“. . . እንዲህ ያለ ሰው አይተን አናውቅም የሚለው ንግግር አንዱን ከሌላው ጋራ በተመሳሳይ መስፈርት አነጻጽሮ ልቆ የተገኘውን ከፍ አርጎ ለማቅረብ ነው። ይህን ቃል ካፋቸው አውጥተው የተናገሩት አባ ማትያስ ናቸው። የተናገሩትም ለብጹዕ አባታችን ፓትርያርክ ተክለ ሃይማኖት ነው። ምን ጊዜና እንዴት ተናገሩት? አቅራቢውስ ይህን ምስክረነት ለመግለጽ ያስቻለው በዚህ ወቅት የት ነበር? የሚሉ ጥያቄዎች ባንባቢ ህሊና ላይ መፈጠራቸው አይቀርም።
“ለምስክርነት ያበቃኝን ዝርዝር በዚህች ጦማር ለማቅረብ ሰአት ወስኖኛል። አስፈላጊ ከሆነ ዝርዝር ሀተታውን ከዚህች ጦማር ቀጥየ ማቅረብ እችላለሁ። . . .” (ሙሉውን ጥናታዊ ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
koster says
in woyane ethnic fascists new Ethiopia, everything has to be new. DIABLOS was also different and what he did with Beyonce and others only GOD and himself knows
Birhan says
ቀሲስ አስተርዓየ ስለ እመቤታችን ጥንተ አብሶ አቋምህ በቶሎ ንስሀ ግባ።አኃት አብያተ ክርስቲያናት እያልክ አታደንቁረን። አንተ የምትመካባቸው አኃት አብያተ ክርስቲያናት በታቦት አያምኑም። እና እኛም የእነርሱን ፈለግ ተከትለን ታቢታቶቻችንን ለቃቅመን እንድንጥል ትፈልጋለህ? ሌላም ከእኛ የማይገጥሙ ብዙ ነገሮች አሏቸው። ከእነዚህ ውስጥ አንዱ በጥንተ አብሶ ላይ ያለን ትምህርት ነው። በዚህ ትምህርት ካቶሊኮች ከእኛ ጋር ከተመሳሰሉ ልናደንቃቸው ይገባል እንጂ እኛን አያሳፍረንም። ከአኃት አብያተክርስቲያናት ጋር ያለን አንድነት Unity with diversity መሆኑን ተገንዝበህ ራስህን በጊዜ አስተካክል። በተሃድሶ ኑፋቄ የአባቶቻችንን ትምህርትና የእመቤታችንን ክብር አታቃልል። አኃት አብያተ ክርሰቲያናት እንኳን ከእኛ ጋር እርስ በርሳቸውም የማይገጥሙ ብዙ ነገሮች አሏቸው። ድንግል ማርያም ልቡና ትስጥህ። አሜን።