ታ ሪኩ ገናና፤ ስራው የለው አቻ
ላ ሰበበት ጉዳይ፤ የሌለው ፍራቻ
ቁ ጣን ቂም በቀልን፤ ያጠፋ ጥላቻ
ማ ንዴላ ታላቁ፤ የነፃነት ጮራ
ን ጥረ መብረቅ ሆኖ፤ አፍሪካን ያስጠራ
ዴ ሞክራሲ እንዲያብብ፤ ተስፋውን ሰንቆ
ላ ሰበው አላማ፤ ቆሞ ነበር ታጥቆ
የ ህይወት ዘመኑ፤ ቢሆንም መራራ
ነ ፃነት አላብሷል፤ ስሙን የሚያስጠራ
ፃ ድቅ የሆነ ሰው፤ እያለ በሕይወት
ነ ውና ተግባሩ፤ መልካም ነገር መስራት
ት ዕዛዙን ፈጽሟል፤ በእድሜው ዘመናት
ዓ ለም መቆያ ናት፤ ተቀባይ እንግዳ
ባ ህሪዋ መራር፤ ወሳጅ በሞት እዳ
ት ልቅ ትንሽ ሳትል፤ ድንገት የምትከዳ
ና ልን አይባልም፤ ማንዴላም ተመለስ
ቸ ሩ ፈጣሪያችን፤ የታላቁን ሰው ነፍስ
ው ለታ ይክፈላት፤ ወደሱ ስትደርስ
Leave a Reply