈርቶችን በግብዓትነት የተጠቀመ መሆኑን አስታውቋል። እነዚህም፤ የስነሕዝብ ተጽዕኖ፡ ከህዝብ ብዛት ጋር በተያያዘ የምግብ ዕጥረት፣ የሟቾች ቁጥርና ፍጥነት፤ ስደተኞችና በአገር ውስጥ የሚፈናቀሉ፡ በስደት ወደ አገር የሚገቡና በአገር ውስጥ ከየቦታው የሚፈናቀሉ፤ የቡድን (የሕዝብ) ሃዘን፡ በአገር ውስጥ ባሉ ቡድኖች መካከል ያለው ውጥረትና ጠብ፤ አገር ጥለው የሚሄዱና … [Read more...] about ተሰባሪ መንግሥታትና የመሰበራቸው ምክንያቶች
የኔኛው
አንዱ አንበሳ ነው. . . ወገኑ ሲነካ ዘራፍ ነው የሚለው። ሌላው ደግሞ ጅብ ነው. . . የሚበላ አግኝቶ ግዳይ የጣለ ዕለት፥ ወገኑን ሳይጠራ ጭራሹን አይነካት። የኔኛው ውሻ ነው ለያውም ተናካሽ፥ የራበው ወንድሙን ወገኑን አስለቃሽ። የሞተ አግኝቶ በልቶ ይጠግብና፥ ወገኖቹ ውሾች እንዳይበሉ ይልና፥ እዛው ጋር ይተኛል እያባረራቸው፥ ትንሽ እንዳይቀምሱ ሊከለክላቸው። ግን ቁራና ጭልፊት ከሰማይ የሆኑት፥ ምንም አይላቸው ስስቱን ሲበሉት። ----- (By Gemechu Merera) 23/11/2009 … [Read more...] about የኔኛው
ሀገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ከጥፋት የሚያድነው ብቸኛው መንገድ!!!
ዛሬ እውነት እውነቱን እንቅጭ እንቅጩን እንነጋገራለን፡፡ እንዴ! ይሄ ሰው ከዚህ ቀደም ሲያወራልን የኖረው ቅጥፈት ነበር እንዴ? እንዳትሉ፤ አለ አይደል ይሄ መፏከቱን መሸራደዱን መበሻሸቁን ትተን እንደ ባለ አእምሮና ኃላፊነት እንደሚሰማው ዜጋ በንጹሕ በቅዱስ ልቡና ልዕልና ያለውን ሐሳብ አንሥተን እንወያያለን ለማለት ነው፡፡ የኢትዮጵያ አምላክ ዐይነ ሕሊናችንን ያብራልን እዝነ ልቡናችንን ይክፈትልን አሜን!! ሀገራችን ኢትዮጵያ የዘውግ ፖለቲካ (እምነተ-አስተዳደር) ወይም ብሔር ተኮር የሆነ ከፋፋይና አጥፊ የአገዛዝ ሥርዓት ውስጥ በግዳጅ እንድትዘፈቅ ከተደረገች 24ኛ ዓመታችንን ይዘናል፡፡ በዚህ ዘመን ውስጥ አንድነት የነበረው ሕዝብ በግድ ካልተነጣጠልክ፣ በጎሪጥ ካልተያየህ፣ እንደ አንድ ሀገር ሕዝብ ሁሉ ለእኛ ለእኛ ሳይሆን ለእኔ ለእኔ (ለብሔረሰቡ ብቻ) ካላልክ ተብሎ እየተወተወተ ወዶ … [Read more...] about ሀገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ከጥፋት የሚያድነው ብቸኛው መንገድ!!!
Center for the Rights of Ethiopian Women (CREW) Fundraising Event
አራዊታዊ መንግሥታት
አራዊታዊው ኢሀደግ እና የየመን መንግሥት በአቶ አንዳርጋቸው ላይ በፈጸሙት አራዊታዊ ተግባር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቀሳውስት ዶክተር ቀሲስ አማረ ካሣየ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ አባ ኃ/ሚካኤል የሰጡት መግለጫ፦ በአገራችን ላይ ክፉ ዘመን የወለደው አራዊታዊው መንግሥትና የየመን መንግሥት በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የፈጸሙት አራዊታዊ ተግባር በፈጣሪና በፍጡሩ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው፤ የሰው ጥንተ ጠላት የሆነው የሰይጣን ተግባር ስለሆነ፤ በቅድስት ቤተ ክርስቲያችን የሚወገዝ ነው። ሕዝባችንም የዜግነት ከለላ ከሰጣቸው ከእንግሊዝ መንግሥት ጋራ በመተባበር አቶ አንዳርጋቸውንና በተመሳሳይ አራዊታዊ አደና የተያዙትን ሁሉ ኢትዮጵያውያን ለማስለቀቅ የጀመረውን ጥረት አስፈላጊ በሆነው ሁሉ መንገድ እንዲቀጥል እግዚአብሔር የሚቀበለውና የቅድስት ቤተ ክርስቲያንም … [Read more...] about አራዊታዊ መንግሥታት
ነጻነትን ለመጎናጸፍ ባሩዷን ማሽተት የግድ ነው !!!
የወያኔ የግፍ ስርዓት በህዝብ ትከሻ ላይ ድሩን አድርቶ ፤ የማይጠረግ እስኪመስለን ድረስ ሁለት አስርት አመታቶችን በላያችን ላይ ዘልቋል ።በሰላማዊ መንገድ የግፉ ስርዓት ተቋጭቶ ፍትህና እኩልነት በሀገራችን ይሰፍን ዘንድ ብዙ ተሞክሯል ። ነገር ግን በወያኔ ስልጣን አልጠግብ ባይነት እና የሰላማዊው መንገድ ክርችም ብሎ በመዘጋቱ ባሩዷን ማሽተት ግድ የሆነበት ጊዜ ላይ ከደረስን ከራርመናል ።ትግሉ ከኛ ምን ያህል የአላማ ጽናትን ይፈልጋል ? ምን ያህልስ መስዋእትነትን ያስከፍለናል ? እንዴትስ ብንታገል ካሰብነው የነጻነት ደጃፍ ባጭሩ ያደርሰናል ብለን ብንጠያየቅ ትክክለኛ ጊዜው አሁን ይመስለኛል። አብዛኛው ኢትዮጵያዊም በተለይም በወጣትነት የእድሜ ክልል ያለው የህብረተሰብ ክፍል ስልጣንን ከህወሃት መዳፍ ውጭ አይቶት ስለማያውቅ ፤ ሀገሪቱን እነሱ ብቻ እንዲመሩ መለኮታዊ የሆነ ፈቃድ ያላቸው … [Read more...] about ነጻነትን ለመጎናጸፍ ባሩዷን ማሽተት የግድ ነው !!!
የጋዛ ፍልስጥኤማውያን የደም እንባ!
የእስራኤል የ10 ቀናት የአየር ድብደባ ከ220 በላይ ፍልስጥኤማውያን የጋዛ ነዋሪዎች በአሰቃቂ ሁኔታ በሚወሰደው ዘመቻ ነገን ላያዩ መቀጠፋቸውን እየሰማን ነው: (ከአንድ ሽህ በላይ የዘለቁ በጠና የቆሰሉትን እና ከቀያቸው የተፈናቀሉት ዜጎችን መከራ እያየንም ነው። እኒህኞቹን በራሳቸው ሀገር ስደተኛ የሆኑትንማ ፍዳ ማየቱ ከሞቱት በላይ ያማል። ሰቆቃው በዚህ ቢያቆም መልካም ነበር ፣ ግን አልሆነም ። በሳምንቱ መጀመሪያ የፍልስጥኤማውያን ሃማስ የጦር ክንፍ ሰው አልባ ሚጢጢ አውሮፕላን Drone ...በእስራኤል ሰማይ መስፈንጠሩን አስታወቀ። ይህም የሃማስን የሚሳኤል ሮኬት ውንጨፋ ለወረራው ምክንያት ላደረጉት እስራኤሎች ከስጋት ባለፈ ጥሩ የመልሶ ማጥቂያ ምክንያት ሆነና ነገሮችን ሁሉ በፍጥነት መቀያየር ይዘዋል። ብቻ ...ዛሬ ሃሙስ ለአርብ በደረቁ ሌሊት የደረሰን ሰበር ዜና አስራኤል … [Read more...] about የጋዛ ፍልስጥኤማውያን የደም እንባ!