• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ማዲባ አረፉ!

December 6, 2013 06:55 am by Editor 2 Comments

ደቡብ አፍሪካን ከ1994 – 1999 (እኤአ) በፕሬዚዳንትነት የመሩት ኔልሰን ሮሊህላህላ ማንዴላ ከረጅም ጊዜ ህመም በኋላ ህዳር 26፤ 2006ዓም በ95 ዓመታቸው አርፈዋል፡፡

በፕሬዚዳንትነት መንበር ላይ ከመቀመጣቸው በፊት ለ27 ዓመታት ታስረዋል፡፡ ለነጻነት በተደረገው ትግል እስከ 156 በሚደርሱ የተለያዩ “ወንጀሎች” ተከስሰው እንደነበር ይታወቃል፡፡ ራሱ አሸባሪ የነበረው የአፓርታይድ አገዛዝ “ወንጀለኛና አሸባሪ” በማለት ስም ከሰጣቸው በኋላ አሜሪካም ተመሳሳይ እርምጃ በመውሰድ “አሸባሪ” የሚለውን ስም ለጥፋባቸው ለረጅም ዓመታት ቆይታለች፡፡ ከዚህም አልፎ ማንዴላን ጨምሮ በርካታ የኤኤንሲ አመራሮችንና አባላትን በአሸባሪነት ዝርዝር ውስጥ በማስገባት ለተለየ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር (ለተባበሩት መንግሥታት ዓይነት ስብሰባ) ወደ አሜሪካ የመግቢያ ቪዛ ሲከለከሉ ቆይቷል፡፡

ሁኔታው በዚህ መልኩ ቆይቶ የቪዛ ዕገዳው እንዲነሳ የአሜሪካው ምክርቤት ባወጣው ሕግ ላይ ፕሬዚዳንት ቡሽ ፊርማቸውን በማኖር በሕግ እንዲጸድቅ እስካደረጉበት ሐምሌ 2008ዓም (እኤአ) ድረስ ማንዴላን ጨምሮ በርካታ የኤኤንሲ አመራሮች የአሜሪካንን ምድር መርገጥ አይችሉም ነበር፡፡

ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከአባት አልፈው “እምዬ” በመባል እንደሚጠሩት ምኒልክ፤ ደቡብ አፍሪካውያንም ተወዳጁን መሪያቸውን “ማዲባ” (አባት) በመባል ይጠሯቸው ነበር፤ “father of the nation” የሚለው መጠሪያ ከአገራቸው አልፎ በመላው አፍሪካ የማንዴላ ልዩ መጠሪያቸው ሆኖ ቆይቷል፡፡

ማንዴላን ለዚህ አይነት የተወዳጅነት ክብር ያበቃቸው የመሃትማ ጋንዲን ዓይነት መርህ በመከተል አገራቸውን ከደም መፋሰስና ዕልቂት በመታደጋቸው ነው፡፡ ህንዳውያኑም ጋንዲን “መሃትማ (እጅግ ክቡር፤ የላቀ ነፍስ)” ከማለት አልፈው “ባፑ” (አባት) በማለት ይጠሯቸው ነበር፡፡ ከዚህም አልፎ “father of the nation” የሚለው መጠሪያ ለእርሳቸውም ተሰጥቷቸዋል፡፡mandela 3

Long Walk to Freedom በተሰኘው ግለታሪክ መጽሐፋቸው ላይ ማንዴላ ከእስር ከተለቀቁ በኋላ በዓለም ዙሪያ ስላደረጉት ጉብኝት በመጥቀስ እንዲህ ብለው ነበር፡፡ “በሃሳቤ ውስጥ ኢትዮጵያ ሁልጊዜ ልዩ ስፍራ አላት፤ በፈረንሳይ፣ በእንግሊዝ እና በአሜሪካ ያደረኩት ጉብኝት ቢደመር እንኳን በኢትዮጵያ ያደረኩት ጉብኝት ከሁሉም በላይ የሳበኝና የላቀ ነው፡፡ ምክንያቱን ጉብኝቱ መነሻዬንና ከየት እንደመጣሁ የሚያሳየኝ እንዲሁም አፍሪካዊ ተብዬ እንድጠራ ያስቻለኝን ሥረመሠረት ቆፍሮ የማግኘት ያህል ነው፡፡”

አገራችን ላለችበት ከፍተኛ ቀውስ የማንዴላን ዓይነት ሁሉን አቻችሎ ወደ ዕርቅ የሚያመጣ፤ ጉዳት ቢደርስበትም እንኳን ራሱን ዝቅ በማድረግ በቅንነትና ልበሰፊነት የአገሩ ጥቅም በማስቀደም አገራችንን ከገባችበት የዘር ጥላቻና ደም መፋሰስ የሚታደግ አባታዊ መሪ የሚያስፈልገን ወቅት ቢኖር አሁን ነው፡፡

የዛሬ 17 ዓመት ገደማ ማዲባ እንዲህ ብለው ነበር፤ “ሞት መቼም የማይቀር ነገር ነው፤ አንድ ሰው ለሕዝቡና ለአገሩ መደረግ አለበት ብሎ የሚያምነውን ካደረገ በኋላ ወደ ዕረፍቱ በሰላም መሄድ ይችላል፡፡ የምችለውን ጥረት በማድረግ ይህንን ተግባር ፈጽሜአለሁ ብዬ አምናለሁ፤ ስለዚህ አሁን ለዘላለም አርፋለሁ፡፡”

አገራችን እንዲህ ዓይነት የሞራል ብቃት ያለው፤ ከተራ መሪ በላይ የሆነ፤ በምናብ የሚመራ ሳይሆን አርቆ የሚያስብ፤ ልቡ በጥላቻና በቂም የጠቆረ ሳይሆን በቅንነት የተዋበ “አባት” የሚያስፈልጋት ጊዜ አሁን ነው፡፡

ማንዴላን ስንሰናበት “የእኛስ ማዲባ ማን ይሆን?” ብለን እንጠይቃለን፡፡


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. በለው! says

    December 7, 2013 06:59 pm at 6:59 pm

    ወያኔ/ህወአት/ኢህአዴግ የትልቅን ሰው ሞት የመጨረሻ ዜና ? የሌላው ሀገር እውነተኛ ዘገባና ሀዘን!?
    http://www.ethiotube.net/video/28572/ETV-News–ETV-reporting-the-passing-of-Nelson-Mandela–December-06-2013
    *ድንቄም!የዘር መድሎ ትግል! ህወአት/ኢህአዴግ ግን የዘር መድልዎ አፓርታይድ ማፈናቀልን የሜንጫ መጨፋጨፍን ታስፋፋላችሁ። ህወአት/ወያኔ/ኢህአዴግና ሆድዳር አድርባይ ምሁር እምዬ ምንይልክ አይታወስ ብላችሁ ለምን ለማንዴላ ተቆላችሁ? አስመሳይ! ማንዴላ ኢትዮጵያን ለማየት የመረጠው ለመልስና ለኅይለማርያም አደለም!ለትግል አጋሩ ለኮ/መንግስቱ ኅ/ማርያምና ለእውነተኞች ኢትዮጵያን ነው። ነጭን ድል የነሳው የጥቁር ህዝብ ኩራት፣ አንበሳው ትውልድ በእቴጌ ጣይቱ ተመክሮ በእምዬ ምንይልክ ጥሪ ክርስቲያን ሙስሊሙ በማርያም ተምሎ የጊዮርጊስ ታቦትን አስቀድሞ ብሔር ቋንቋ ሳይል አድዋ ላይ ነው ድል በኅብረት ተሠራው!።
    *የህወአትሻቢያ ቤተሰቦችማ ከኋላ አሻጥር ሲሰሩ፣ ሲገድሉ ሚስጠር ለጠላት ሲያቀብሉ፣ንብረት ሲያወድሙ፣የወታደር ስንቅ በመርዝ ሲበክሉ፣ ለጠላት ቤተሰብ እንቁላል አቅራቢ ሹምባሽ ነበሩ። እናንተም የባንዳ ልጅ የልጅ ልጆች በኤርትራም በሱማሊያም ጦርነት ተበቀላችሁን ‘የዘሬን ብተው ይዘርዝረኝ አላችሁ!” እናንተም በዛን ዘመን ድልድይ አፍራሽ፣ ተገንጣይ፣ ወንበዴ ነበራችሁ፤በስምምነት ፸ሺህ በላይ ድሃ ልጅ ፈጃችሁ አስፈጃችሁ። ዛሬ ተገልብጣችሁ”በልማታዊ መንግስት”ሥም ሀገር ቆራረሳችሁ ትውልድ አፈናቅላችሁ አሰደዳችሁ ለባዕድ ሸጣችሁ።

    *ህወአት/ወያኔ/ኢህአዴግ…ሠላም፣ ፍቅር፣ አንድነት፣ ዕርቅ አንድነትና በጋራ እድገት የሚባል ነገር ሁሉ ጠላቱ ነው። ሽብር፣ አመጽ፣ ደልድይ ማፍረስ፣ ንብረት ማውደም፣ ማሠር፣ መደብደብ፣ መግደል፣ ቢሆን አንደኛ ነው። በዓለም የኒልሰን ማንዴላ ህልፈተ ሕይወት ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ዘር ቀለቀም ሳይለይ ሰበር ዜና! አሳዛኝ ዜና!ትልቅ ሀዘን! ታላቅ ሰው ኣለም አጣች! ሲባልና ሲዘገብ የወሮበላ ሀገር…የጋጠ ወጥ ሥርዓት ውሸት ከሞላው ዜና “በመጨረሻም!” ብሎ የክቡር ሰው ሞት ይዘግባል። ለምን? ክብር አያቁማ! ሀገር የለማ! ምሁር የለም! ታጋይ ምሁር ጠበብት እኛው የሞቱ ጠ/ሚኒስትር ብቻ ናቸው። በባንዲራ ጠቅልለው ጥለው ታጋይ አይሞትም!! ብለው በፋውንዴሽን እያሳበቡ የውጭ ምንዛሪ እያቀባበሉ ንግድ አጣጡፈዋል “ቁጥር ሁለት ፋውንዴሽንም “ሀበሻ ፋውንዴሽን” የራዕይ ፋውንዴሽን፡ እያሉ በድሃ ሀገርና ሕዝብ ላይ ያሾፋሉ።
    *ታላቁ መሪ መሌ ዜናዊ ምን ደላት ያም አፈር ያም ድንጋይ ጫነባት በቀን አበል ተለቀሰለት፣ ኪራይ ስብሳቢ፣ ሙሰኛ፣አድርባይ በስሙ ከበረበት በዚያች ፵፻፪፻ብር የወር ገቢ ተቆራፍዶ ከኮብል አስቶን አንጣፊ ደሞዝ በታች ተቀጥሮ የሀብታም ልጅነቱን ጥሎ ድሃ ልሁን ብሎ በረሃ ገባ !? ለዓለም ምሳሌ የሆነ፣ እየተራበ ፫ነጥብ፫ ቢሊየን ዶላር መቆጠብ የቻለ ታጋይ! አትራፊ መሪ ! “በአባታችን ይጠራል እንጂ ምንም አያገናኘንም የሚሉት እህታቸው ጠላ ሻጭ ወንድማቸው ጢቢኛ ይሸጣል! ምድረ አድርባይ፣ ሆድአደር፣ የጎጠኛ፣ የዘረኛ፣ በኅብረት ሀገር አጥፊ፣ትውልድ አምካኝ፣ ባንዳ ሁሉ ባነር እየወጠረ በጸይ መነጽር ተሸፍኖ ፎቶግራፍ ተሸክሞ እየዞረ በሰውዬው ሥም ይነግዳል። ሌባ በለው! ለራሱ መሪ ክብር የሌለው፣ለራሱ ታሪክና ሉዓላዊነት ለዜጋው የማይቆሮቀር ለሰው ሀገር ጅግና ጭራ መቁላትም የሰውን ክብር ማሳነስም በጣም አሳፋሪ ነው። *ሠርታችሁ ዓላማን ተግብሩ! ቀብሮ ከማልቀስ ኖሮ ማስደሰት!”

    * የአፋር ግመል የሚያውቀውን የሀገር ዳርድንበር፣ ሉዓላዊነት፤ ኅብረሔርና ሰንደቅ የጠፋችሁና ያጠፋችሁ አውርቶ አደሮች ሆይ፣! ብሔሮቻችሁን አታሰድቡ! መልካም ሥም ከመቃብር በላይ ነው” ሲባል ሠምታችሁ በዘጠኙም ክልል መለስን ቀብራችሁ ‘ታጋይ አይሞትም!’ እያላችሁ ታናፋላችሁ? ወይ ጥጋብ! ነፍሳችሁ አይማር!!

    Reply
  2. Mulat Arsi says

    December 7, 2013 09:26 pm at 9:26 pm

    I fear that we can’t get our Madiba in a short period as creating such visionary leader requires us to bring about radical change in our attitude. If we wish to have our Madiba, at least, we have to stop killing our icons and learn to respect each other and ideas of others and above all we have to make peace with our past and put principle first.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ባልደራስ የአገርን ደኅንነት አደጋ ላይ በመጣል ሊጠየቅ ይገባዋል ተባለ July 1, 2022 09:23 am
  • “ሚካኤል ችግኝ ነው። … ችግኝ ይተክላል” ቴዲ አፍሮ June 29, 2022 03:30 am
  • “የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች (22ቱንም) የቀበርኩት እኔ ነኝ” አቶ መሀመድ የሱፍ ከምዕራብ ወለጋ June 28, 2022 01:07 pm
  • የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ June 20, 2022 11:34 pm
  • “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል June 12, 2022 07:09 pm
  • የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው June 12, 2022 06:21 pm
  • ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል June 12, 2022 05:40 pm
  • የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ June 12, 2022 05:35 pm
  • በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ June 10, 2022 09:13 am
  • ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት June 8, 2022 12:59 pm
  • ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር June 8, 2022 11:53 am
  • እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ? June 8, 2022 05:59 am
  • ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ June 7, 2022 01:11 am
  • “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ” June 5, 2022 06:58 pm
  • በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ May 30, 2022 02:20 am
  • የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ May 29, 2022 04:01 pm
  • “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!” በሚል ቁጭት ነው እየሠራን ያለነው May 29, 2022 01:04 pm
  • “ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መርህ ለአማራ ገበሬዎች የግብርና ሜካናይዜሽን ተሰጠ May 29, 2022 02:02 am
  • ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል May 27, 2022 02:51 am
  • “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ May 27, 2022 01:40 am
  • ትግራይን አገር እናደርጋለን፤ “በውይይት እና በጦርነት” ሁሉንም ጉዳይ እንቋጫለን – የወንበዴው መሪ ደብረጽዮን May 26, 2022 09:18 am
  • “ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ተዋጊ ዶክተሮች” May 26, 2022 08:19 am
  • ወደ ትህነግ ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ May 25, 2022 01:57 am
  • የጦርነቱ ስትራቴጂያዊ እውነታዎች May 19, 2022 09:37 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule