የጎልጉል ጥብቅ ማሳሰቢያ! ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ዋናው ዓላማ የሕዝብ እንደመሆኑ በጨዋነት የሚላኩልንን ጽሁፎች የምናትም መሆናችንን ስንገልጽ ቆይተናል፡፡ ሆኖ ግን አልፎ አልፎ የሚላኩልን ጽሁፎች በግለሰብ ዙሪያ ያጠነጠኑ ከመሆናቸው ባሻገር ምንም እንኳን ጸያፍ ቃላትን በግልጽ የሚታይባቸው ባይሆንም የሚሰነዘሩት ሃሳቦች ግን የግለሰቦችን ሰብዕና የሚነካ ከመሆኑ ባሻገር በስራችን ላይ ከፍተኛ ውስብስብ ነገር የሚፈጥርና ወደ አልተፈለገ እንካሰላንቲያ የሚመራ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ በመሆኑም በእንደዚህና መሰል ጽሁፎች ላይ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ለየት ያለ የኤዲቶሪያ ፖሊሲ በመጠቀም ጽሁፎችን እንደሁኔታው እያየን የምናትም መሆናችንን እንገልጻለን፡፡ በተለይ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አስተያየት ዙሪያ የሚላክልንን ማንኛውንም ጽሁፍ የማንቀበል መሆናችንን እንገልጻለን፡፡ በጉዳዩ ለመነጋገር … [Read more...] about “ያላወቂ ሳሚ … ይለቀልቃል”
Archives for September 2013
የተቃውሞ ፓርቲዎች ሠላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ ከ 33ቱ ፓርቲዎች ጋራ በመሆን ለዛሬ በመስቀል አደባባይ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በፖሊስ ክልከላ የአንድነት ጽ/ቤት በሚገኝበት ቀበና መካሄዱ ተገለፀ። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ሰልፉን ተከታትሎ ባደረሰን መረጃ መሰረት እጅግ በርካታ ሠላማዊ ሰልፈኞች ሠልፉን ለማከናወን ወዳቀዱበት መስቀል አደባባይ እንዳይሄዱ ፖሊስ መንገዱን በመዝጋት ተከላክሎዋል። ከ ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ጋ ያደረግነውን ቃለ መጠይቅ ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል። አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ ከ 33ቱ ፓርቲዎች ጋራ በመሆን ለዛሬ በመስቀል አደባባይ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በፖሊስ ክልከላ የአንድነት ጽ/ቤት በሚገኝበት ቀበና መካሄዱ ተገለፀ። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ሰልፉን ተከታትሎ ባደረሰን መረጃ መሰረት እጅግ … [Read more...] about የተቃውሞ ፓርቲዎች ሠላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ
ሰላማዊ ሰልፉ ቢታገትም፣ የተሳካ ሕዝባዊ ንቅናቄ ነበር!
አንድነት ፓርቲ ከ33ቱ ፓርቲዎች ስብስብ ጋር በመሆን ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ለማድረግ ያቀዱት ሰላማዊ ሰልፍ በገዢው ፓርቲ (መንግስት) ክልከላ ሠልፉ ሊደረግበት ወደነበረው መስቀል አደባባይም ሆነ በአማራጭ ነት ያቀረቡት 9 አደባባዮች እንዳይንቀሳቀስ ተደርጎ ከአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት እስከ ቀበና አደባባይ ባለው አስፋልት ላይ ቁጥሩ ከ80 ሺህ በላይ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተገኙበት ደማቅ ሕዝባዊ ንቅናቄ ተደርጓል፡፡ ለዚህ ደማቅ ሕዝባዊ ንቅናቄ የአንድነት ፓርቲና የ33ቱ ፓርቲዎች አመራሮች አባላትና ደጋፊዎች ያደረጉት ያላሰለሰ ጥረትና ሕዝቡ የመንግሥትን ፀጥታና የፖሊስ ኃይሎች ማስፈራራት አልፎ የላቀ አዎንታዊ ምላሽ ከፍተኛ ድርሻ አበርክተዋል፡፡ የአንድነት ፓርቲና የ33ቱ አመራር ህዝቡ ለሰጠው አመርቂ ምላሽ ከፍ ያለ ምስጋና እያቀረቡ፣በቀጣይ ለሚደረገው ወሳኝ ትግል ታላቅ … [Read more...] about ሰላማዊ ሰልፉ ቢታገትም፣ የተሳካ ሕዝባዊ ንቅናቄ ነበር!
“መስቀል የሚያቃጥል (አይደለም)”
በአቃቂ ቃሊቲ ገላን ጉራ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ባለፈው ነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ ከሠማይ ወረደ ስለተባለው መስቀል ቅዱስ ሲኖዶስ ውሣኔ እስኪያስተላልፍ ህዝቡ በትዕግስት እንዲጠባበቅ የአዲስ አበባና የጅማ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ አሣሠቡ፡፡ “መስቀል ከሠማይ ወርዷል አልወረደም? ትክክለኛ ነው አይደለም?” የሚለውን ለመመለስ የግድ ቅዱስ ሲኖዶሡ ጉዳዩን መርምሮ ውሣኔ ሊያስተላልፍበት ይገባል ያሉት ብፁዕነታቸው፤ ይህን ለማድረግም ጉዳዩን ለቅዱስ ሲኖዶሱ ቋሚ አባላት እንዳሣወቁ ተናግረዋል፡፡ መስቀሉ እንደተባለው ከሠማይ የወረደ አለመሆኑ ከተረጋገጠም የቤተክርስቲያኒቱ ሃላፊዎች ይጠየቁበታል ብለዋል-ብፁዕነታቸው፡፡ መስቀሉ ከሠማይ ወረደ በተባለ በ4ኛው ቀን ነሐሴ 27 ቀን 2005 ከሠአት በኋላ ወደ ስፍራው በማቅናት ተገቢውን የፀሎት ስርአት ከካህናቱና … [Read more...] about “መስቀል የሚያቃጥል (አይደለም)”
ከአንድነቶች ሶስት ወር ዘመቻዎች የተማርናቸው!
የህውሃት/ኢህአዴግ ጠንካራ ጎኑ እስከ ጥርሳቸው ድረስ የታጠቁት ፖሊስ፣ ድህንነት፣ ምድር ጦር፣ አየር ኃይል፣ አየር ወለድ፣ ካድሬ እና ቅጥረኛ ወርበሎችን ያካትታል። የሚያውቀው የፖለቲካ ትግል ዘዴ በጫካ መገዳደልን እንጂ በከተሞች ሰላማዊ ትግሎች ማድረግ አይደለም። ስለዚህ ሰላማዊ ትግል ህውሃት/ኢህአዴግን በማያውቀው የትግል ሜዳ፣ የትግል ዘዴ እና በደካማ ጎኑ እንዲታገል እንደሚያስገድደው እና የህዝብ ድጋፍ የሚያሳጡ ስህተቶች እንደሚያሰራው የአንድነቶች የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ ወለል አድርጎ አስተምሮናል። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ) … [Read more...] about ከአንድነቶች ሶስት ወር ዘመቻዎች የተማርናቸው!
ሀገር ማለት
በዚህ ርእሰ ጉዳይ ላይ አስቀድሞ ደራሲ በዓሉ ግርማ በኋላም ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ ግጥሞቻቸውን ጽፈው ነበር፡፡ ሌላም የጻፈ ይኖራል፡፡ ነገር ግን እነኝህ የሥነ-ጽሑፍ ሰዎች ግጥሞቻቸውን ሲጽፉ የተቆነጸለ ወይም የተሳሳተ ትርጉም ሊያሰጥ በማያስችል ሁኔታ ግጥሞቻቸውን ባለመጻፋቸው እንደምገምተው እነሱም ሊሉ ባልፈለጉት መንገድ ተተርጉሞ የቅጥረኞች መጠቀሚያ እስከመሆን ድረስ በቃና ሕዝብን ለማደናገሪያ አገለገለ፡፡ ከሕዝቡ ጥቂት የማይባል ወገንም በመወናበድ ይሄንን የተሳሳተ ትርጉም ይዞ ማንጸባረቅ ያዘ፡፡ ይህም መሆኑ ሀገር በሕዝብ ልብ ውስጥ የነበራት ቦታና ትርጉም ከመዛባቱም ባሻገር በወደፊት የሀገር ህልውና ላይ ከባድ አደጋ የጋረጠ ሆኖ ቁጭ አለ፡፡ እናም እንደዜጋ አሳሰበኝና ይሄንን የተሳሳተ ትርጉም ለማረም የሀገርን ትርጉም ሳይቆነጸል ሳይጎነጠል ለማስፈር ተገደድኩና ይህችን ግጥም … [Read more...] about ሀገር ማለት
የደብሪቱ ወተት
ሰፈራችንን መሀል ለመሀል ሰንጥቆ ከሚያልፈው መንገድ በስተቀኝ ሃያ አንድ መኖሪያ ቤቶች ይገኛሉ። ከነዚህ ቤቶች ነዋሪዎች ውስጥ ከአብዛኛዎቹ ጋር የስጋ ዝምድና አለን። በተለይ በአንድ ግቢ ውስጥ የምንኖረው ስምንት ቤተሰቦች ደግሞ የቅርብ - በጣም የቅርብ ዘመዳሞች ነን። በነዚህ ቤቶች ውስጥ አያቶች፣ እናቶች፣ አባቶች፣ አክስቶች፣ አጎቶች፣ አማትና አማቾች ሲኖሩ ከሁሉም የተውጣጣን የልጅ ልጆችም እንገኛለን። ከአጎቶቻችንና ከአክስቶታችን መካከል ሁለቱ ከኛ ዕድሜ ብዙ ስለማይርቁ ቀረቤታችን የጎላ ነው። አሰግድ ገ/እግዚአብሔርና ... አሰግድ ቀልደኛ ነው። በማንኛውም ጊዜ በትንሹም በትልቁም ነገር እራሱን አዝናንቶ ሌላንም ለማስደሰት ይጥራል። የወጣለት ፀሐፊም ነው። እንደዛሬው የትያትር ጥበብ ሳይስፋፋ በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ከሚሉ ጥቂት ተዋናዮች መካከልም አንዱ ነበር። አሰግድ አጎቴ … [Read more...] about የደብሪቱ ወተት
10 American Foods that are Banned in Other Countries
Americans are slowly waking up to the sad fact that much of the food sold in the US is far inferior to the same foods sold in other nations. In fact, many of the foods you eat are BANNED in other countries. Here, I’ll review 10 American foods that are banned elsewhere. (Click here to read) … [Read more...] about 10 American Foods that are Banned in Other Countries
የልማት መጀመሪያው ሰብዓዊ መብትን ማክበር ነው!
የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ:: … [Read more...] about የልማት መጀመሪያው ሰብዓዊ መብትን ማክበር ነው!
“ወሲባዊ ጂሃድ (ጂሃድ አል-ኒቃ)” በሶሪያ!
የቱኒዚያ ሴቶችና ልጃገረዶች በሶሪያ የአሳድን መንግሥት እየተፋለሙ ከሚገኙት እስላማዊ አማጺያን ጋር “ወሲባዊ ጂሃድ” በመፈጸም በጦርነቱ ላይ ተሳትፏቸውን እየገለጹ መሆናቸው ተነገረ፡፡ በሌላ በኩል በዚሁ ጦርነት ላይ በሳውዲ አረቢያ የሞት ፍርድ የተበየነባቸው ወንጀለኞች እንዲሳተፉ እየተላኩ መሆናቸው ተረጋገጠ፡፡ በያዝነው የመስከረም ወር መጀመሪያ አካባቢ የቱኒዚያው የአገር ውስጥ ሚኒስትር ሎትፊ ቢን ጄዱ በአገሪቱ ፓርላማ ፊት ቀርበው እንደተናገሩት በጦርነቱ ከፍተኛ መስዋዕትነት እየከፈሉ ለሚገኙት ተዋጊዎች ማደፋፈሪያ እንዲሆንና በትግሉ የነርሱንም ድርሻ ለመወጣት የቱኒዚያ ሴቶችና ልጃገረዶች ራሳቸውን በ“ወሲባዊ ጂሃድ” በመስጠት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ በአረቡ ዓለም በሚገኙ የዜና ማሰራጫዎች በሰፊው የተዘገበው ይህ ዜና እንደሚያስረዳው ሚኒስትሩ ጉዳዩ አሳሳቢ ደረጃ ላይ … [Read more...] about “ወሲባዊ ጂሃድ (ጂሃድ አል-ኒቃ)” በሶሪያ!