• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በመዲናዋ ምስጢራዊ የወሲብ ገበያ ደርቷል

December 8, 2013 12:31 pm by Editor 7 Comments

  • የትላልቅ ድርጅቶች ፀሃፊዎች፣ ሞዴሎችና ተዋናዮች አሉበት
  • ድንግልናን በ10ሺ ብር የሚያሻሽጡ ደላሎች ሞልተዋል
  • የከተማዋ ቱባ ባለሃብቶች “የአገልግሎቱ” ተጠቃሚዎች ናቸው

ሲኤምሲ ሣሚት ማዞሪያ አካባቢ ካሉት ዘመናዊ ቪላ ቤቶች በአንደኛው 12ሺ ብር ወርሃዊ ኪራይ እየከፈለች ትኖራለች፡፡ የምታሽከረክረው ኤክስኪዩቲቭ ቶዮታ፣ በየዕለቱ የምትቀያይራቸው እጅግ ውድ ዋጋ ያላቸው አልባሳቶቿና በየመዝናኛ ሥፍራው የምትመዘው ረብጣ ብር የተንደላቀቀ ኑሮ እንደምትመራ ይመሰክራሉ፡፡ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናትና መዲናችን አለማቀፋዊ ስብሰባዎችን በምናስተናግድበት ጊዜያት እሷን ፈልጐ ማግኘት የማይታሰብ ነው፡፡

ቦሌ ፍሬንድሽፕ ሕንፃ ላይ በከፈተችው ቡቲክ የምታገኘው ገቢ ይሄን ያህል ሊያዝናናት እንደማይችል የታወቀ ነው፡፡ ገቢ ወጪዋን አጥብቃ የማትቆጣጠርበትን ይህንኑ ቡቲኳን ታናሽ እህቷ ትውልበታለች፡፡ እሷም አልፎ አልፎ “ሥራ” በማይኖራት ጊዜ ብቅ እያለች ትጐበኘዋለች፡፡ ታናሽ እህቷ ቤተሰቡን ሁሉ ቀጥ አድርጋ የምታስተዳድረው እህቷ፤ ስለምትሰራው ምስጢራዊ ሥራ አንዳችም የምታውቀው ነገር ያለ አይመስልም፡፡ እሷ የምታውቀው ከተለያዩ የውጪ አገር ሰዎች ጋር የአየር ባየር ንግድ እንደምታጧጡፍና በየጊዜው ወደተለያዩ አገራት ለሥራ ጉዳይ እንደምትመላለስ ብቻ ነው። ሥራዋ የግል ሚስጢሯ ብቻ ሆኖ እንዲኖር የምትፈልገው ህሊና (ስሟ ለዚህ ጽሑፍ የተቀየረ) ይህንን የእህቷን እምነት አጥብቃ ትፈልገዋለች። በተለያዩ የመዝናኛ ሥፍራዎች ከአገር ውስጥና ከውጭ አገር ደንበኞቿ ጋር እየከረመች በመጣች ቁጥር ለእህቷ የተለያዩ ቸኮሌቶችና ስጦታዎችን እየያዘችላት መምጣቷ የእህቷን እምነት አጠናክሮላታል፡፡

እሷ “ቢዝነስ” ብላ የገባችበት ህይወት ገቢ፣ እህቷ ቀኑን ሙሉ ተገትራ ከምትውልበት ቡቲክ ገቢ ጋር ሊወዳደር እንደማይችል ስለሚገባት “ሥራውን” አጥብቃ መያዙን  ትፈልገዋለች፡፡ የንግድ ፍቃድ እድሣት፣ ቫት ምዝገባ፣ ሪሲት ማሽን፣ ቀረጥና ታክስ የሚሉ ዝባዝንኬዎች የሌሉበት፣ “ራስን እያስደሰቱ ሌሎችን በማዝናናት” በቀን የሚገኝ ረብጣ ብር ከቡቲኳ ወርሃዊ ገቢ በእጅጉ ይልቃል። ተፈጥሮ ያደላትን ውበትና ማራኪ ቁመናዋን ለገበያ እያቀረቡ በተሻለ ገንዘብ ለመሸጥና ጠቀም ያለ የኮሚሽን ገንዘብ ለመቀበል አሰፍስፈው የሚጠባበቁ ደላላ ደንበኞች አሏት፡፡ ለዚህ ተግባር ብቻ የምትጠቀምበት የሞባይል ስልኳ ሲጮህ “ሥራ” እንደተገኘ እርግጠኛ ትሆናለች። ቅያሬ ልብሶችን የምትይዘበትና ሁሌም ለጉዞ ዝግጁ የምታደርገውን ቦርሣዋን አንጠልጥላ ውልቅ ነው። አብዛኛውን ጊዜ ወደ ሥራ የምትንቀሳቀሰው በደላሎቹ መኪና ነው። ደላላው እሷን ካለችበት ወስዶ ወደምትፈለግበት፣ ሥራዋን ስትጨርስ ደግሞ ወደነበረችበት የመመለስ ግዴታ አለበት፡፡

የኮሚሽን ክፍያው እነዚህን አገልግሎቶች ያካተተ ነው፡፡ ህሊና ይህንን ህይወት ላለፉት አራት አመታት ኖራበታለች። ከዚህ ህይወት ስለመውጣትና ቢዝነሱን ስለመተው ለአፍታም አስባ አታውቅም፡፡

ባላት ትርፍ ሰዓት ሁሉ ራሷን እጅግ አድርጋ መጠበቅ፣ ጂም መሥራት፣ ሳውና፣ ስቲምና ማሣጅ በየጊዜው መግባት ታዘወትራለች፡፡ ውበቷንና ጥሩ ቁመናዋን ጠብቃ ለማቆየት ማድረግ የሚገባትን ሁሉ ከማድረግ ወደኋላ አትልም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ለዚህ ሁሉ አዱኛ ያበቃት እሱ በመሆኑ የሚፈልገውን ሁሉ ማድረግ እንዳለበት ታምናለች፡፡ ይህ የህሊና ህይወት የብዙ ኢትዮጵያውያን ወጣት ሴቶች ህይወት እየሆነ ከመጣ ሰነባብቷል፡፡ በመዲናችን አዲስ አበባ እየተጧጧፈ የመጣውን ምስጢራዊ የወሲብ ገበያ የተቀላቀሉ የከተማችን ወጣት ሴቶች የትላልቅ ድርጅቶች ኤክስኪዩቲቭ ፀሐፊዎች፣ የሽያጭ ሰራተኞች፣ ሞዴሎች፣ የፊልም ተዋናዮች፣ የዩኒቨርስቲዎችና የኮሌጅ ተማሪዎችና ገና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያላጠናቀቁ የሀብታም ልጆች ናቸው፡፡ እነዚህን ወጣት ሴቶች ለወሲብ ሽያጭ “ሥራ” የሚያመቻቹና የማገናኘት ተግባሩን በቅልጥፍና የሚወጡ ፈረንጆች “ፒምፕ” የሚሏቸው አይነት ደላሎች በከተማችን እየተበራከቱ ነው፡፡ ደላሎቹ ራሳቸው በኔትዎርክ የተሣሰሩ፣ የራሳቸውን መኪና ይዘው የሚንቀሳቀሱ፣ በከተማው ውስጥ አሉ የተባሉ ሆቴል ቤቶችን፣ እንግዳ ማረፊያዎችን፣ መቃሚያ ቤቶችንና የመዝናኛ ሥፍራዎችን በቁጥጥራቸው ሥር ያደረጉ ናቸው፡፡

ደላሎቹ ወደ እነዚህ ሥፍራ የሚመጡ አዳዲስ እንግዶችንና ነባር ደንበኞቻቸውን ለማጥመድና እንደ እንግዳው ፍላጐት የሚጠይቀውን ለማቅረብ ሁሌም ዝግጁ ናቸው፡፡ በአንዳንድ የከተማችን ሆቴሎችና እንግዳ ማረፊያዎች ውስጥ የሚሰሩ እንግዳ ተቀባዮች፣ (receptionists) አስተናጋጆችና የትላልቅ ቪላ አከራዮች የኔትዎርኩ አባላት ናቸው፡፡ አዲስ እንግዳ የመምጣቱ ዜና እነዚህ ደላሎች ጆሮ ለመድረስ ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ይበቃሉ፡፡ ከዛም ደላሎቹ ሥራቸውን ይጀምራሉ። በእንግዳው መውጫና መግቢያ ላይ መረቡ ይዘረጋል። አብዛኛውን ጊዜ የደላሎቹ መረብ አሣውን ሣያጠምድ አይመለስም። ከልጃገረድ እስከ ቤት ልጅ፣ ከቤት ልጅ እስከ የቡና ቤት ሴት ድረስ እንግዳው የጠየቀው ይቀርብለታል። በዚሁ የሴት ድለላ ተግባር ላይ የተሰማሩ ደላላዎች እንደነገሩኝ፤ በአሁኑ ወቅት በከተማችን ለገበያ የሚቀርቡ ልጃገረድ ሴቶች እየተበራከቱ ነው። ሴቶቹ በአብዛኛው ዕድሜያቸው ከ14-17 ዓመት የእድሜ ክልል ላይ የሚገኙ ተማሪዎች ናቸው፡፡ አልፎ አልፎም ከክፍለ ሃገር የሚመጡ ታዳጊ ልጆች የዚህ ድርጊት ሰለባ ይሆናሉ፡፡ ወደ አረብ አገራት ለመሄድ ከተለያዩ የአገራችን ክልሎች ይመጡ የነበሩት ታዳጊ ሴቶችም የእነዚህ ደላሎች ወጥመድ ውስጥ የሚገቡበት አጋጣሚ እንዳለ ይታወቃል፡፡

ልጃገረዶቹ ድንግልናቸውን በሽርፍራፊ ገንዘብ በደላላ ሸጠው ወዳሰቡበት ባህር ማዶ ይሻገራሉ፡፡ ይህ ወደ አረብ አገር ባቀኑ በርካታ ሴት እህቶቻችን ላይ ሲፈፀም የኖረ ሃቅ እንደሆነ ደላሎቹ ያለሀፍረት ይናገራሉ፡፡ ከዚህ በተረፈ በተለያዩ ማባባያዎችና ጉትጐታዎች ከቤታቸው የሚወጡ ከየትምህርት ቤቱ የሚወሰዱ ታዳጊ ሴቶች፤ ድንግልናቸውን ከእነሱ በእድሜ እጅግ ለሚበልጣቸው (አንዳንዴም ለወጣት ሀብታም ነጋዴዎች) በ10ሺዎች በሚቆጠር ብር ይሸጣሉ፡፡ ይህ ተግባር በስፋት የሚከናወንባቸው ሆቴሎችና እንግዳ ማረፊያዎች በተለይም ከአዲስ አበባ ወጣ ባሉ ከተሞች (ዱከም፣ ደብረዘይት፣ ሞጆና ናዝሬት… በብዛት ይጠቀሳሉ) በስፋት ይገኛሉ፡፡ በዚህ “የልጃገረዶች የድንግልና ግብይት” ውስጥ በብዛት ተሣታፊ የሚሆኑት የከተማችን ቱጃር ነጋዴዎችና አልፎ አልፎ ዲያስፖራዎች ናቸው፡፡

ቀይ፣ ጠይም፣ ጠቆር ያለች፣ ረዥም፣ ቀጭን፣ ቁመናዋ ያማረ… እንደ እንግዳው ስሜትና ምርጫ ተፈላጊዋን በደቂቃዎች ውስጥ መኝታ ቤት ድረስ ማምጣት ለደላሎቹ አዳጋች ሥራ አይደለም። ከውጭ አገራት ከሚመጡና ይህንን አይነት አገልግሎት በስፋት ከሚጠይቁ የውጪ ዜጐች መካከል አብዛኛዎቹ አረቦች እንደሆኑ በስራው ላይ የተሰማሩ ደላሎች ይናገራሉ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ሱዳኖችም በብዛት እንደሚመጡ እነዚሁ ደላሎች ገልፀውልኛል። ለረዥም አመታት ውጪ ኖረው ወደ አገራቸው የተመለሱ ዳያስፖራዎች፣ የተለያዩ የአፍሪካ አገራት ዲፕሎማቶችና በተለያዩ ስብሰባዎችና ሥራ ሰበብ አሊያም ለጉብኝት የኢትዮጵያን ምድር የሚረግጡ የውጪ ዜጐች ሁሉ የዚህ “አገልግሎት” ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ ከተማችን የምታስተናግደው አለማቀፋዊ ስብሰባ በሚኖርበት ወቅት የደላሎቹ ወይም የግብይቱ ኔትወርክ ይጨናነቃል፡፡

የአብዛኛዎቹ “አገልግሎት” ፈላጊዎች ጥያቄም “ቆንጆ የቤት ልጅ እፈልጋለሁ” የሚል ነው፡፡ ጥያቄያቸውን በአግባቡ መመለስ የቻለ ዳጐስ ካለ ክፍያ በተጨማሪ ወፈር ያለ ጉርሻ ማግኘቱም እርግጥ ነው፡፡ “አንዳንድ ጊዜ “የቤት ልጆች” ከገበያ የሚጠፉበት ወቅት አለ። እንዳልኩሽ ስብሰባዎች በሚኖርበት ወቅት ገበያው ስለሚሟሟቅ የቤት ልጆች በጊዜ ያልቃሉ፡፡ ስለዚህ ያለን አማራጭ ብዙም ያልተጐሳቆሉ ሴተኛ አዳሪዎችን እየፈለግን በቤት ልጅ ታርጋ ለገበያ ማቅረብ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ አንዳንድ ጊዜ ይባነንበታል፡፡ ሰዎቹ  የቤት ልጅና ሴተኛ አዳሪን የሚለዩበት የራሳቸው መንገድ አላቸው ብሎኛል ከገበያው ደላሎች አንዱ፡፡”

በከተማችን የተለያዩ ሥፍራዎች ቦሌ፣ ወሎ ሰፈር፣ ሳር ቤት፣ ሳሚት፣ መስቀል ፍላወርና መገናኛ አካባቢዎች የሚገኙ ቪላ ቤቶች ከነሙሉ የቤት ዕቃዎቻቸው ለቀናት፣ ለሳምንታትና ለወራት ከውጪ የሚመጡ እንግዶችን ይቀበላሉ፡፡ የእነዚህ ቤቶች የጥበቃ ሠራተኞች ከደላሎቹ ጋር በኔትዎርክ የተሳሰሩ ናቸው፡፡ ለሴቶቹ የሚከፈለው ዋጋ እንደ እንግዳው አይነትና እንደ ሴቷ የማስተናገድ ብቃት እንደሚለያይ ደላላው ይናገራል፡፡ ሴቷ እንግዳው በፈለገው መንገድና ሁኔታ ልታስተናግደው (ያፈነገጠ የወሲብ ጥያቄን ያካትታል) ፈቃደኛ ከሆነች ክፍያዋ ከፍ ይላል፡፡ በአብዛኛው ግን ለውጪ አገር ዜጐች የሚቀርቡ ሴቶች ለአንድ ምሽት ከ300-400 ዶላር ክፍያን ይጠይቃሉ፡፡ የቆይታ ጊዜያቸው የሚራዘምና እነሱም የሚመቻቹ ከሆነ ግን ክፍያው እንደየሁኔታው ሊለዋወጥ ይችላል። ለሁለትና ለሶስት ቀናት በነበራቸው ቆይታ እጅግ ተደስተው ከዋናው ክፍያ ጋር ተጨማሪ ቲፕ (በገንዘብም በአይነትም) ለምሳሌ ላፕቶፕ፣ ካሜራ፣ አይፎንና መሰል ውድ ዋጋ ያላቸውን ንብረቶች በስጦታ ሰጥተዋቸው የሚሄዱም አሉ። ከዚህ ባስ ሲልም ወደ አገራቸው እስከ መውሰድ የሚደርሱም ይኖራሉ፡፡ በከተማዋ የሚገኙ ትላልቅ የመቃሚያ ቤቶችን እንደ እጁ መዳፍ አብጠርጥሮ እንደሚያውቃቸው የሚናገረውና በዚሁ ሴቶችን በመደለል “ቢዝነስ” ላይ የተሰማራው ሌላው የላዳ ታክሲ ሾፌሩ ታዲዮስ፤ በአሁኑ ወቅት በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ የምትገኝን “የቤት ልጅ” አንጠልጥሎ ለወሲብ ገበያ ማቅረብ ለእሱ እጅግ ቀላል ሥራ እንደሆነ ይናገራል፡፡

“ሴቶቹ የብር ፍቅር ሊገላቸው ነው ዝም ብለሽ እኮ አንዳንድ ትላልቅ የቁንጅና ሣሎኖች፣ ካፌዎችና መዝናኛ ሥፍራዎች ብትሄጂ ሆን ብለው ለጠለፋ የሚወጡ የቤት ልጆችን ማግኘት ትችያለሽ፡፡ በየመቃሚያ ቤቱ ለዚሁ ተግባር የሚዞሩ ሴቶች ነፍ ናቸው፡፡ እኛ ደግሞ ፈላጊና ተፈላጊን ማገናኘት ነው ሥራችን። እነሱ ሲመቻቹ እኛም ይመቸናል” ይላል ታዲዮስ። በከተማዋ ካሉ ትላልቅ ሆቴሎች በአንዱ በእንግዳ ተቀባይነት የሚሰራው ፍፁም (ስሙ የተየቀረ) በሆቴሉ ውስጥ ከሚያርፉ እንግዶች አብዛኛዎቹ የተለያዩ አገር ዜጐች እንደሆኑ በመጠቆም፤ በሥራው ወቅት የሚያጋጥመውና እጅግ ያስመረረው ጉዳይ ግን የእነዚህን እንግዶች “ሴት አስምጣልን” ጥያቄ መመለስ እንደሆነ ይናገራል። የእንግዶቹን ጥያቄ መመለስ ካቃተው እንግዶቹ በአግባቡ እንዳልተስተናገዱ ለሆቴሎቹ ኃላፊዎች ከመናገር ወደ ኋላ እንደማይሉም ይገልፃል፡፡ ይህ እንዳይሆንም በእነ ታዲዮስ ኔትወርክ መታቀፍ ግድ ሆኖበታል፡፡ እንግዶቹ በዚህ ዓይነት መንገድ በከተማችን በሚጧጧፈው ምስጢራዊ የወሲብ ገበያ ውስጥ ተዋናይ ሆነው ቆይተው ወደ አገራቸው በሚመለሱበት ወቅት ከአበሻ ውብ ቆነጃጅት ጋር የፈፀሙትን የወሲብ ገድል እንደ ፌስ ቡክ፣ ትዊተር ባሉ የማህበረሰብ ድረገፆች ላይ በማስፈር ለዓለም ያስኮመኩማሉ፡፡ ጐበዝ! ወዴት እየተጓዝን ይሆን? ምስጢሩም ቢገለጥ ዝምታውም ቢበቃ አይሻልም ትላላችሁ፡፡ ምንም ቢሆን መወያየቱ አይከፋም እላለሁ፡፡(መታሰቢያ ካሣዬ – አዲስ አድማስ)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Social Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. kebere says

    December 8, 2013 12:47 pm at 12:47 pm

    minalbatim yihe wode mabkiaw medresachinin ayasayim tilalachihu?

    Reply
  2. Musie says

    December 8, 2013 11:00 pm at 11:00 pm

    Yetewaredachihu zegoch !!!

    Reply
  3. Gize Lekulu says

    December 9, 2013 10:06 am at 10:06 am

    Ere Besintu ENIKATEL? AYE ETHIOPIA!!!

    Reply
  4. aradaw says

    December 10, 2013 12:45 am at 12:45 am

    We had sexual exploitation in Ethiopia before, it came with modernization and spread with the Italian occupation of Ethiopia. but, in the last 22 years it reached to an alarming rate that threatens the moral, psychological and even to the survival as a nation. There are a lot of researches, articles in this issue but I will like to mention what happened after The Charities and Societies Proclamation (2009). This inhuman proclamation made a devastating impact on human right. I quote”Human rights work restricted in the law comprises, the advancement of human and
    democratic rights; the promotion of equality of nations, nationalities … peoples … gender and
    religion; the promotion of the rights of the disabled and children’s rights; the promotion of
    conflict resolution or reconciliation; the promotion of the efficiency of the justice and law
    enforcement services” The sexual exploitation we see is a human right question, the solution lies in teaching families, youth their right as human being. Teaching women their right in a society. The NGO can work in activities in the promotion of and protection of right and freedom of citizen, family and above all women. However this proclamation disabled the organization from functioning and we see the spread of the activities mentioned. We have deep rooted problem with the dictatorial and ethnic based EPRDF/TPLF that does not care for humanity in general. This regime incapacitated the nation not only with the mentioned proclamation only, one can also mention Anti-Terrorism Proclamation in 2009 that restricts the ability of the nation to criticism the government.

    The question mentioned on the sexual exploitation of women and the spread of prostitution can only be answered wit the removal of the TPLF/EPRDF government. They have already done enough damages in all aspect of human life. The most recent misery from Saudi Arabia is a reason to say enough is enough.

    Reply
  5. frezer says

    December 10, 2013 04:37 am at 4:37 am

    My opinion is on all articles and such books on this matter. Its good to tell but should be carfully written. Because it should not persuade others. Most of the time These articles shows how fruitfull this bussines is. It even declares the price. I rather think its a promotion .
    Do you know how many girls are out there struggling to win their life. lot more girls who doesn’t have income, living with family.
    So please let take care when we write such articles, it shouldn’t persuade others!

    Reply
  6. tesfaye g w says

    December 12, 2013 11:54 pm at 11:54 pm

    ነገሩን ባልደግፈውም የባለ (ፑቲኻን ) ገቢና ወጪ ልታውራርድ መፈለግህ ቅናት ቢጤ ይመስላል .ወይም ስራ ፈት ወርሬኛ.

    Reply
  7. tesfaye g w says

    December 13, 2013 12:22 am at 12:22 am

    ሰውን በግለሰብ ደረጃ መከታተል ማንኛውም ግለሰብ ወንድም ሆነ ሴት በፍለገው የሕይወት መንገድ ሕይወቱን የመምራት መብት እንዳለው እንዲሁም ተፈጥሮያዊ መብቱ መሆኑን አለመረዳት ይመስለኛል .

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule