በሳምንቱ መጨረሻ ላይ 100 የሚጠጉ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እንደታሰሩና አንዳንዶቹም ክፉኛ እንደተደበደቡ ፓርቲው ገለጸ::
እሁድ ሊካሄድ ለነበረው ሰላማዊ ሰልፍ የተዘጋጁ የድምጽ መሣሪያዎች እንደተወሰዱባቸውና ሰልፉም እንዳይካሄድ እንደተደረገ የፓርቲው ሊቀመንበር ይልቃል ጌታቸው አስታውቀዋል::
የመንግሥት መገናኛ ሚ/ር ሽመልስ ከማል ድርጊቱ አልተፈጸመም ሲሉ የካዱ ሲሆን መንገዱ አክራሪነትን ለመቃወም መንግስት ለጠራው ትዕይንተ ሕዝብ አስቀድሞ ተይዞ እንደነበር መንግሥት አስታውቆዋል::
ኢትዮጵያን የሚገዛው ኢህአዴግ የሕዝቡን ህይወት በተመለከተ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርግ ይታወቃል::
ሰማያዊ ፓርቲ በሰኔ ወር የጠራው ህዝባዊ ተቃውሞ በ1997 ከተደረገውና የመቶዎች ህይወት ከቀጠፈው ሰላማዊ ትዕይንተ ሕዝብ በኋላ የተደረገ የመጀመሪያው ነበር:: ያለፈው ተቃውሞው የመብት ተሟጋቾችና ጋዜጠኞች ከእስር እንዲፈቱ የጠየቀ የነበረ ሲሆን የትላንቱ ደግሞ የፓለቲካ ታሃድሶ እንዲካሄድ ጥሪ የሚያደርግ ነበር::
አቶ ሽመልስ እንደሚሉት ማንኛውም ህዝባዊ ተቃውሞ የሚያደርግ አካል ፍቃድ ማግኘት አለበት:: ሆኖም ባለሥልጣናት ፍቃድ መከልከል አይችሉም ነገርግን ስብሰባው (የዕለቱ ክስተት) በሌላ ቦታና ጊዜ እንዲካሄድ መንግሥት የማያወላውል አቋም ሊይዝ ይችላል በማለት አክለው ተናግረዋል::
መለስ ከሞቱ በኋላ ሃይለማርያም ደሳለኝ የሚመሩዋት ኢትዮጵያ ባለችበት ቀጣና እስላማዊ አማጺያንን በመዋጋት የአሜሪካ አጋዥ ነች::
Leave a Reply