
አንዱ አንበሳ ነው. . .
ወገኑ ሲነካ
ዘራፍ ነው የሚለው።
ሌላው ደግሞ ጅብ ነው. . .
የሚበላ አግኝቶ ግዳይ የጣለ ዕለት፥
ወገኑን ሳይጠራ ጭራሹን
አይነካት።
የኔኛው ውሻ ነው
ለያውም ተናካሽ፥
የራበው ወንድሙን ወገኑን
አስለቃሽ።
የሞተ አግኝቶ በልቶ ይጠግብና፥
ወገኖቹ ውሾች እንዳይበሉ ይልና፥
እዛው ጋር ይተኛል እያባረራቸው፥
ትንሽ እንዳይቀምሱ ሊከለክላቸው።
ግን ቁራና ጭልፊት ከሰማይ
የሆኑት፥
ምንም አይላቸው ስስቱን ሲበሉት።
—–
(By Gemechu Merera)
23/11/2009
Leave a Reply