በሳውዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ ሁለት የጸጥታ ጥበቃዎችን ጨምሮ ከ13 በላይ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች በስሩ እንደሚገኙ የሚነገረለት ይህ የመዝናኛ ማዕከል ከተቆርቆረ ሁለት አስርት አመታትን ቢያስቆጥርም ከቅርብ ግዜ ወዲህ በተለያዩ ሰንካል ምክንያቶች ከትርፋማነት ይልቅ ኪሳራ፤ ከእድገት ይልቅ ወደቀትን እያቀነቀነ አሁን ላለበት ደረጃ መድረሱን የሚናገሩ እማኞች በሰራተኞቹ ላይ እይተፈጸመ ያለው በደል ከመቸውም ጊዜ በላይ እየከፋ መምጣቱን ገልጸዋል። ይህ የኮሚኒቲ ማህበር ካፍቴሪያ ማዕከል ዛሬ ላለበት አሳፍሪ ደረጃ ምክንያት መሆኑ የሚነገረው በተለያዩ ወቅቶች በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ጀርባ ታዝለው ያለችሎታቸው አመራር የሚሆኑ ግለሰቦች ከኮሚኒቲው ካፍቴሪያ ሰራተኞች ጋር በቀረበት ተነጋገረው የካፍቴሪያውን መሰረታዊ ችግር ለመቅረፍ የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት ከመወጣት ይልቅ ከማህበሩ … [Read more...] about “ድምጽ አልባው አስዛኝ የወገኖቻችን ለቅሶ በሳውዲ አረቢያ ሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ!”
Archives for December 2013
የነፃነት አባት
ታ ሪኩ ገናና፤ ስራው የለው አቻ ላ ሰበበት ጉዳይ፤ የሌለው ፍራቻ ቁ ጣን ቂም በቀልን፤ ያጠፋ ጥላቻ ማ ንዴላ ታላቁ፤ የነፃነት ጮራ ን ጥረ መብረቅ ሆኖ፤ አፍሪካን ያስጠራ ዴ ሞክራሲ እንዲያብብ፤ ተስፋውን ሰንቆ ላ ሰበው አላማ፤ ቆሞ ነበር ታጥቆ የ ህይወት ዘመኑ፤ ቢሆንም መራራ ነ ፃነት አላብሷል፤ ስሙን የሚያስጠራ ፃ ድቅ የሆነ ሰው፤ እያለ በሕይወት ነ ውና ተግባሩ፤ መልካም ነገር መስራት ት ዕዛዙን ፈጽሟል፤ በእድሜው ዘመናት ዓ ለም መቆያ ናት፤ ተቀባይ እንግዳ ባ ህሪዋ መራር፤ ወሳጅ በሞት እዳ ት ልቅ ትንሽ ሳትል፤ ድንገት የምትከዳ ና ልን አይባልም፤ ማንዴላም ተመለስ ቸ ሩ ፈጣሪያችን፤ የታላቁን ሰው ነፍስ ው ለታ ይክፈላት፤ ወደሱ ስትደርስ … [Read more...] about የነፃነት አባት
ማንዴላን በተመለከት ለግማሽ ዓመታት የተደበቅ ምስጢር
ኔልሰን ማንዴላ የደቡብ አፍሪካ የፀረ-አፓርታይድ (የዘር-መድሎ) ተዋጊ አርበኛ መሆናቸው ይታወቃል። በደቡብ አፍሪካ ዘረኛ መንግስት ለእስር የተዳረጉት ኢትዮጵያ ውስጥ ወታደራዊ ስልጠና ወስደው እንደተመለሱ ነበር። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ 1962 ዓም ማንዴላ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ኢትዮጵያ ፓስፖርት በመስጠት አጋርነቷን የገለፀች ብቸኛ ሀገር ነበረች። ከዘመናት በኃላ ማንዴላ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ወቅት የግድያ ሙከራ ሴራ ተደርጎ እንደነበር ሚስጥሩን ከግማሽ ክፍለዘመን በላይ ይዘው የቆዩ በቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ዘመን የኢትዮጵያ ፖሊስ መኮንን ዛሬ ጥቅምት 15/2006 ዓም ለመጀመርያ ጊዜ በሸገር ራድዮ የዜና እወጃ ላይ ገልፀዋል። ሻምበል ጉታ ዲንቃ በንጉሡ ዘመን የፖሊስ መኮንን ነበሩ። ማንዴላን በከፍተኛ ሚስጥር እንዲጠብቁ ኃላፊነት ከተሰጣቸው ጄኔራል ታደሰ(የማንዴላ አሰልጣኝ … [Read more...] about ማንዴላን በተመለከት ለግማሽ ዓመታት የተደበቅ ምስጢር
በብሔር ፖለቲካ ሥር “የተቀበረው ፈንጂ”!
የብሔር ጥያቄ በኢትዮጵያ ምላሽ እንዳገኘ የሚያስተጋባው ኢህአዴግ “የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች” በዓልን ማክበር ከጀመረ ስምንት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በአንፃሩ “ተመልሷል” የተባለው ጥያቄ እንደተቀበረ ፈንጂ በየጊዜው በየቦታው እየፈነዳ በህይወት፣ በንብረትና በኢትዮጵያዊነት ላይ አደጋ ማድረሱን ዳዊት ሰለሞን ሁነቶችን በመጥቀስ ይሞግታል፡፡ ከአስርት አመታት በፊት የኢትዮጵያ ተማሪዎች በለውጥ አብዮት ናፍቆት እየተናጡ ነው፡፡ እዚህም እዚያም በተፈጠሩ ቡድኖች የማርክሲስት-ሌኒንስት ፍልስፍናን የሚሰብኩ የርዕዮተ ዓለም ጽሁፎች ይነበባሉ፡፡ ተማሪው ይከራከራል፣ የሌኒኒዝም ፍልስፍና ቀለም ቀለም መሽተት ለጀመረው የ1960ዎቹ ትውልድ ልብ የቀረበ ሆኗል፡፡ ፍልስፍናውን በአገራቸው የፖለቲካ ግለት ለመተርጐም የቋመጡት ወጣቶች በሁለት ጠርዝ ተሰልፈው በኢትዮጵያ ያለው “የመደብ ወይስ የብሔር … [Read more...] about በብሔር ፖለቲካ ሥር “የተቀበረው ፈንጂ”!
ሰማያዊ ፓርቲ በአሜሪካ
ተከብሮ ያላስከበረ ሕገ-መንግስት …
ህዳር 29 ቀን 1987 ዓ.ም ሕገ-መንግስቱ የፀደቀበት ቀን ነው፡፡ ይህንንም ተከትሎ በመንግስት አሳሳቢነት እልፍ ሲልም አስገዳጅነት ህዳር 29 በየዓመቱ ከተለያዩ ጎሳ የተወጣጡ ሰዎች ተሰባስበው በመንግሰት ሹማምንቶች ፊት በአደባባይ ከበሮ የሚደለቅበት ቀን ነው፡፡ ይሁን እንጂ የአብዛኛው ኢትዮጵያዊያን መልካም ፍቃድና ተሳትፎ ባልታየበት የፀደቀው ህገ መንግስት በብዙሃን ዘንድ ተቀባይነቱ ጥያቄ ውስጥ የገባ ነው፡፡ በዚህም መሠረት ከቃሉ አጠቃቀም ጀምሮ እስከ አከባበሩ ክብረ በዓል አብዛኛዉ ሰው እኔንም ጨምሮ ግድ አይሰጠንም፡፡ ‹‹ይህ ህገ-መንግስቱን የመነዳ ተግባር ነው!!!›› ከገዢው መንግስት ተደጋግሞ የሚሰማ ለመፈረጅ ወይም ለመከሰስ የሚጠቀሙበት ቃል ነው፡፡ አንድ ወዳጄ እንዲህ አለኝ ‹‹ይህ ህገ መንግሰት ዝም ብሎ የተደረደረ ብሎኬት ነው እንዴ የሚናደው?›› በማለት ሲተች … [Read more...] about ተከብሮ ያላስከበረ ሕገ-መንግስት …
በቃ! በለን አምላክ (say us enough! O’ God)
ያ የምትወደው ፤ ያ የምታሞካሸው ልጆቸና ሕዝቤ ፤ እያልክ ያከበርከው መከራ አፈናቅሎት ፤ ከሀገሩ ከቀየው ከአሕዛብ ደጅ ወድቆ ፤ ግፍ ሰቆቃ ቆላው፡፡ የጭንቅን ልክ ዓየ ፤ ሞት በዓይነት ቆጠረ የሰቆቃን ጣራ ፤ ከፍ ብሎ በረረ ሞትን ተላመደ ፤ ንቆም ተዳፈረ በእሱ እየተበላ ፤ በእሱ ላይ ፎከረ የአውሮችን አውሬነት ፤ ተበልቶ አጋለጠ ድብቁን አወጣ ፤ ነፍሱን ለሀቅ ሰጠ፡፡ ምን ዓይነት ፍጥረቶች ፤ ምን ዓይነት ጉዲራ እውን ሰዎች ናቸው ? የሆኑ የእጅህ ሥራ ? ወይስ ሰይጤ እንዳለው ፤ እኔ ነኝ ፈጣሪ ይሆኑ ይሆን የሱ ፤ የዚያ እርኩስ መሠሪ በሁለ ነገሩ ፤ እሱን አስመስሎ እንደራሱ አድርጎ ፤ ፈጥሯቸው አንቦልቡሎ ? ወይስ ከነገዱ ፤ ከሆኑት እንደሱ ሥጋ ለብሰው መጡ ? ሰው መስለው … [Read more...] about በቃ! በለን አምላክ (say us enough! O’ God)
በመዲናዋ ምስጢራዊ የወሲብ ገበያ ደርቷል
የትላልቅ ድርጅቶች ፀሃፊዎች፣ ሞዴሎችና ተዋናዮች አሉበት ድንግልናን በ10ሺ ብር የሚያሻሽጡ ደላሎች ሞልተዋል የከተማዋ ቱባ ባለሃብቶች “የአገልግሎቱ” ተጠቃሚዎች ናቸው ሲኤምሲ ሣሚት ማዞሪያ አካባቢ ካሉት ዘመናዊ ቪላ ቤቶች በአንደኛው 12ሺ ብር ወርሃዊ ኪራይ እየከፈለች ትኖራለች፡፡ የምታሽከረክረው ኤክስኪዩቲቭ ቶዮታ፣ በየዕለቱ የምትቀያይራቸው እጅግ ውድ ዋጋ ያላቸው አልባሳቶቿና በየመዝናኛ ሥፍራው የምትመዘው ረብጣ ብር የተንደላቀቀ ኑሮ እንደምትመራ ይመሰክራሉ፡፡ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናትና መዲናችን አለማቀፋዊ ስብሰባዎችን በምናስተናግድበት ጊዜያት እሷን ፈልጐ ማግኘት የማይታሰብ ነው፡፡ ቦሌ ፍሬንድሽፕ ሕንፃ ላይ በከፈተችው ቡቲክ የምታገኘው ገቢ ይሄን ያህል ሊያዝናናት እንደማይችል የታወቀ ነው፡፡ ገቢ ወጪዋን አጥብቃ የማትቆጣጠርበትን ይህንኑ ቡቲኳን ታናሽ እህቷ … [Read more...] about በመዲናዋ ምስጢራዊ የወሲብ ገበያ ደርቷል
ማዲባ አረፉ!
ደቡብ አፍሪካን ከ1994 – 1999 (እኤአ) በፕሬዚዳንትነት የመሩት ኔልሰን ሮሊህላህላ ማንዴላ ከረጅም ጊዜ ህመም በኋላ ህዳር 26፤ 2006ዓም በ95 ዓመታቸው አርፈዋል፡፡ በፕሬዚዳንትነት መንበር ላይ ከመቀመጣቸው በፊት ለ27 ዓመታት ታስረዋል፡፡ ለነጻነት በተደረገው ትግል እስከ 156 በሚደርሱ የተለያዩ “ወንጀሎች” ተከስሰው እንደነበር ይታወቃል፡፡ ራሱ አሸባሪ የነበረው የአፓርታይድ አገዛዝ “ወንጀለኛና አሸባሪ” በማለት ስም ከሰጣቸው በኋላ አሜሪካም ተመሳሳይ እርምጃ በመውሰድ “አሸባሪ” የሚለውን ስም ለጥፋባቸው ለረጅም ዓመታት ቆይታለች፡፡ ከዚህም አልፎ ማንዴላን ጨምሮ በርካታ የኤኤንሲ አመራሮችንና አባላትን በአሸባሪነት ዝርዝር ውስጥ በማስገባት ለተለየ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር (ለተባበሩት መንግሥታት ዓይነት ስብሰባ) ወደ አሜሪካ የመግቢያ ቪዛ ሲከለከሉ ቆይቷል፡፡ ሁኔታው በዚህ … [Read more...] about ማዲባ አረፉ!
“ታህሳስ 5 ከሰአት በኋላ ለመገደል ፈርሜአለሁ”
ታህሳስ 5 ከሰአት በኋላ ለመገደል ፈርሜአለሁ ገጽ 410 ይላል የስደተኛው ማስታወሻ፤ አቶ ተስፋዬ ገብረአብ "ጓደኛዬ" የሚለው ሆላንዳዊ ስለያዘው የሞት ቀጠሮ ሲያብራራ፤- ለሚቀጥለው … ማስታዉሻ መጽሀፉ ይረዳው ዘንድ ሆላንድ ውስጥ የሞት ቀጠሮ እንዴት እንደሚያዝ ከዚህ በታች አብራራለሁ፤ ከዚያ በፊት ግን ስለ ስደተኛው ማስታወሻ የምለው ከዚህ የሚከተለውን ነው፤ ጫልቱ ብሎ የሰየማትን ተዋናይ እዛው የቡርቃ ዝማታው ላይ ቢከታት ኖር ገጸ ባህርይዋ ከዛ ጋር ይሰምርለት ነበር፡፡ ነገር ግን ከአለቆቹ የደረሰው ትእዛዝ አማራና ኦሮሞን ማፋጀት የኢትዮጵያን ስማ ማጥፋት በመሆኑ የግድ መካተት ነበረባት፤ በጎሳ እምነት የተለከፉ ሰዎች አመለካከታቸው ወደሌላ ሰውነት እንደተሰራጨ ካንሰር ነው፤ ቢነግሩአቸው ቢያስረዷቸው አይጠሩም፤ የተስፋዬ ገብረአብ ተማሪዎች በቀደም ሳውዲ አረቢያን ተቃውሞ ሰልፍ ላይ … [Read more...] about “ታህሳስ 5 ከሰአት በኋላ ለመገደል ፈርሜአለሁ”