• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

መልካም ጅምር፡ ተደጋጋሚ ስህተቶች

September 1, 2013 08:58 am by Editor Leave a Comment

የአንድነት ፓርቲ አመራር አካላት በፈረንጅ አቆጣጠር ኦገስት 30 ቀን ከሚድያ አካላት ጋር ያደረጉትን የቴሌ ኮንፈረንስ ውይይት በጥሞና ተከታትያለሁ::  መልካም ጅምር ቢሆንም ተደጋጋሚ ስህተቶች ከመፈጸም ግን የተቆጠብን አይመስልም::  በውይይቱ ላይ ብዙ መልካም ነገሮች ቢሰሙም የሚፈጸሙት ስህተቶች ግን ያው የጥንት የጠዋቱ በመሆኑ ውይይቱ ምን ያህል ወደፊት የሚያራምድ መሆኑ መገመት ይከብዳል::  የተንሸራሸሩት ሀሳቦች አዲስ ፈጽሞ የማናውቃቸው አይደሉም:: የተቃዋሚ ኅይሉ ደጋፊዎች ስጋት የታወቁ ናቸው:: ትልቁ ጥያቄ መልስ በአጥጋቢ ደረጃ ያልተገኘለት ተቃዋሚዎች አንድ ላይ መስራት ለምን ይቸግራቸዋል የሚለው ነው?   የተቃዋሚ አመራር አካሎችን አብረው እንዲስሩ ደጋፊ አደራ የሚጥልባቸው ወይም ተጽዕኖ የሚያሳድርባቸው መንገዶች ተድበስብሰው በመታለፋቸው ካለፈው አሁን ምን አሻሸላችሁ ቀርባቹሀል የሚል ጥያቄ ወደፊት በሚደረጉ ውይይቶች መጠየቅ አይቻልም::

ለኔ እንደሚታየኝ ከሆነ አንዱና ዋንኛ ድክመት ጠንካራና ተከታታይ ጥያቄ ማለትም ተጠያቂውን ግለሰብም ሆነ የድርጅት ሃላፊ ለጥያቄ ተገቢ መልስ ሳይሰጡ በአራዳ ቋንቋ “ሸውደው” እንዳያልፉ የሚያደርግ አወያይ ባለመኖሩ ነው:: አንዱ ምክንያት አወያዩ ለተጠያቂዎች ያለው ከበሬታ ሊሆን ይችላል:: ወይም ደግሞ ካላቸወ ቀረቤታ ተጠያቂው ላይ ከበድ ያሉ ጥያቄዎች እንዳይደርሱ ለመከላከል ወይም ማሳለፍ ሊሆን ይችላል::   ይህ ደግሞ ለአድማጭ ምንም እርካታ ሳይሰጥ ተጠያቂውም ግለሰብ አለምንም ሀላፊነት በማርያም መንገድ ይነጉዳል::  ስለዚህ በዚህ ውይይት ምንም አዲስ ነገር አለተሰማም ባለስልጣናቱም ለምንም ነገር ሃላፊነት ሳይወስዱ በመጡበት ተመልሰዋል::

ይቺ አጭር ትችት ፍላጎት ይህን ችግር በጥሞና ተመልክቶ ለማሻሻል እንዲረዳ እንጂ ውይይቱን ያዘጋጅቱ ሰዎች ለመውቀስና ያደረጓቸውን ጥረቶችና ውጣ ውረዶች ላለማድነቅና ግለሰቦቹንም የሚገባቸውን ምስጋና ለመንፈግ አይደለም:: መታረም የሚገባቸውን ጉድለቶች አርመን ለሚቀጥሉት በዙ ውይይቶች አሻሽለን ካልቀረብን አንዲትም ጋት ፎቀቅ ሳንል እዛው አሰልቺ አዙሪት ውስጥ እንቆያለን:: ስለዚህ የሚፈጸሙ ጉድለቶችን መጠቆም አስፈላጊ መሆኑን በማመን ነው::

ለማንኛውም ከተወረወሩት ሃሳቦች ለምሳሌ ያህለ ጠቃሚ የሆኑትንና ብዙም ጠቃሚ ያልሆኑ አንድ ሁለቱ  እንመልከት:

መልካም ምክር   አቶ ንጉሴ የሚባሉ ተሳታፊ የአንድነት ፓርቲ የብሄር/ብሄረሰቦች አቋም በሕብረተሰቡ ዘንድ ብዙም አይታወቅም ብለዋል:: ይህንን ክፍተት በመጠቀም የገዥው ፓርቲ ደግሞ ብሄር/በሄረሰቦችን ከምንግዜውም የበለጠ እኩልነት አምጥቻለሁ ብሎ የሐሰት ፕሮፓጋንዳ እንዲነዛ ጠቅሞታል:: ለድጋፍም ዋናው መቀሽቀሻ አድርጎታል::  እውነታው ግን ብሄረሰቦችን ከመሸንግል በቀር በትክክለኛው መንገድ የብሔረሰብ እኩልነት ሳይሆን የአንድ ብሄረሰብ የበላይነት ነው የነገሰው::  አንድነት ፓርቲ በምን አይነት መንገድ ከገዢው ፓርቲ በተሻለ የብሄረሰብ እኩልነትን እንደሚያስከብር በስፋት የመቀሽቀሻ ዘዴ አድርጎ መጠቀም አለበት ሲሉ በጣም ጠቃሚ ሀሳብ አቅርበዋል::  ልብ በሉ አቶ ንጉሴ ያሉት የአንድነት ፕሮግራም የብሔረሰብ መብት የሚያስከብር አንቀጽ የለውም አይደለመ ያሉት:: በስፋት አለተነገረም ነው ያሉት:: ፕሮግራሙ ውስጥ ተቀበሮ ቀርቷል ማለት ነው:: ጎልቶ አልታየም:፡ በስፋት አለተነገረም::  ከሰሜን እስከ ደቡበ ከምሰራቅ እስከ ምእራብ ያለው ህብረተሰብ ጥርት ባለ መልኩ አያውቀውም: ስለዚህም ገዥው ፓርቲ ይህንን ክፍተት በሚገባ ለራሱ ፕሮፓጋንዳ ተጠቅሞበታል::  ይህ ርዕስ ላይ ምላሽ ሳይሰጥበትና ውይይት ሳይደረግበት ታልፏል::  የፓርቲው ባለስልጣናት ይህን ጠቃሚ ሀሳብ ምን ያህል ስራ ላይ እንደሚያውሉት አልታወቀም:: ሀሳቡ ቢወስዱት ግን ሕብረተሰቡን ከብዙ ውዥንብር ከማዳኑም በላይ አንድነት ፓርቲ ዋና ዋና የሚባሉ ነባራዊ ችግሮችን በምንዓይነት  መልክ መፍትሄ እንደሚሰጥ በጠራ መልኩ ያሳይ ነበር:: ሃሳቡን ግን መውሰዳቸው ስለማይታወቅ ታዳሚው እርካታ የሚያገኝበት አይመስልም::  ስለዚህ ይህ ስህተት ሳይታረም መስከረም ይጠባል ማለት ነው::

ገንቢ ሂስ ወ/ሮ ሙሉ የሚባሉ ተሳታፊ ደግሞ ለምን መከፋፈል እንደሚኖርና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ውስጥ የሴቶች ተሳትፎ ለምን አነሰ በሚለው ላይ ገነቢ ሂስ አቅርበዋል:: ጠያቂዋም የአንድነት ባለስለጣናቱ ጋር እንደሚተዋወቁ ገልጸዋል:: አጠር ባለ ቃል ወ/ሮ ሙሉ እናንተ አቶ ግርማ ሰይፉና አቶ በላይ የምትሰሩት በቲፎዞ ነው ብለዋል:: ይህ አባባል ጠቅላላ የአንድነት ፓርቲን እንደሚመለከት ግን ጥርጥር አይግባን::  ይህ የቲፎዞ አሰራር ነው ቅንጅትን ያፈራረሰ እስካሁንም ድረስ ድርጅቶችን እየበጠበጠ ያለው:: ስለዚህ መታለፍ የማይገባው አፍራሽ ባህርይ ነው:: ሆኖም ግን ተጠያቂው መልስ ለመስጠት አልደፈሩም:: አወያዩም ለማስታወስ ወይ አልፈለጉም ወይ ጠቃሚነቱ አልገባቸውም::  እዚህ የቲፎዞ አሰራር ላይ ነው የእህቶቻችንና የወንዶች የውስጥ ባህርይ የሚለያየው::  እህቶቻችነ ማህበራዊ ባህርያቸው ሰፋ ያለ በመሆኑ ሁሉን አባል እኩል የማየት ባህርያቸው ከወንዶች ይልቃል::  ያለአግባብ ማድላት ወይም አንድን አባል ጠቅሞ ሌላውን አባል ያላግባብ መጉዳት የመሳሰሉ በግለሰብ ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ከወንዶች የበለጠ ይሰማቸዋል::  የቡድናዊ የቲፎዞ ስሜታቸው አነስተኛ በመሆኑ ከእንደዚህ ዓይነት መድሎ መራቅ ይመርጣሉ::  ይህ ዋንኛ ምክንያት ሊሆን ይችላል በአንድነት ፓርቲ ውስጥ የሴቶች ተሳትፎ አንሶ የተገኘው::  ይህ ሂስ እንደ ገንቢ ባለመወሰዱ ፓርቲው ከመመለስ ይልቅ አደበስብሶ ማለፍ መርጧል:: ትምህርት አልተገኘም ማለት ነው:: ለሚቀጥለው ውይይት መሻሻልን ሳይሆን የምንነጋገረው ደግመን ይህንኑ ጥያቄ ነው የመሻሻያ አንድ ዕድል አለፈ ማለት ነው::

ድርጅታዊ ሥራ  የአቶ ሺበሺ የሚባሉ ደግሞ በጀብዱና በጀግና መሀከለ ያለውን ልዩነት አስረዱኝ የሚል ጥያቄ አቅርበዋል::  ይህ ደካማ ድርጅታዊ ካድሬ ስራ መሆኑን ሁሉም አድማጭ ይረዳል::  ጥያቄው ጠቀሜታ ቢኖረው ኖሮ መለካም ነበር:: ሆኖም ግን አብዛኛው ተሳታፊ የተቃዋሚ ደጋፊ በሆነበት መድረክ ከትዝብት በቀር ለመሻሻልም ሆነ የደጋፊን ስጋት ለማበረድ ምንም ጥቅም የለውም:: ድርጅታዊ ጥያቄ በመሆኑ መላሹ ሰፋ ያለ ጊዜ ወስደው እንዴት የአንድነት አባለት በፍቼ ከተማ በተደረገው ግብግብ ጀግንነት እንዳሳዩ ገልጸዋል:: ቃላቶቹ የምያምታቱ አይደሉም::  ጀብድ የሚፈጸም ድርጊት ሲሆን ጀግና ደግሞ ጀብድ ፈጻሚ ሰው ነው:: በፍቼ በወያኔ ካድሬዎች በግፍ የተደበደቡት የአንድነት ፓርቲ አባላት ጀብዱ የፈጸሙ ጀግኖች ናቸው:: በቃ ሌላ ምንም ትርጉም የለወም:: የተነሳው ጥያቄ ግን  የምንጠላውን ክፍፍል የሚያሰፋ እንጂ የሚያቀራርብ አይደለም:: ምክንያቱም የጥያቄው ዓላማ ድንበር ዘለልና ግልጽ በመሆኑ ነው:: የሰማያዊ ፓርቲ በቁርጠኝነት ከገዥው ፓርቲ ጋር ከዚህ ቀደም ባልታየ ሁኔታ ለመጋፈጥ መወሰኑን ጀብደኛ ለማለት የታለመ ነው:: ይህ አይነት እርስ በእርስ የመጠላለፍ አሰራር ነው የተጠላው ሆኖም ግን ከመደጋገም አልተቆጠብንም።

አድርባይነት ይህ ክስተት የታየው ወ/ሮ ሙሉ የሚባሉት ተሳታፊ የሰላ ሂስ የአንድነት አመራር ላይ በሰነዘሩበት ወቅት ነው:: ከላይ እንደጠቀስኩት ወ/ሮ ሙሉ በቅርብ የሚያውቅቱን የቲፎዞ አሰራር እንዳለ አጋለጠው መታረም እንዳለበት ተናግራዋል::  አባ መላ ተብሎ የሚታወቀው የቀድሞ የወያኔ ደጋፊ ተቃዋሚን ሁሉ ሙልጭ አድርጎ ሲሳደብ እንዳልነበረ ሁሉ ይህ ሂስ ሲሰነዘር ዘሎ በመግባት ልብ አድርጉልኝ እኒህ ሴትዮ የኔን የፓል ቶክ ክፍል ተሳታፊ አይደሉም ብሎ ማሳሰብያ ሰጥቷል:: ወይዘሮይቱም እውነትነቱን አረጋግጠውለታል:: ስለዚህ በሱ ፓል ቶክ ክፍል ውስጥ የተመረጡ ሰዎች ለጥያቄ የተዘጋጁ እንዳለ ያሳያል ማለት ነው:: ይህ ብቻም ሳይሆን የግለሰቡ ፈጽሞ አድርባይነት ፍንትው አድርጎ ያሳያል:: በዚህ መንገድ ችግሮች አይፈቱም:: ተደጋጋሚ ስህተቶች እየተፈጸሙ ወደፊት መራመድ አይቻልም::

ደህና እንክረም

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሤራ አክሻፊው ጎንደር ለሦስተኛ ጊዜ ታሪክ ሠራ May 10, 2023 09:25 am
  • ማር በከፍተኛ ደረጃ የኮንትሮባንድ ሰለባ ሆኗል May 9, 2023 09:24 am
  • ኦነግ በኦሮሚያ ሪፈረንደም እንዲካሄድ መጠየቁ ለሰላም ንግግሩ ዕንቅፋት ሆነ May 4, 2023 01:12 am
  • መረጃ ቲቪ ያጋራው አሳሳች መረጃ May 2, 2023 12:37 pm
  • “ከፈጣሪ በታች መከላከያ የሁላችን ዋስ ጠበቃ ነው፤ ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን” April 13, 2023 10:19 am
  • በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው April 13, 2023 08:56 am
  • በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ April 13, 2023 03:21 am
  • “የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል April 12, 2023 09:23 am
  • ከዕድሜ ልክ እስከ 20 ዓመት ቅጣት ተበይኖባቸዋል April 11, 2023 02:58 pm
  • የኡጋንዳ የክልሎች ሚኒስትር በቆርቆሮ ሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ April 10, 2023 03:59 pm
  • ታከለ ከተነሳ በኋላ የመዐድን ሌቦች እየተያዙ ነው April 6, 2023 02:53 pm
  • አገር ለማተራመስ ያለመ የምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ህቡዕ ቡድን ተያዘ April 4, 2023 10:07 am
  • በ10 ዓመት ውስጥ ከ44 ቢሊየን ዶላር በላይ ሸሽቷል April 4, 2023 09:26 am
  • አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም March 29, 2023 09:47 am
  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule