• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በመንግስታዊ ውንብድና ትግላችን አይገታም!!!!!

September 3, 2013 08:15 am by Editor 2 Comments

ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም. ባካሄደው ታላቅ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለመንግሥት ያቀረባቸው ጥያቄዎች አስፈላጊው ምላሽ እንዲሰጣቸው በመጠየቅ ይህ ካልሆነ ግን ከሦስት ወር በኋላ ተቃዉሞውን ከፍ ባለ ደረጃ እንደሚያቀርብ በመጋለፅ ሰልፉን አጠናቋል፡፡ ለተነሱት ጥያቄዎች የተገኘ ምላሽ ባለመኖሩ ፓርቲው ለሕዝብ በገባዉ ቃል መሠረት ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም. ታላቅ የተቃዉም ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሔድ በመወሰን በሕግም ሆነ በሥራ የሚያስፈልጉ ነገሮችን በማጠናቀቅ እለቱን በመጠበቅ ላይ እያለ ምንም አይነት መለዮ ባልለበሱ ግለሰቦች የሚመራ የፖሊስ መለዮ ለባሽ ታጣቂዎች ከሕግ ውጭ ነሐሴ 25 ቀን 2005 ዓ.ም. ከምሽቱ 12 ሰዓት አካባቢ የፓርቲውን ቢሮ ጥሰው በመግባት ፓርቲው ይጠቀምባቸው የነበሩ የቅስቀሳ ቁሳቁሶችና ሌሎች የፓርቲውን ንብረቶች ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወርሰዋል፡፡ በፓርቲው ፅ/ቤት የነበሩ አባላትን እና መሪዎችን በጠመንጃ በማስገደድ ወደተለያዩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያዎች ከፋፍሎ በመውሰድ አስረዋል፣ ዘልፈዋል፣ አስፈራርተዋል እንዲሁም አረመኔያዊ በሆነ መንገድ ደብድበዋል፡፡

አንዳንዶችን በጭቃ ላይ ጭምር አንከባለዋል፡፡ ይህ ሁሉ ሕገ ወጥና አረመኔያዊ ድርጊት ሕገ መንግስታዊ የሆነውን መብታቸውን በሚጠቀሙ ዜጎች ላይ ሲፈፀምና በሕግ ማስከበር ስም በቁጥጥር ሥር በዋሉ ዜጎች ላይ የግል ጥላቻን መወጣጫ እስኪመስል ድረስ ማንኛዉንም የማንአለብኝነት ድርጊት ሲፈፅሙ ማየት ያልታጠቁ ዜጎችን አቅመ ቢስነትና የሕግ ከለላ ማጣትን ገሃድ አድርጎታል፡፡ ይሕ አይነቱ የጡንቻ ሥራ በአንድ በኩል ልብን በሐዘን የሚሰብር ድርጊት ሲሆን በሌላ በኩል ለነፃነትና ለፍትህ የሚደረገው ትግል እጅግ ትክክለኛና ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ሰማያዊ ፓርቲ የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ሕጋዊ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ሁሉ አድርጓል፡፡ የአስፈፃሚው አካላት በሕግ ከተሰጣቸው ስልጣንና ተግባር በመውጣት የፈለጉትን ለማድረግ መብት እንደሌላቸው ማሳዬት ፓርቲያችን ከተመሰረተባቸው አብይ መርሆች አንዱ በመሆኑ፤

1ኛ. በአዲስ አበባ ከተማ ከቤት ውጭ የሚደረጉ ስብሰባንና ሰላማዊ ሰልፍን አስመልክቶ ጥያቄዎችን ተቀብሎ በሕግ በተወሰነው መሰረት አስፈላጊውን ሁሉ ማከናወን የሚገባው በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የሕዝባዊ ስብሰባና የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ኃላፊነቱን ባለመወጣቱ በፓርቲው ላይ ለደረሰው የአካል፣ የንብረትና የሞራል ጉዳት ምክንያት በመሆኑ በሕግ እንጠይቃለን፤

2ኛ. የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የፓርቲ መሪዎችን በማስፈራራት ከሰልፍ ለማስቀረት የሚያደርገው ድርጊት ከህግ ውጭ በመሆኑና በፖሊስ መለዮ ለባሾች ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የፓርቲውን ቢሮ በመውረር ለፈፀሙት የንብረት ዘረፋና ውድመት እንዲሁም ፓርቲው ባቀደውና በተዘጋጀበት ጊዜ የተቃውሞ ሰልፉን እንዳያካሂድ በማደናቀፉ በሕግ እንጠይቃለን፤

3ኛ. በሐገራችን ፓርቲዎችን እንዲያስተዳድርና እንዲከታተል ስልጣን የተሰጠው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና ሰጥቷቸው በሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ላይ እንዲህ አይነት ሕገ ወጥ ድርጊት እየተፈፀመባቸው መሆኑን እንዲያውቀው እናደርጋለን፤

4ኛ. የፖለቲካ ትግላችንን በመቀጠል ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብታችንን የትኛውም የአስፈፃሚ አካል የመከልከል መብት ስለሌለው የተቃውሞ ሰልፈችንን ቅዳሜ ጳጉሜ 2 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እንደምናከናውን ለአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የሕዝባዊ ስብሰባና የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል በዛሬው ዕለት አሳውቀናል፡፡

በመሆኑም ከዚህ ቀደም ለመንግስት ያቀረብናቸው ጥያቄዎች እንደተጠበቁ ሆነው በተደጋጋሚ እንዳስተዋልነው በዚህች ታሪካዊት ሐገር የሕግ የበላይነት ግብዓተ መሬት ከመፈፀሙ በፊት እንድንደርስላት ለዘመቻ የሕግ የበላይነት ትግላችን የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማሕበራትና ዜጎች በአጠቃላይ ከጎናችን እንዲሰለፉ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

በመንግስታዊ ውንብድና ትግላችን አይገታም!!!!
ነሐሴ 27 ቀን 2005 ዓ.ም.
አዲስ አበባ

Blue 2

Filed Under: Politics

Reader Interactions

Comments

  1. ali says

    September 3, 2013 10:19 pm at 10:19 pm

    SEMAYAWI BERTU WEYANE EYALEQELET NEW DEL LE ETHIOPIA HEZB

    Reply
  2. ali says

    September 3, 2013 10:31 pm at 10:31 pm

    VICTORY FOR ETHIOPIAN PEOPLE

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
Copyright © 2026 · Goolgule