• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አዜብ መስፍን ይታሰራሉ?

September 3, 2013 11:46 am by Editor 9 Comments

መለስ ዜናዊ ሆን ብለው ለፖለቲካ ሚዛን መጠበቂያ ሲገለገሉበት በነበረው “የሙስና ባህር” ያልተነከረበት የለም። ባህሩ ውስጥ ያልዋኘ የለም። ከባህሩ ራሳቸውን ያገለሉ ጥቂቶች ቢኖሩም ወ/ሮ አዜብ መስፍን ግን የባህሩ ዋናው አጥማቂና የውሃው ባለቤት እንደሆኑ በርካታ ምስክሮች አሉ።

አቶ መለስ “ውርሳቸውን/ሌጋሲያቸውን” ትተው ካለፉ በኋላ አገሩን አከርፍቶት የነበረው የሙስና ባህር በስንጥር መነካካት ተጀመረና አሁን ቁንጮዎቹ ግድም ደርሶ እያሸበረ ነው። ይህንኑ የሙስና ማዕበል ተከትሎ የባለቤታቸውን ውርስ ታኮ ያደረጉት ወ/ሮ አዜብና በተሸናፊው የፖለቲካ መስመር ያሉ ሁሉ ተሸብረዋል። አንዳንድ ጥቆማዎችና የህዝብ አስተያየቶች እንደሚያመለክቱት ወ/ሮ አዜብ ታውከዋል።

ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሃላፊዎችና ከነሱ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ከዋሉት “ባለሃብቶች” መካከል ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር እንደሚነግዱ የሚታወቁ በቁጥጥር ስር መዋላቸው የስጋታቸው መነሻና እምብርት ስለመሆኑ አብዛኞች ይስማማሉ። ከዚህም በተጨማሪ ያለታክስ በሚገቡ ምርቶች፣ ተሽከርካሪዎች፣ በቴሌ የህገወጥ ማስደወል ወንጀል፣ በጫት ኤክስፖርትና በኮንስትራክሽን ዘርፍ በስፋት ቢዝነስ እንደሚያጫውቱ የሚታወቁት ወ/ሮ አዜብ በገንዘብ የከበሩትን ያህል በርካታ ጠላት እንዳፈሩም የሚቀርቧቸው ይናገራሉ።

azeb 2ኤፈርትን ለወ/ሮ አዜብ ያስረከቡት አቶ ስብሃት ነጋ በተደጋጋሚ ስለሙስና መናገር የጀመሩት አቶ መለስ አፈር ሳይቀምሱ ነበር። ወ/ሮ አዜብ የባለቤታቸውን ጡንቻና በዘመቻ በጀት ተመድቦለት “ባለራዕይ፣ ታላቁ መሪ” በሚል የተሰጣቸውን የሸቀጥ ስም ተገን አድርገው ሙስና ውስጥ መነከራቸውን የሚያውቁት አቶ ስብሃት ስም አይጥቀሱ እንጂ ነገራቸው ሁሉ ከወ/ሮ አዜብ ደጅ እንደነበር ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የሚናገሩት የአደባባይ ምስጢር ነው።

አቶ ስብሃት ነጋ ከመለስ ሞት በኋላ ይህንኑ አቋማቸውን አጠንክረው የገፉበት ቢሆንም በፖለቲካ አሰላለፋቸው ተሸናፊ በመሆናቸው ለማፈግፈግ ተገደው እንደነበር የሚናገሩ አሉ። ከውስጥ አዋቂዎች እንደሚሰማውና በተባራሪ እንደሚነገረው አቶ ስብሃት ዳግም አሸናፊውን ቡድን ተመልሰው ተቀላቅለዋል። ለዚህም ይመስላል እሳቸው ምን ያህል የጸዱ ስለመሆናቸው መረጃ ባይኖርም አሁን ከተጀመረው የሙስና ዘመቻ ጀርባ እንዳሉበት የሚጠቆመው። አንዳንዶች እንደሚሉት ህወሃት በትከፋፈለ ጊዜ (ዘመነ ህንፍሽፍሽ) አቶ አባይ ጸሐዬ ውህዳኑን ተቀላቅለው መረጃ ከሰበሰቡ በኋላ አቶ መለስን በመቀላቀል የተጫወቱትን የ”መንታ”/ደብል/ ስልት፣ የመለስ ሞትን ተከትሎ ለተነሳው የሃይል ሰልፍ ትንቅንቅ አቶ ስብሃት ነጋም ተጠቅመውበታል። በዚሁ ስልታዊ አካሄድም የእነ ዶ/ር ደብረጽዮን ክንፍ አሸናፊ ሆኖ እንዲወጣ አስችለዋል።

አዜብ መስፍን ለምን አይታሰሩም?

ከሙስና ጋር ስማቸው በስፋት የሚነሳው ወ/ሮ አዜብ፤ በባለቤታቸው እንደ ቪኖ ቡሽ ድንገት ሲፈተለኩ በሃዘን ድባብ ውስጥ ሆነው የጀመሩት ዘመቻ የቀልድ መሃላ ይዘት ያለው ነው። በ”ፖለቲካ ቁጭ በሉ” እንዲመለኩ የተደረጉትን አቶ መለስን ደጋግሞ በመጥራት አዜብ መስፍን “የመለስ ራዕይ ካልተቀየረና ሌጋሲው እስካልተበረዘ ድረስ …” እያሉ ካድሬውንና ቀሪውን የህወሃት ሰዎች መማጸን ላይ አተኩረው ነበር። በሄዱበትና ባገደሙበት የባለቤታቸው ስምና ዝና ላፍታም ካንደበታቸው የማይለያቸው ወ/ሮ አዜብ ጀርባቸውን ስለሚያውቁት የመለስን ስም የሚያንጠለጥሉት ራሳቸውን ለመከላከል እንደሆነም ከታች እስከ ላይ ስምምነት አለ።

ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ከደረሱት አስተያየቶች መካከል “ካድሬው ባብዛኛው፣ የበላይ አመራሩ በከፊል አዜብስ?” በማለት ለምን በቁጥጥር ስር እንደማይውሉ የሚጠይቁትና የሚነጋገሩት በገሃድ ነው። ይሁን እንጂ አዜብ ለምን እንዲታሰሩ የፍርድቤት ትዕዛዝ (ዋራንት) አይቆረጥባቸውም? ለሚለው የሚሰጠው መልስ “የመለስ ሌጋሲ እንዳይወድም፣ እንዳይቆሽሽ፣ የተሰራው የረከሰና የሸቀጥ ያህል በፖለቲካ ውዳሴ የተገነባው ከንቱ ዝና እንዳይቆሽሽ፣ ብሎም ሌላ ጥያቄ እንዳያስነሳ ነው” የሚል ነው።azeb 1

አቶ ስብሃት ሲመሩት የነበረው ኤፈርትን በሳቸው አዲስ አመራርና በመለስ ልዩ አመራር ሰጪነት በሺህ ለሚቆጠሩ የትግራይ ልጆች የስራ እድል ማዘጋጀቱን፣ ትግራይ ውስጥ በርካታ ፋብሪካዎች እንደሚከፈቱና ሲደበቅ የነበረው በጀት በዶላር ተሰልቶ ለህዝብ ይፋ እንዲሆን በማድረግ ስብሃት ነጋን የማሳጣት እጅ አዙር ዘመቻቸውን አጣድፈው የጀመሩት ወ/ሮ አዜብ የትግራይን ህዝብ ልብ ለማግኘትና አቶ ስብሃት የሚከፍቱባቸውን ዘመቻ አስቀድሞ ለመቋቋም በማሰብ ነበር።

ህወሃት የክልሎችን በጀት እልብ አድርጎ የሚጠባበት የብር ማሽኑ የሆነውን ሜጋ ኢንትርፕራይዝን ይመሩ የነበሩት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከምርጫ1997 በኋላ በድርጅት አቋም፣ በአቶ መለስ ፊርማና ውሳኔ እንዲነሱ መደረጉን፤ ከሃላፊነት የተነሱበት ደብዳቤ እንደደረሳቸው አኩርፈው ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሄደው “በሽማግሌ” ከባለቤታቸው ጋር እንደታረቁ፣ ሽምግልናውን ባከናወኑት ሰው አማካይነት ወ/ሮ አዜብ የተነጠቁት ሹመት እንዲመለስላቸው መደረጉን እንደሚያውቁ የሚናገሩ ክፍሎች “ኢትዮጵያ ውስጥ ህግና ፍትህ ለሰከንድ ቢተገበር ህገወጥ ስልክ በማስደወል የሜጋን ቢሮ ለዋና ማቀናበሪያና የተጠቀሙበት ወ/ሮ አዜብ የመጀመሪያዋ ተጠያቂ ሊሆኑ በተገባ ነበር። የመለስ ሌጋሲ እንግዲህ ይህን ነው” በማለት ይጠይቃሉ።

እነዚህ ክፍሎችም ሆኑ ሌሎች ወገኖች አዜብ መስፍን የፖለቲካ ሃይላቸው የተቦረቦረ፣ ከበዋቸው የነበሩት ሃይሎች የተመናመኑ፣ እንደ ተርብ የሚናደፈው አንደበታቸውና ባህሪያቸው እንደበረዶ የቀዘቀዘበት ወቅት ላይ እንደሚገኙ እየተገለጸ ነው። በጸለመ ልብስ የሚታዩትና የሃዘን ጥቁር ልብሳቸውን ለመቀየር ፈቃደኛ ያልሆኑት ወ/ሮ አዜብ ተቅለስላሽ ሰው ሆነው መታየታቸው ስጋታቸው ማየሉን የሚያሳይ እንደሆነ የሚመሰክሩት ክፍሎች “አዜብ መስፍን ወዳጅ እንደሌላቸውና በተለይም በህወሃት ሰዎችና ካድሬዎች ዘንድazeb-mesfin ስለማይወደዱ ዙሪያቸውን ከሚዞራቸው የሙስና ደወል ማምለጥ ስለሚችሉበት ሁኔታ ሊያስቡ እንደሚችሉ እንገምታለን” ይላሉ። ለአብነትም ሲያኮርፉ ወደ ሳዑዲ እንደሚሄዱና በዱባይ ሪል ስቴት እንዳላቸው ስለሚታሙ ጓዛቸውን ጠቅልለው ወደዚያው ሊያመሩ እንደሚችሉ ምልክት እንዳለ ይጠቁማሉ። በዱባይ አላቸው ስለሚባለውና በሌሎች ተቋራጭ ድርጅቶች ስም ስለተገነቡት ቤቶችና ንብረቶቻቸው እነዚህ ክፍሎች ለጊዜው ዝርዝር አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል።

በሌላ ወገን ግን አሁን የባለቤታቸውን የፋውንዴሽን ስራ እንዲሰሩ የተመደቡት ወ/ሮ አዜብ የእነ በረከት ስምዖን ቡድን በመሆናቸው፣ ለዚሁ ቡድን ቀኝ እጅ የሆኑት የደህንነቱ አውራ አቶ አሰፋና ሸራተን ያሉት ባለሃብት እጅግ ወዳጃቸው በመሆናቸው ቀስ በቀስ እንዲከስሙ ይደረጋል እንጂ አይታሰሩም ሲሉ በድፍረት ይናገራሉ። ወ/ሮ አዜብን ማሰር ማለት አቶ መለስን ከመቃብር አውጥቶ እንደገና ፍርድ አደባባይ የማቅረብ ያህል እንደሆነ የሚናገሩት እነዚህ ክፍሎች “ታላቁ፣ ባለራዕዩ፣ አስተዋዩ፣ አርቆ አሳቢው፣ የደሆች አባት፣ ራሱን ‘ለኢትዮጵያ’ አንድዶ የሞተ፣ አንዲት ሃሳብ ይዞ ወደ (ኢትዮጵያ) ምድር የመጣው አዳኝ፣ እረፍት የማያውቀው፣ ዜጎቹን በቀን ሶስቴ እንዲበሉ ያስደረገው፣ የአፍሪካ አንደበት፣ የዓለም ቅርስ፣ የወደፊቱ ኢትዮጵያ ተምሳሌት፣ የታሪክ አውራ፣ እርምና ወንጀል የሌለበት … በማለት ህወሃት ሆን ብሎ የገነባውን ስም አዜብን በማሰር አፈር አይከተውም” በማለት አዜብ ሊታሰሩ የማይችሉበትን ምክንያት ያመላክታሉ።

የመጨረሻው መጀመሪያ

birhane
ብርሃነ ኪዳነማርያም

ወ/ሮ አዜብ የመጨረሻው መጀመሪያ ላይ ስለመሆናቸው ምልክቶች እንዳሉ የሚጠቅሱ አሉ። ያለ ከልካይ ሲመሩትና ሲነዱት ከነበረው ግዙፉ የህወሃት የገንዘብ ቋት ኤፈርት ተሰናብተዋል። ወንበራቸውን እንዲቀሟቸው የተደረጉት የዋልታ ኢንፎርሜሽን ዋና ስራ አስኪያጅና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት የሆኑት ብርሃነ ኪዳነማርያም (ብርሃነ-ማረት) የቀድሞው የፍቅር ወዳጃቸው ናቸው። በደህንነት ውስጥ አድራጊና ፈጣሪ የነበሩት የቅርብ የንግድ ሸሪካቸው አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የሚጠየፉትን ወህኒ ገብተውበታል። በከፍተኛ የንግድ ቅርርብና ሽርክና የሚወዳጇቸው አቶ ነጋ ገብረ እግዚአብሔር ከታሰሩ ወራት ተቆጥሯል። የገቢዎችና ጉምሩክ ምክትል ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ገብረዋህድ ከቀረጥ ነጻ በመፍቀድ አብረዋቸው በኤፈርት ታርጋ ገንዘብ ሲያልቡ ኖረው አሁን ወደ እስር ቤት ተወርውረዋል። የቴሌ የሙስና ቅሌትና በኦሮሚያ የመሬት ንግድ አብረዋቸው ሲሳተፉ የነበሩ ሁሉ ዋራንቲ ተቆርጦባቸው እስር ቤት ገብተዋል። እንግዲህ በዚህ ሁሉ መዓት ውስጥ ያልተነኩት ወ/ሮ አዜብ ብቻ ናቸው።

ለፌደራል የጸረ ሙስና ኮሚሽን ቅርብ የሆኑ ምንጮች እንደሚሉት ተጠርጣሪዎቹ በምርመራ ወቅት ወ/ሮ አዜብን በትዕዛዝ ሰጪነትና በንግድ አጋርነት ዋና ተባባሪ መሆናቸውን በማመልከት መስክረዋል። ከዚህም በላይ በርካታ ጥቆማ አለ። በነዚህና በበርካታ ምክንያቶች ጣት የተቀሰረባቸው ወ/ሮ አዜብ አሁን የቀብርና የተስካር፣ ሙት ዓመት ዘካሪና የማስታወሻ ግንባታ ኮሚቴ ሃላፊ ሆነው ተቀምጠዋል። የመጀመሪያው መጨረሻ “መገለል” እንደሆነ፣ ከዚያም እውነተኛው መጨረሻ ሊገጥማቸው እንደሚችል ግምታቸውን የሚሰጡ ተበራክተዋል። “ከቶውንም አይታሰሩም። ለመለስ ሲባል “የሚሉት ደግሞ መጨረሻቸው ከኢህአዴግና አሁን ካለው የቡድን ፍትጊያ ጋር እንደሚሆን ይናገራሉ።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. ZERAY ASGDOM says

    September 3, 2013 01:18 pm at 1:18 pm

    over respected person,Meles legese,Realy do you beleive that did he done important things?no!how money Ethiopians are live standerdize life?did he done more for Ethiopia?but his name is over and over by his supporters,SO,SORY!

    Reply
  2. TEWBEL says

    September 3, 2013 01:25 pm at 1:25 pm

    yeinbway kab !!

    Reply
  3. yohannes says

    September 3, 2013 03:41 pm at 3:41 pm

    yemayalf binor ye amilak qal bicha new.be tibebu yhnnm mechereshawn yasayenal.

    Reply
  4. ethio says

    September 4, 2013 06:49 am at 6:49 am

    next month she jail

    Reply
  5. yohannes tadesse aka says

    September 4, 2013 06:13 pm at 6:13 pm

    መለስ ዜናዊ በአዜብ እጅ ነው ሲዘርፍ የኖረው ። ይህ የታወቀ ሐቅ ነው።

    Reply
  6. Haile says

    September 4, 2013 09:57 pm at 9:57 pm

    Azeb Mesfin should go to jail without doubt. All her friends are there – better to keep her with her comerades and lovers

    Reply
  7. Bellay says

    September 6, 2013 05:33 pm at 5:33 pm

    It is every Ethiopians wish. But she & Bereket are above the LAW !!!.

    Reply
  8. Abeba says

    September 13, 2013 12:17 am at 12:17 am

    I donot understand why AZEB And SEBHAT is not taking legal action against the neftnya newspapers when they hunt them by false informations, their main aim is to divide the TPLF LEADERSHIP I know the leadership knows who this people are. These are people who are part of the fundamentalist neftegyna groups who lost power in ethiopia. The oppressed amhara people who live in gojam, showa, goder, wollo always stand with their tigrina brothers. the neftgyna is the main problem behind the curtain

    Reply
  9. mitike haile says

    July 24, 2015 03:44 pm at 3:44 pm

    አዜብን ከእሙኪያ የበለጠ ንፅህናዋን የሚያቅ የለም የ32አመት ልጅ ነኝ በእጅ የያዙት ወርቅ ሆነ እንጂ ለሷ ያላችሁ የቆሸሸ አመለካከታችሁ የሽንትቤት አር ነውና አርታችሁ ሰትጨርሱ የሷን አማላጅነት ትረዳላችሁ ከማርያም በታች አዜብዬ የኔ ቆንጆ ናት ጌታ አላት ይበቃታል

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule