መለስ ዜናዊ ሆን ብለው ለፖለቲካ ሚዛን መጠበቂያ ሲገለገሉበት በነበረው "የሙስና ባህር" ያልተነከረበት የለም። ባህሩ ውስጥ ያልዋኘ የለም። ከባህሩ ራሳቸውን ያገለሉ ጥቂቶች ቢኖሩም ወ/ሮ አዜብ መስፍን ግን የባህሩ ዋናው አጥማቂና የውሃው ባለቤት እንደሆኑ በርካታ ምስክሮች አሉ። አቶ መለስ "ውርሳቸውን/ሌጋሲያቸውን" ትተው ካለፉ በኋላ አገሩን አከርፍቶት የነበረው የሙስና ባህር በስንጥር መነካካት ተጀመረና አሁን ቁንጮዎቹ ግድም ደርሶ እያሸበረ ነው። ይህንኑ የሙስና ማዕበል ተከትሎ የባለቤታቸውን ውርስ ታኮ ያደረጉት ወ/ሮ አዜብና በተሸናፊው የፖለቲካ መስመር ያሉ ሁሉ ተሸብረዋል። አንዳንድ ጥቆማዎችና የህዝብ አስተያየቶች እንደሚያመለክቱት ወ/ሮ አዜብ ታውከዋል። ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሃላፊዎችና ከነሱ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ከዋሉት "ባለሃብቶች" መካከል ከወ/ሮ አዜብ … [Read more...] about አዜብ መስፍን ይታሰራሉ?
Archives for September 2013
ሰላማዊ ትግል በካዮች እና መከላከያ ምክሮች!
ህውሃት (መንግስት) ህዝብን የሚገዛበት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ አቅሙ ከሰማይ የሚወርድለት ወይንም በተፈጥሮው ከውስጡ የሚንጠፈጠፍለት ሳይሆን ከህዝብ የሚነጭለት ነው። ፖሊሱም፣ ደህንነቱም፣ የኢቲቪ ሰራተኛውም፣ የቃሊቲ አስተዳዳሪውም፣ የኢምባሲ ሰራተኛውም፣ ወ.ዘ.ተ. ከህዝብ የሚመለመሉ ናቸው። ለህውሃት በደሞዝ ክፍያ ያገልግሉ እንጂ የሰዎቹም ሆኑ የደሞዛቸው ምንጭ ህዝብ ነው። በግብር እና በሌሎች ምክንያቶች ከህዝብ የሚሰበሰብ ነው ደሞዛቸው። አሊያም በኢትዮጵያ ህዝብ ስም ከውጭ በዕርዳታ፣ በብድር ወይንም በሌሎች ስምምነቶች የሚያገኘው ነው ደሞዛቸው። የፋብሪካ፣ የኢንዱስትሪ፣ የመገናኛ፣ የትራንስፖርት፣ የአየር መንገድ፣ የመድህን ሰራተኞች፣ የንግድ እና አገልግሎት ድርጅቶች ወ.ዘ.ተ. በሙሉ ስራ ቢያቆሙ ከህዝብ መንጭቶ ወደ ህውሃት የሚፈሰው ሃብት ብር ይቋረጣል። ህውሃት … [Read more...] about ሰላማዊ ትግል በካዮች እና መከላከያ ምክሮች!
በመንግስታዊ ውንብድና ትግላችን አይገታም!!!!!
ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም. ባካሄደው ታላቅ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለመንግሥት ያቀረባቸው ጥያቄዎች አስፈላጊው ምላሽ እንዲሰጣቸው በመጠየቅ ይህ ካልሆነ ግን ከሦስት ወር በኋላ ተቃዉሞውን ከፍ ባለ ደረጃ እንደሚያቀርብ በመጋለፅ ሰልፉን አጠናቋል፡፡ ለተነሱት ጥያቄዎች የተገኘ ምላሽ ባለመኖሩ ፓርቲው ለሕዝብ በገባዉ ቃል መሠረት ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም. ታላቅ የተቃዉም ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሔድ በመወሰን በሕግም ሆነ በሥራ የሚያስፈልጉ ነገሮችን በማጠናቀቅ እለቱን በመጠበቅ ላይ እያለ ምንም አይነት መለዮ ባልለበሱ ግለሰቦች የሚመራ የፖሊስ መለዮ ለባሽ ታጣቂዎች ከሕግ ውጭ ነሐሴ 25 ቀን 2005 ዓ.ም. ከምሽቱ 12 ሰዓት አካባቢ የፓርቲውን ቢሮ ጥሰው በመግባት ፓርቲው ይጠቀምባቸው የነበሩ የቅስቀሳ ቁሳቁሶችና ሌሎች የፓርቲውን ንብረቶች ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ … [Read more...] about በመንግስታዊ ውንብድና ትግላችን አይገታም!!!!!
ፖለቲካ ሳይንስ ነው ወይ? ፖለቲካ ምሁራዊነት ያስፈልገዋል ወይ?
መግቢያ በዚህ አርዕስት ላይ ለመጻፍ ከአሰብኩ ረዥም ጊዜ ሆነኝ። እንደሚታወቀው አንድ ጥናታዊ ጽሁፍ ለማቅረብ ቀላል አይደለም። የመንፈስ ርጋታን የሚጠይቅ ብቻ ሳይሆን፣ ለአንባቢ የሚቀርበው ጽሁፍ ከርስ በርስ ቅራኔዎች የተላቀቀና አሳማኝ እንዲሆን አድርጎ ለመጻፍና ለማስነበብ ረዥም ጊዜን ይፈጃል። ብዙ ዕውቀትንና ምርምርን ይጠይቃል። ተመራምሮና የተለያዩ አስተሳሰቦችን አወዳድሮና አመዛዝኖ ለአንባቢ አንድ የሚያረካና እንደመመሪያ ጥናት ለማቅረብ ረዥም ጊዜ ብቻ ሳይሆን ቢያንስ የሶስትና የአራት ሰዎችን የስራ ክፍፍል ይጠይቃል። አንድ ሰው ብቻ የሚጽፍ ከሆነ ደግሞ ቢያንስ የሶስት ወር ዝግጅት ማድረግ አለበት። በተጨማሪም በኢንስቲቱሽንና በገንዘብ የሚደገፍ መሆን አለበት። በተለይም ለአገር ዕድገትና ነፃነት ተብሎ የሚጻፍ ጽሁፍና የፖለቲካ ሀተታ በአቦ ሰጡኝ የሚቀርብ ሳይሆን ብዙ ጥንቃቄን … [Read more...] about ፖለቲካ ሳይንስ ነው ወይ? ፖለቲካ ምሁራዊነት ያስፈልገዋል ወይ?
የኢትዮጵያ መንግሥት በሰማያዊ ፓርቲ ላይ ጥቃት አላደረስኩም ሲል ካደ
በሳምንቱ መጨረሻ ላይ 100 የሚጠጉ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እንደታሰሩና አንዳንዶቹም ክፉኛ እንደተደበደቡ ፓርቲው ገለጸ:: እሁድ ሊካሄድ ለነበረው ሰላማዊ ሰልፍ የተዘጋጁ የድምጽ መሣሪያዎች እንደተወሰዱባቸውና ሰልፉም እንዳይካሄድ እንደተደረገ የፓርቲው ሊቀመንበር ይልቃል ጌታቸው አስታውቀዋል:: የመንግሥት መገናኛ ሚ/ር ሽመልስ ከማል ድርጊቱ አልተፈጸመም ሲሉ የካዱ ሲሆን መንገዱ አክራሪነትን ለመቃወም መንግስት ለጠራው ትዕይንተ ሕዝብ አስቀድሞ ተይዞ እንደነበር መንግሥት አስታውቆዋል:: ኢትዮጵያን የሚገዛው ኢህአዴግ የሕዝቡን ህይወት በተመለከተ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርግ ይታወቃል:: ሰማያዊ ፓርቲ በሰኔ ወር የጠራው ህዝባዊ ተቃውሞ በ1997 ከተደረገውና የመቶዎች ህይወት ከቀጠፈው ሰላማዊ ትዕይንተ ሕዝብ በኋላ የተደረገ የመጀመሪያው ነበር:: ያለፈው ተቃውሞው የመብት ተሟጋቾችና … [Read more...] about የኢትዮጵያ መንግሥት በሰማያዊ ፓርቲ ላይ ጥቃት አላደረስኩም ሲል ካደ
መልካም ጅምር፡ ተደጋጋሚ ስህተቶች
የአንድነት ፓርቲ አመራር አካላት በፈረንጅ አቆጣጠር ኦገስት 30 ቀን ከሚድያ አካላት ጋር ያደረጉትን የቴሌ ኮንፈረንስ ውይይት በጥሞና ተከታትያለሁ:: መልካም ጅምር ቢሆንም ተደጋጋሚ ስህተቶች ከመፈጸም ግን የተቆጠብን አይመስልም:: በውይይቱ ላይ ብዙ መልካም ነገሮች ቢሰሙም የሚፈጸሙት ስህተቶች ግን ያው የጥንት የጠዋቱ በመሆኑ ውይይቱ ምን ያህል ወደፊት የሚያራምድ መሆኑ መገመት ይከብዳል:: የተንሸራሸሩት ሀሳቦች አዲስ ፈጽሞ የማናውቃቸው አይደሉም:: የተቃዋሚ ኅይሉ ደጋፊዎች ስጋት የታወቁ ናቸው:: ትልቁ ጥያቄ መልስ በአጥጋቢ ደረጃ ያልተገኘለት ተቃዋሚዎች አንድ ላይ መስራት ለምን ይቸግራቸዋል የሚለው ነው? የተቃዋሚ አመራር አካሎችን አብረው እንዲስሩ ደጋፊ አደራ የሚጥልባቸው ወይም ተጽዕኖ የሚያሳድርባቸው መንገዶች ተድበስብሰው በመታለፋቸው ካለፈው አሁን ምን አሻሸላችሁ … [Read more...] about መልካም ጅምር፡ ተደጋጋሚ ስህተቶች
Jailed: top TPLF warlord Woldesilassie’s kingdom of death and deceit crumbles
He was the dead tyrant Meles Zenawi’s alter ego and docile horse for 21 years and the most feared man in the complex TPLF security cluster. He amassed millions through corrupt practices and managed to build his own kingdom in partnership with equally corrupt former first lady Azeb Mesfin and her daughter Semhal Meles, the two queens of his vast empire. The malevolent warlord was well protected by the Zenawi family for 21 years and well placed in the inner circle of the ruling elite where … [Read more...] about Jailed: top TPLF warlord Woldesilassie’s kingdom of death and deceit crumbles
የከባድ ሙስና ተጠርጣሪዎች ክሱ ሳይሰጣቸው ተከሳችኋል መባላቸውን ተቃወሙ
* አቶ በእግዚአብሔርና አቶ ምሕረተአብ ተጨማሪ ጊዜ ተጠየቀባቸው * ሦስት የባለሥልጣኑ ሠራተኞች በነፃ ተሰናበቱ * የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ስምንት የክስ መዝገቦች አቅርቧል የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን በከባድ የሙስና ወንጀል ተሳትፎ በጠረጠራቸውና ከሦስት ወራት በላይ በእስር ላይ ባቆያቸው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉሙሩክ ባለሥልጣን ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ ኃላፊዎች፣ ሠራተኞች፣ ነጋዴዎችና ሌሎች ተጠርጣሪዎች ላይ ነሐሴ 23 ቀን 2005 ዓ.ም ክስ መመሥረቱን፣ ለፍርድ ቤት ቢያሳውቅም፣ ተጠርጣሪዎቹ መከሰሳቸውን የሚያሳይ ክስ እንዳልደረሳቸውና የሕግ ሥርዓትን ያልተከተለ መሆኑን በመግለጽ ክሱን ተቃወሙ፡፡ የኮሚሽኑ መርማሪ ቡድን በተጠርጣሪዎቹ ላይ ምርመራውን አጠናቆ ለኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ማስረከቡን፣ ጊዜ ቀጠሮውን ሲከታተል ለነበረው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ … [Read more...] about የከባድ ሙስና ተጠርጣሪዎች ክሱ ሳይሰጣቸው ተከሳችኋል መባላቸውን ተቃወሙ