እኔን ያሰፈራኝ ጎርበጥባጣው መንገድ . . . ኢትዮጵያውያን በግብጽ . . . ሰሞነኛ የማለዳ ወጌን ወደ እናንተ ላደርስ አንዱን አንስቼ አንዱን ስጥል አንድ ወዳጀ ስልክ ደውሎ በግብጵ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአባይን ግድብ ውዝግብ ተከትሎ አደጋ ላይ መሆናቸውን መረጃ ቢጤ አቀበለኝ ። በማስከተልም ከጥቆማ መረጃው ጋር በቀጣዩ ቀን ነዋሪዎች በነቂስ ሰላማዊ ስልፍ ለማደረግ እንዳቀዱ በመግለጽ እንዳነጋግራቸው መከረኝ ። መረጃ ለመሰብሰብ የሚረዱኝን ወንድሞች አድራሻ የሰጠኝን ወንድም አመስግኜ ወደ ሃገረ ግብጽ ካይሮ ደጋግሜ ደወልኩ። ከብዙ ጥረት በኋላ ግን የፈለግኩትን መረጃ ሙሉ በሙሉ ባላገኝም ያገኘሁትን ሰባስቤ ለተጨማሪ መረጃ የሚረዱኝን ተጨማሪ ስልክ ቁጥሮች ሰባሰብኩ። ያሰባሰብኳቸው መረጃዎች ግን ለኢትዮጵያ መጻኤ ህይወት እንድሰጋ እንድፈራ አድርገውኛልና ፈራሁ! ልቤ እንቢ እያለኝ … [Read more...] about ከአረብ ሃገራት ሰማይ እስከ ሚሊንየም አዳራሽ!
Archives for June 2013
የሙስና ምርመራ እየተወሳሰበ ነው!
በጉምሩክና ገቢዎች ባለስልጣን የተጀመረው የጸረ ሙስና ዘመቻ ተከትሎ እየተካሄደ ያለው ምርመራ እየተወሳሰበ መሔዱ ተሰማ። በከፍተኛ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ተከሳሾች የሚሰጡት መረጃ መበላላት ያስነሳል የሚል ፍርሃቻ እያስነሳ ነው። “ሰፈር የለየው” የጸረ ሙስና ዘመቻ የፈጠረው ስጋት የሃይል ሚዛን የያዙትንም ስጋት ውስጥ ከትቷል። በኢትዮጵያ ባለፉት 10 ዓመታት ውስጥ የታየው የውስን ሰዎች በድንገት በመበልጸግ ከባለስልጣኖችና ከከፍተኛ የስርዓቱ ሰዎች ቤተሰቦች ጋር በሚከናወን መተሳሰር አማካይነት እንደሆነ ከህዝብ የተሰወረ አይደለም። ሰሞኑንን ይፋ የተደረገው የባንክና የንብረት እግድ እንዳመለከተው የዝርፊያው ሰንሰለት በቤተሰብ የታጠረ መሆኑን ነው። አቶ መለስ ከድነው ያቆዩትና የሳቸውን ሞት ተከትሎ ከፖለቲካው ልዩነት ጋር በተያያዘ እንደተጀመረ የሚነገርለት የጸረ ሙስና ዘመቻ፣ … [Read more...] about የሙስና ምርመራ እየተወሳሰበ ነው!
የቢሮ ኃላፊው በሙስና ላይ ምስክር ሳይሆኑ ተገደሉ
በነበራቸው የስራ ሃላፊነት በድብቅ መረጃ ሲያሰባስቡ ቆይተው ለመንግስት ካጋለጡ በኋላ ራሳቸውን ደብቀው የነበሩት አቶ ተስፋዬ ኢሬሣ ምሳ እየተመገቡ ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ። አቶ ተስፋዬ ሰኞ ለጸረ ሙስና ኮሚሽን የምስክርነት ቃላቸውን ለመስጠት ከኮሚሽነር አሊ ሱሌማን ጋር ቀጠሮ ይዘው ነበር። በቅርቡ ወደ ፌደራል መንግስት የተዛወሩት የጋምቤላ የቀድሞ ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ኡሞት ኦባንግ፣ ከ83 ሚሊዮን ብር በላይ አላግባብ ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውን፣ እንዲሁም በክልሉ የሚፈጸሙትን የተጭበረበሩ የበጀት አፈጻጸሞችንና ምዝበራዎችን የሚያጋልጡ ሰነዶችን በሚስጥር በማደራጀት ለኢህአዴግ ያቀረቡት አቶ ተስፋዬ አሟሟታቸው አነጋጋሪ ሆኗል። አቶ ተስፋዬ ኢሬሳ ከፍተኛ ምስጢር ያላቸውን ሰነዶች በመያዝ ከመታሰራቸው በፊት መሰወራቸውን፤ “የቢሮ ሃላፊው ይዘው የተሰወሩት መረጃ አቶ ኦሞት … [Read more...] about የቢሮ ኃላፊው በሙስና ላይ ምስክር ሳይሆኑ ተገደሉ
“ፍትሕ ሁሉን አቀፍ የሆነ መብት ነው”
ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለ ማርያም 50ኛ ዓመቱን ለማክበር በዝግጅት ላይ የሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት የመጀመርያ ዙር ተመራቂ ናቸው፡፡ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን አሜሪካ ከሚገኘው የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ያገኙ ሲሆን፣ የፒኤችዲ ዲግሪም ያገኙት እዚያው አሜሪካ ነው፡፡ ዶ/ር ያዕቆብ በቀይ ሽብር ምክንያት ከአገር ከመሰደዳቸው በፊት በሕግ አማካሪነትና በጠበቃነት ያገለገሉ ሲሆን፣ በአሜሪካ ከ20 ዓመታት በላይ በማስተማር ሥራ ላይ ተሰማርተው ቆይተዋል፡፡ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ፍርድ ቤት ሩዋንዳ ውስጥ በዓቃቤ ሕግነት ለሦስት ዓመታት አገልግለዋል፡፡ ወደ ማስተማር ሥራቸው ተመልሰው ለሁለት ዓመታት ከቆዩ በኋላ በተመድ ግብዣ በናይጄሪያና በካሜሩን መካከል የነበረውን የወሰን ክርክር ለማየት ተቀጥረው ለሁለት ዓመታት ያህል አገልግለዋል፡፡ በአብዛኛው በሰው … [Read more...] about “ፍትሕ ሁሉን አቀፍ የሆነ መብት ነው”
ከእሁድ እስከ እሁድ
ኢትዮጵያ ከመለስ ሞት በኋላ!! አቶ መለስ ከሞቱ በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የፖለቲካ ሁኔታ የአሜሪካ ኮንግረስ የውጪ ጉዳዮች ኮሚቴ የተለያዩ ተናጋሪዎችን ጋብዟል። እኤአ ሰኔ 20፤2013 ቀን በሚካሄደው የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ የሚሰማበት ውይይት ከኢትዮጵያ ሁለት ተናጋሪዎች ተጋብዘዋል። ታዋቂው የመብት ተሟጋች፣ በከፍተኛ ደረጃ የኢትዮጵያዊያንን ድጋፍ እያገኙ ያሉትና በውጭው ዓለም የዲፕሎማሲና የፖለቲካ መስመር ተሰሚነታቸው እያደገ የመጣው የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ፣ እንዲሁም በበክኔል ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በዕለቱ ተናጋሪ መሆናቸውን ስብሰባውን ያዘጋጁት ክፍሎች ይፋ አድርገዋል። ከሁለቱ ኢትዮጵያዊያን በተጨማሪ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሳደር የነበሩትና በአሁኑ ወቅት … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
አገር በቤተሰብ ስትዘረፍ ኢህአዴግ የት ነበር?
በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ባለስልጣናት፣ ባለሃብት፣ ደላሎችና ባለድርጅቶች በልጆቻቸውና በቤተሰቦቻቸው ስም "ዘርፈው አስቀመጡት" የተባለው ንብረታቸውና የባንክ ሂሳባቸው መታገዱ ታወቀ። የዜናውን ይፋ መሆን ተከትሎ አዲስ አበባን ያጥለቀለቋት ህንጻዎችና የንግድ ድርጅቶች ጉዳይ ለምን ዝም ተባሉ የሚል ጥያቄ እየተሰነዘረ ነው። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ነጋ ገብረ እግዚአብሔር 54 ተሽከርካሪዎች ተይዘውባቸዋል። ገንዘቡን ሳይጨምር 54 ተሽከርካሪዎች በስማቸው ተመዝግበው የተያዙባቸው አቶ ነጋ ፣ የወ/ሮ አዜብ መስፍን የንግድ ሽሪክ እንደሆኑ የሚያውቋቸው ይገልጻሉ። በኢህአዴግ ጉባኤዎች ላይ የማይቀሩት አቶ ነጋ በየስብሰባው ወቅት ሻይና ቡና ሲሉ ከወ/ሮ አዜብ ጋር አብረው እንደሆነ የሚገልጹት ታዛቢዎች፣ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን “አትሌት … [Read more...] about አገር በቤተሰብ ስትዘረፍ ኢህአዴግ የት ነበር?
አባ ማትያስ “እንዲህ ያለ ፓትርያርክ አይተን አናውቅም”
". . . እንዲህ ያለ ሰው አይተን አናውቅም የሚለው ንግግር አንዱን ከሌላው ጋራ በተመሳሳይ መስፈርት አነጻጽሮ ልቆ የተገኘውን ከፍ አርጎ ለማቅረብ ነው። ይህን ቃል ካፋቸው አውጥተው የተናገሩት አባ ማትያስ ናቸው። የተናገሩትም ለብጹዕ አባታችን ፓትርያርክ ተክለ ሃይማኖት ነው። ምን ጊዜና እንዴት ተናገሩት? አቅራቢውስ ይህን ምስክረነት ለመግለጽ ያስቻለው በዚህ ወቅት የት ነበር? የሚሉ ጥያቄዎች ባንባቢ ህሊና ላይ መፈጠራቸው አይቀርም። "ለምስክርነት ያበቃኝን ዝርዝር በዚህች ጦማር ለማቅረብ ሰአት ወስኖኛል። አስፈላጊ ከሆነ ዝርዝር ሀተታውን ከዚህች ጦማር ቀጥየ ማቅረብ እችላለሁ። . . ." (ሙሉውን ጥናታዊ ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about አባ ማትያስ “እንዲህ ያለ ፓትርያርክ አይተን አናውቅም”
የዶ/ር መሠረት ቸኮል አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ
በቅርቡ ያረፉት ዶ/ር መሠረት ቸኮል ላለፉት 8 ዓመታት ሲለፉባት የነበረውና የኢትዮጵያን የ100 የፕሬስ ታሪክ የሚያሳይ መጽሐፍ ለገበያ መቅረቡን ቤተሰቦቹ ገለጹ። ጥልቀት ባላቸው ትንታኔዎቹና ቀላል አቀራረቡ የሚታቀው ጋዜጠኛና መምህር ዶ/ር መሠረት ቸኮል የጻፈው ታሪካዊው መጽሐፍ “The Quest for Press Freedom: One Hundred Years of History of the Media in Ethiopia” የሚሰኝ ሲሆን በamazon.com እንዲሁም በባርነስ ኤንድ ኖብል የመጽሐፍት መሸጫ መደብሮች እንደሚገኙ ቤተሰቦቹ ገልጸዋል። ይህ መጽሐፍ ለማስተማሪያነት ሁሉ ታስቦ እንደተጻፈ የገለጹት የዶ/ር መሠረት ባለቤት ወ/ሮ በልዩ ወደፊት መጽሐፉን በአማርኛ ለማሳተም እንደተዘጋጁም ገልጸዋል። “ዶ/ር መሠረት ይህን መጽሐፍ በአማርኛም ጀምሮት ነበር። ሆኖም ግን በድንገት ሳጨርሰው በማረፉ … [Read more...] about የዶ/ር መሠረት ቸኮል አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ
ኢሕአፓ በአዲስ አበባ በርካታ ቦታዎች በህቡዕ ወረቀት በተነ
በስውር የሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያ ህዝብ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)አባላት በአዲስ አበባ በርካታ ቦታዎች ረቡዕ ሌሊት ሰኔ 5/2005 ዓ.ም. /June 12, 2013/ "ተነሥ" በሚል ርዕስ የተዘጋጁ ቀስቃሽ ፅሑፎችን የበተኑ ሲሆን በዋናነት በቦሌ፣በካዛንቺስ፣በአራት ኪሎ፣በሽሮ ሜዳ፣በቄራ፣በፈረንሳይ ለጋሲዪን፣በሜክሲኮ፣በፒያሳ፣በመገናኛ፣በኮልፌ፣በመርካቶ፣በጎፋ እና በመሳሰሉት ዋና ዋና የከተማዋ ክፍል በሚገኙ የማስታወቂ ቦርዶች ላይ ተለጥፈው የታዩ ሲሆን በተለይ ሐሙስ ሰኔ 6/2005 ዓ.ም. በርካታ ነዋሪዎች ጽሑፉን ማንበብ ችለዋል።ይሁን እንጂ ይህ ዜና የደረሳቸው የገዢው ፓርቲ አመራሮች ወዲያው የፌደራል ፖሊሶችን እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላትን በማሰማራት በዋና ዋና ቦታዎች ላይ የሚገኙትን ያነሱ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢ ግን ጽሑፎቹ እስከ ቀትር ሳይነሱ በበርካታ ሰዎች መነበብ … [Read more...] about ኢሕአፓ በአዲስ አበባ በርካታ ቦታዎች በህቡዕ ወረቀት በተነ
አስቸጋሪው ነገር አገርን መገንባት ነው!!
ወያኔን ማስወገድ አይደለም የሚያስቸግረው፤ አስቸጋሪው ነገር አገርን መገንባት ነው !! "We are just leaving barbarism and are still entirely at the beginning. The French, however have already gone a piece of the way and have a century`s lead in every respect.” Friedrich the Great II to Wilhelm of Prussia መግቢያ የወያኔን አገዛዝ ነፍስ ለመዝራት፣ ወይንም የአገዛዙን ዕድሜ ለማራዘም የሚደረገውን በአንዳንድ ምሁሮች የሚነዛውን የማያስፈልግ አጻጻፍ ትተን፣ እስከዛሬ ድረስ በተለይም ብዙዎቻችንን ያሰጨነቀንና የሚያስጨንቀን፣ የቀድሞዎቹ አገዛዝም ሆነ ወያኔ ያተራመሰውን አገር እንዴት መገንባት አለብን ? የሚለው ሳይሆን፣ እሱን አስወግዶ እንዴት ስልጣን መያዝ … [Read more...] about አስቸጋሪው ነገር አገርን መገንባት ነው!!