• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የጋዛ ፍልስጥኤማውያን የደም እንባ!

July 18, 2014 04:56 pm by Editor Leave a Comment

የእስራኤል የ10 ቀናት የአየር ድብደባ ከ220 በላይ ፍልስጥኤማውያን የጋዛ ነዋሪዎች በአሰቃቂ ሁኔታ በሚወሰደው ዘመቻ ነገን ላያዩ መቀጠፋቸውን እየሰማን ነው: (ከአንድ ሽህ በላይ የዘለቁ በጠና የቆሰሉትን እና ከቀያቸው የተፈናቀሉት ዜጎችን መከራ እያየንም ነው። እኒህኞቹን በራሳቸው ሀገር ስደተኛ የሆኑትንማ ፍዳ ማየቱ ከሞቱት በላይ ያማል።

ሰቆቃው በዚህ ቢያቆም መልካም ነበር ፣ ግን አልሆነም ።  በሳምንቱ መጀመሪያ የፍልስጥኤማውያን ሃማስ የጦር ክንፍ ሰው አልባ ሚጢጢ አውሮፕላን Drone …በእስራኤል ሰማይ መስፈንጠሩን አስታወቀ። ይህም የሃማስን የሚሳኤል ሮኬት ውንጨፋ ለወረራው ምክንያት ላደረጉት እስራኤሎች ከስጋት ባለፈ ጥሩ የመልሶ ማጥቂያ ምክንያት ሆነና ነገሮችን ሁሉ በፍጥነት መቀያየር ይዘዋል።

ብቻ …ዛሬ ሃሙስ ለአርብ በደረቁ ሌሊት የደረሰን ሰበር ዜና አስራኤል እግረኛ ጦር ወደ ጋዛ ማሰማራቷን ጠቁሟል። ሃማስም ከእግረኛው ጦር ጋር ፍልሚያው መጀመሩን ከዛቻ ጋር አስታውቋል። የተፈራው አደጋ  የፍጥጫ እልህ ውዝግቡ የፍጻሜ ውጤት አቅጣጫ እዚህ ላይ ደርሷል።  የቦንብ ናዳ  ያላባራባት ጋዛና የጋዛ ነዋሪ በሰማዩ ስር በሃዘን ድባብ ተውጦ ምድር ገሃነብ ሆኖበት ሰንብቷል። የሃማስ ተወንጫፊ ሚሳኤሎች ጎድተው ላይጎዱ በተለያዩ የጽዮኗ ምድር ከመዝነብ  ያቆማቸው የለም። እስካሁን ሞቶ የሰማነው እስራኤላዊ ቁጥር ግን አንድ ብቻ ነው።

እስራኤል  “ነውጠኛ አሸባሪው ሃማስን የማጽዳት ዘመቻ” በማለት በያዘችው ማጥቃት በምክንያትነት ከሚጠቀሱት  ኢላማዎች መካከል እስካሁን ተገደሉ የተባሉ ቁጥር ፣ ከተገደሉት ንጹሃን ጋር ሲወዳደር እዚህ ግባ አይባልም። በዋይታ ይህችን ፍትህ የጎደላት አለም እየተለዩ ያሉት ፍልስጥኤማውያን አቅመ የእድሜ ባለጸጋዎች፣ ህጻናትና አባወራ የቤተሰብ አባላት ናቸው። ይህ ልብን በሃዘን ቆልፎ ይሰብራል  🙁

ከሁሉም የሚዘገንነው በእስራኤል ዘመቻ የተቀጠፉት “ጦር ሰባቂ ፣ ቆስቋሽ ” የሚባሉት የሃማስ ሚሊሻዎች አለመሆናቸው ሲሆን ሚሊሽያ ታጣቂዎች እንደ ዶፍ በሚዘንበው አረር  ኢላማ የገቡ አይመስልም። “ለሃጥአን የመጣ ለጻድቃን ” እንዲሉ  በአዋጅ ነጋሪት ክተት ተብሎ የተዘመተባቸው ሃማሶች ሳይገደሉ ንጹሃን በግፍ እያለቁ ነው። ከሃማስ ሸማቂ በኩል ሞቱ የተባሉት ከቆሰሉት ጋር ቢደመሩ ከሃያ ፈቀቅ ለማለቱ መረጃ አላየሁም። ድብደባውም ሃማስን ሚሊሻዎች ሚሳኤል ከመወንጨፍ አላስቆማቸውም። ይህ ምልክት ያን ሰሞን ” የመከራ ደወል !” ያልኩትን የአደጋ ስጋት ሲያዘክር ዛሬ የስጋቱ ጊዜ አክትሞ መከራ ሰቆቃውን እያየነው ነው።  እየሆነ ያለው አሳዛኙ ውጤት ፍጻሜ ይህ ይመስላል !  ዳሩ ግን ሃማስን ለማንበርከክ የግዛት ክልሉንና የሚያስተዳድረውን ህዝብ በአየርና በምድር ጦር በትምክህት ደፍጥጦ መበቀል ከሆነ ሌላ ነገር ነው።

የሃማስ የጦር ክንፍ መክቶ  ላይመክት ፣ ጎድቶ ላይጎዳ ባስፈነጠራቸው ሮኬቶች ሌላ አደጋ በህዝቡ ላይ እያስከተለ ነው። በአጣብቂኝ ስርቻም ሆኘ በራሪ Drone  ሰራሁ ብሎ ማወጁ ለፍልስጥኤማውያን የፈየደው ወረራውን ማፋጠን ነው። ብቻ ሃማስ ከእስራኤል ጦር ጋር ተፋጦ በሚያደርገው መቆራቆስ የንጹሃን ደም ግብር የማከፈልበት መቸ ለሚመጣው፣  ማን ለሚኖርበት ትንሳኤ እንደሆነ አልገባኝ …

አረቦች ለፍልስጥኤም ግፉአን ወንድሞቻቸው መከታ እንዳይሆኑ በልዩነት ተበታትነዋል።  የአለም መንግስታት በአንጻሩ ይህ መሰሉ ግፍ በጋዛ ፍልስጥኤም ሲፈጸም ዛሬም መሸምገል ገዷቸው ደም ሲፈስ የግፍ ተመልካች ሆነዋል። በሩዋንዳው የጅምላ ጭፍጨፋ እልፍ አእላፍ አልቀው ፣ በትኩሱ ሬሳ ላይ ቆመው ያነቡት የአለም መራሔ መንግስታት  “ይህ ግፍ ፈጽሞ አይደገምም” Never Again ብለው ያፈሰሱት እንባ “የአዞ እንባ” መሆኑን ዛሬም ሆነ ትናንት በጋዛ ፍልጥኤማውያን እየሆነ ባለው “የአዛኝ እንባቸውን” እያየነው ነው: (

የእስራኤልን ዘመቻ ፣ የንጹሃንን እልቂት ፣ የሃማስን ስልት የጎደለው መከላከል በሉት ማጥቃት አልገባህ ብሎኛል። ይህንን ንጹሃን የሚቀጠፉበትን ዘመቻ ለማውገዝ ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው። ይህ ሁሉ ውስብስብ ያልሆነ ግን ቅንነት ጠፍቶ የአለም  ማህበረሰብ መፍታት ባልቻሉት ውዝግብ በዚህ ዘመን ይህን ግፍ አለም ማስተናገድ ነበረባት?  ይህ ግልጽ የሃይል ሚዛን እና የተጽዕኖ መፍጠር ጫና  ለፍልስጥኤም ንጹሃን ማለቅና ለአለም ዝምታ መምረጥ ምክንያት አይደለምን ?  ይህስ በራሱ ግፍ አይደለምን ? ግልጽ የሚታየው እንቆቅልሽ መፈቻው ጊዜ መቸ ይሆን?  በሁለት ጽንፈኞች መካከል ታርቀው የሚረግፉት የፍልስጥኤማውያን እንባስ ማቆሚያው መቸ ነው?

እስኪ ቸር ያሰማን …

ነቢዩ ሲራክ

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
Copyright © 2026 · Goolgule