• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ወሲባዊ ጂሃድ (ጂሃድ አል-ኒቃ)” በሶሪያ!

September 26, 2013 07:29 pm by Editor 6 Comments

የቱኒዚያ ሴቶችና ልጃገረዶች በሶሪያ የአሳድን መንግሥት እየተፋለሙ ከሚገኙት እስላማዊ አማጺያን ጋር “ወሲባዊ ጂሃድ” በመፈጸም በጦርነቱ ላይ ተሳትፏቸውን እየገለጹ መሆናቸው ተነገረ፡፡ በሌላ በኩል በዚሁ ጦርነት ላይ በሳውዲ አረቢያ የሞት ፍርድ የተበየነባቸው ወንጀለኞች እንዲሳተፉ እየተላኩ መሆናቸው ተረጋገጠ፡፡

በያዝነው የመስከረም ወር መጀመሪያ አካባቢ የቱኒዚያው የአገር ውስጥ ሚኒስትር ሎትፊ ቢን ጄዱ በአገሪቱ ፓርላማ ፊት ቀርበው እንደተናገሩት በጦርነቱ ከፍተኛ መስዋዕትነት እየከፈሉ ለሚገኙት ተዋጊዎች ማደፋፈሪያ እንዲሆንና በትግሉ የነርሱንም ድርሻ ለመወጣት የቱኒዚያ ሴቶችና ልጃገረዶች ራሳቸውን በ“ወሲባዊ ጂሃድ” በመስጠት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትር ሎትፊ ቢን ጄዱ (ፎቶ: አልጃዚራ)
ሚኒስትር ሎትፊ ቢን ጄዱ (ፎቶ: አልጃዚራ)

በአረቡ ዓለም በሚገኙ የዜና ማሰራጫዎች በሰፊው የተዘገበው ይህ ዜና እንደሚያስረዳው ሚኒስትሩ ጉዳዩ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ጠቁመዋል፡፡ “እነዚህ ሴቶች” አሉ ሚኒስትር ቢን ጄዱ “እነዚህ ሴቶች (ሶሪያ በሚቆዩበት ጊዜ) ከ20፣ 30፣ 100” አማጺያን ጋር በመተኛት የወሲብ “አገልግሎት” ይፈጽማሉ፡፡  “ወሲባዊ ግንኙነቱንም የሚያደርጉት በ“ጂሃድ አል-ኒቃ” (ማለትም ወሲባዊ ቅዱስ ጦርነት) ስም ሲሆን ወደ ቱኒዚያ የሚመለሱትም እርጉዝ ሆነው ነው” በማለት ሚኒስትሩ ለተከበሩት የፓርላማው አባላት በግልጽ አብራርተዋል፡፡

ከጂሃዲስቶቹ ልጅ አርግዘው የሚመጡት ሴቶች ቁጥር ምን ያህል እንደሆነ ሚኒስትሩ አልጠቆሙም፡፡ ሆኖም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሴቶች በጉዳዩ ላይ እንደሚሳተፉ ከዚህም በተጨማሪ ከ3ሺህ በላይ ቱኒዚያውያን የአማጺያኑን ኃይል ለመደገፍ እንደዘመቱ ይነገራል፡፡ ይህ የቱኒዚያውያኑ ቁጥር በአሳድ ላይ ጂሃድ በማወጅ የሶሪያን አማጺዎች ከተቀላቀሉት የሌላ አገር ዜጎች ከፍተኛውን ቁጥር የያዘ ነው፡፡

ሚኒስትሩ እንደሚሉት ከሆነ እርሳቸው ሥልጣን ከያዙ ካለፈው ዓመት መጋቢት ወር ጀምሮ “ስድስት ሺህ ያህል ወጣቶች በሶሪያ የእርስበርስ ጦርነት እንዳይሳተፉ ለመከልከል” መቻሉን ለፓርላማው አስረድተዋል፡፡ አል አረቢያ ሚኒስትሩን ጠቅሶ እንደዘገበው የቱኒዚያን ድንበር በማቋረጥ ወደ ሶሪያ ለመዝመት የሚፈልጉ ወጣቶችን ለመከላከል በቱኒዚያ የድንበር ቁጥጥር መጠናከሩን ገልጾዋል፡፡ በተጨማሪም በዚህ ድንበር በማሻገር ተግባር ላይ የተሰማሩ 86 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አል አረቢያ ጨምሮ ዘግቧል፡፡

አቡ ኢያድ አል-ቱኒዚ (ፎቶ: አል-ማስዳር)
አቡ ኢያድ አል-ቱኒዚ (ፎቶ: አል-ማስዳር)

በጂሃድ አል-ኒቃ ስም ከጋብቻ ውጪ ከበርካታ ሰዎች ጋር ለወሲብ መተኛት በአንዳንድ አክራሪ የሱኒ ሙስሊም ሳላፊስቶች ዘንድ ተቀባይነት ያለው ቅዱስ ጦርነት (ጂሃድ) ነው፡፡ ይህ በሶሪያ ተከስቷል ተብሎ መነገሩ የሙጃሂዲኑን ቅስም ለመስበር የተደረገ የአሳድ ሴራ ነው በማለት የሚኮንኑት አሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ “ወሲባዊ ጂሃድ” በሶሪያ እንዲካሄድ የሚመሩት አንሳር አል-ሻሪያ የተባለው በቱኒዚያ የዋንኛው ሳላፊስት እንቅስቃሴ መሪ የሆኑት አቡ ኢያድ አል-ቱኒዚ ናቸው በማለት የሚወነጅሏቸውም በርካታዎች ናቸው፡፡

በአረቡ ዓለም ጉዳይ ላይ የሚዘግቡ የዜና ምንጮች እንደሚሉት ግን “ወሲባዊ ጂሃድ” እንዲካሄድ የተደረገው “በፋትዋ” (እስላማዊ ትዕዛዝ) ነው ይላሉ፡፡ ባለፈው ዓመት ታህሳስ ወር ፋትዋውን ያወጡት በሳውዲ አረቢያ ወግአጥባቂ የሳላፊ (ዋሃቢ) መሪ ሼክ ሞሃመድ አል-አሪፊ እንደሆኑ በተለይ ፕሬስ ቲቪ ምንጮቹ ጠቅሶ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ “የአጭር ጊዜ ጋብቻ ወይም ጊዜያዊ ጋብቻ” በሶሪያ ለሚፋለሙት አማጺያን እንደሚያስፈልግና ይህ እንደ ሼክ ሞሃመድ አባባል “የወሲብ ጋብቻ” የአማጺያኑን ቁርጠኝነት የሚያደፋፍር በመሆኑ እስከ 14ዓመት ዕድሜ ያላቸው ወጣት ልጃገረዶችና ሴቶች ሊሳተፉ እንደሚገባና በዚህ ተግባር የሚሳተፉ ሴቶች ሁሉ “ጀነት (ገነት)” የእነርሱ እንደምትሆን ሼኩ ቃል መግባታቸው ፕሬስ ቲቪ አክሎ ገልጾዋል፡፡

ሼክ ሞሃመድ አል-አሪፊ (ፎቶ: Press TV)
ሼክ ሞሃመድ አል-አሪፊ (ፎቶ: Press TV)

ይህ ከተሰማ በኋላ እንዲህ ዓይነቱ ተግባር ፍጹም የተከለከለ (ሃራም) መሆኑን የቀድሞው የቱኒዚያው ታላቁ ሙፍቲ ሼክ ዖትማን ባታኪ በይፋ መቃወማቸውን አል-አላም የዜና አገልግሎት ዘግቦ ነበር፡፡ ወደ ሶሪያ “ለወሲባዊ ጂሃድ” የሚሄዱት ሴቶች “የተታለሉና አእምሯቸው የደነዘዘ” ናቸው በማለት ሼክ ባታኪ ይገልጹዋቸዋል፡፡ ሲቀጥሉም “እንዲያውም በሶሪያ ሊታወጅ የሚገባው ጂሃድ-አክባር (በራስ ላይ የሚታወጅ) ጦርነት” መሆን እንዳለበትና ይህም ራስን ለመቆጣጠር የሚደረግ ጂሃድ በጦርነት ለመፋለም ከመሰለፍ የሚበልጥ “ታላቁ ጂሃድ” እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ውጪ የሚደረገው “ጂሃድ አል-ኒቃ (ወሲባዊ ጂሃድ)” ሴተኛአዳሪነት ወይም ዝሙት እንደሆነ መግለጻቸውን አል-አላም ጨምሮ ዘግቧል፡፡

ታላቁ ሙፍቲ ሼክ ዖትማን ባታኪ (ፎቶ: አለአላም)
ታላቁ ሙፍቲ ሼክ ዖትማን ባታኪ (ፎቶ: አለአላም)

ይህንን ገለጻ ከሰጡ በኋላ ታላቁ ሙፍቲ ሼክ ዖትማን ባታኪ በሥልጣናቸው አልዘለቁም፡፡ ከሥልጣን የመነሳታቸውን ጉዳይ ከተናገሩት የተቃውሞ ንግግር ጋር የተያያዘ እንደሆነ ግን ብዙዎች ይስማሙበታል፡፡

በተያያዘ ዜና በዚሁ እጅግ ደም አፋሳሽ በሆነው የሶሪያ ጦርነት ሳዉዲ አረቢያ ከ1,200 በላይ የሞት ፍርድ የተፈረደባቸውን እስረኞች አማጺያኑን በመደገፍ የአሳድን አገዛዝ እንዲዋጉ በምስጢር መላኳ ተረጋገጠ፡፡ የሳውዲ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚ/ር ይህንን ስጦታ ማቅረቡን አሜሪካ አገር የሚታተመው USA Today የአሶሪያን ዜና አገልግሎት ጠቅሶ ባለፈው ዓመት ሚያዚያ ወር መዘገቡ ይታወሳል፡፡

በወቅቱ “እጅግ ከፍተኛ ምስጢር” በሚል ከአገር ውስጥ ጉዳይ ሚ/ር የተጻፈው ማስታወሻ 1,239 የሞት ቅጣት የተበየነባቸው እስረኞች ወደ ሶሪያ ሄደው በምስጢር አማጺያኑን በመደገፍ እንዲዋጉ፤ ለዚህም ይቅርታ እንዲደረግላቸውና በልዋጭ ለቤተሰቦቻቸው ወርሃዊ የገንዘብ ክፍያ እንዲደረግላቸው በዚሁ ማስታወሻ ላይ ተጠቅሷል፡፡

“በሰይፍ እንዲገደሉ” የተወሰነባቸው እነዚህ እስረኞች ነፍስ በማጥፋት፣ አስገድዶ በመድፈር እና አደንዛዥ ዕጽ በማዘዋወር የተወነጀሉ ናቸው፡፡ የሳውዲ ተወላጆች ከሆኑት ወንጀለኞች በተጨማሪ የአፍጋኒስታን፣ የግብጽ፣ የኢራቅ፣ የዮርዳኖስ፣ የኩዌት፣ የፓኪስታን፣ የፍልስጤም፣ የሶማሊያ፣ የሱዳን፣ የሶሪያ እና የየመን ተወላጆች እንደሚገኙበት ተገልጾዋል፡፡

ምስጢራዊውን መረጃው ሳውዲ አረቢያ አስቀድማ የካደች ቢሆንም የዜና ምንጩ የአረቢኛውን ቅጂ ይፋ በማድረጉና የተላኩት እስረኞች በይፋ ከሰጡት ምስክርነት ጋር ተዳምሮ የሳውዲ መንግሥት ጉዳዩን እንዲያምን አድርጎታል፡፡ በወቅቱ ሳውዲ አረቢያ በተመሳሳይ ተግባር ወደፊት እንደማትቀጥል ለሶሪያም ችግር የፖለቲካ መፍትሔ እንደምትፈልግ የሰጠች ቢሆንም ሰሞኑን የወጡ አንዳንድ መረጃዎች የምስጢራዊውን ሰነድ ትክክለኛነት አረጋግጠዋል፡፡ ከተላኩት እስረኞች መካከል 23 የኢራቅ ተወላጆች እና ቁጥራቸው ያልታወቀ የየመን ተወላጆች ግዳጃቸውን ጨርሰውና ከሞት አምልጠው ወደየአገሮቻቸው ተመልሰዋል፡፡ የተቀሩት ያሉበት ሁኔታ እስካሁን አልተገለጸም፡፡

የሜሶፖታሚያ ሥልጣኔ መስራች የሆኑት አሶሪያውያን የሴም ዝርያ ያላቸውና ከአረቦችና አይሁዶች በዘር ፍጹም የተለዩ ናቸው፡፡ አሶሪያውያን ከክርስቶስ ልደት በፊት በመጀመሪው ሺህ ዓመታት የመካከለኛውን ምስራቅ በበላይነት ይቆጣጠሩ ነበር፡፡ (ሽፋን ፎቶ: አለ-አላም)


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. sentayehu says

    September 27, 2013 03:12 am at 3:12 am

    Betam berto

    Reply
  2. ibrahim ahmed says

    September 27, 2013 12:34 pm at 12:34 pm

    Yalteregagete new photow yemeche yetingaw nigigir lay new . Photo algezira yolal any time attache madreg yichalale . Yezih aynet were yeshia amelekaket new press tv yeshia amelekaket yalew ye iran yetelevision tabiya nwe lesuni tiru amelekaket yelachewim. Batekalay yesoriya mengist megbiya sitefaw yegemerew propaganda new !

    Reply
  3. wey ISLMINA says

    September 27, 2013 06:34 pm at 6:34 pm

    ..I KNOW THIS KIND OF JIHAD ,
    I am so surprised, when they are conformed to go to heaven (JENET) after PORN JIHAD.
    this all what ISLAM means,, I wonder a damondozen of people who follow Islam , especially , the Seilafi , sunni. Islam.
    Even they don’t try to use a mini part of their brain to think , by killing a human being the can get heaven , if God (Alah) wants me to be muslim, why he needs me to be killed? why he created me after all? if he wants the wold to be muslim , Alah (God) has a capability to change all by any means even by miracle , overnight ppl of the world can be muslim if God wants to be so. why he orders others to kill , invade others to make them muslim(by Jihad).
    it is not logical , even if I got heaven I WILL GONNA GET ..7,,12 .. numbers of virgin ? what a shame? what about for women? aren’t they human being ? are they created for pleasures of men ? for sex in the earth and on the sky(heaven)? what an idiot Arab! even they don’t have logical fiction(kurehan) , they copied the old christian bible and add new hadis and fictitiously written by Mohamed warier .
    – If there is Islam no peace at all , see any where in the world , Middle east, philippines starting fighting coz many phipinos went to saudi for house mad when the go back to philipiness the they spread their poison and wants to have Islamic state country. they same is coming soon in Ethiopia, but we will deaf them ,malaysia, pakistan…stans countries.

    Islamism is a new human cancer in 21 century, would attack by beheading innocent kids, women , suicide bombers, destruction of their country , etc.

    May God keep away from Islam jihadist !

    Reply
    • aregahegn says

      October 1, 2013 07:46 am at 7:46 am

      calm down.who r u after all to judge islam.have u ever read Quran?have u any attempt to analayse the hadiths?if so u wont to say all these superficial conclusions.its not ur only pbm,its how westerns work.but be logical before to call others illogical.REMEMBES THAT =JIHAD is not to mean holly war.

      Reply
  4. nwba says

    October 4, 2013 12:32 pm at 12:32 pm

    @wey Islemena እና ለመሰሎችህ… ያንተን ቢናገሩት ሆድ ባዶ ይሆናል….አትቀበጣጥር እስልምና እንደሆነ የፈለጋችሁትን የስም ማጥፋት ዘመቻ ብታደርጉም ህዝብን ከማዳን ከመሳብና ከመስፋፋት ልታግዱት አትችሉም …አላህም እንዲህ ብሏል….ይህን እውነት እኔ እንዳወረድኩት እኔው እጠብቀዋለሁ……ስለዚህ አሁን እናንተ አይደላቹሁም ከናንተ በሚሊዮን ጊዜ የሚበልጥ ጭንቅላት ያላቸው ሰዎች ቢመጡም ብርሃኑን ሊያጠፉት አይችሉም….አንድ አውሮፓዊ ተመራማሪ ያለውን ልንገርህ..እስልምና ላይ ባለፉት 50 ዓመታት የተካሄዱትን ሁሉአቀፍ ጦርነቶች/የቃላት፤የፅኁፍና የስብዕና/ በሌላ አስተሳሰብ ወይም አይዲዮሎጂ ላይ ተካሂዶ ቢሆን ኖሮ ከምድረ ገፅ በጠፋ ነበር… ብሏል…ከገባህ ሌሎች ሳይኳቸው በራሳቸው በአጠገባችን ስልጣኔ አለፈ ብለው ሲጠፉ እያየንበት ባለ አለም ማለት ነው………እምነቱ ምንም ብትሉት ለሰው ልጅ ቀላልና ተፈጥሮአዊ /ምንም ቅኔ፤ ድርሰትና ተውኔት የሌበት/ በመሆኑ ንፁኅ አዕምሮ ላለው ሰው በቀላሉ ቅቡል /ውህድ/ ነው፡፡ ለዚህም ነው በስልጣኔ ገፋን የሚሉ ሰዎችን ሳይቀር በዚህ ሁላ የስም ማጠልሽት ዘመቻ ውስጥ ልባቸውን እየገዛ ያለው…አውሮፓ አሜሪካ አውስትራሊያ ብትሄድ በአሁኑ ጊዜ በጨለማው ዘመን የነበሩ አያቶቻቸው የሰጧቸውን አምሎኮ ቤቶች ወይ ዘግተውታል አልያም ለሙስሊሞች እየሸጡ ያለው….

    Reply
    • ቹቹ says

      November 1, 2013 10:09 pm at 10:09 pm

      @nwba ተራ ልፍለፋ ፖስቱ ሌላ አንተ ሌላ ታወራለህ። ሙስሊሞች ሁልጊዜ የባጥ የቋጡን ታወራላችሁ ምነው ?

      Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule