እኔን ያሰፈራኝ ጎርበጥባጣው መንገድ . . .
ኢትዮጵያውያን በግብጽ . . .
ሰሞነኛ የማለዳ ወጌን ወደ እናንተ ላደርስ አንዱን አንስቼ አንዱን ስጥል አንድ ወዳጀ ስልክ ደውሎ በግብጵ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአባይን ግድብ ውዝግብ ተከትሎ አደጋ ላይ መሆናቸውን መረጃ ቢጤ አቀበለኝ ። በማስከተልም ከጥቆማ መረጃው ጋር በቀጣዩ ቀን ነዋሪዎች በነቂስ ሰላማዊ ስልፍ ለማደረግ እንዳቀዱ በመግለጽ እንዳነጋግራቸው መከረኝ ። መረጃ ለመሰብሰብ የሚረዱኝን ወንድሞች አድራሻ የሰጠኝን ወንድም አመስግኜ ወደ ሃገረ ግብጽ ካይሮ ደጋግሜ ደወልኩ። ከብዙ ጥረት በኋላ ግን የፈለግኩትን መረጃ ሙሉ በሙሉ ባላገኝም ያገኘሁትን ሰባስቤ ለተጨማሪ መረጃ የሚረዱኝን ተጨማሪ ስልክ ቁጥሮች ሰባሰብኩ። ያሰባሰብኳቸው መረጃዎች ግን ለኢትዮጵያ መጻኤ ህይወት እንድሰጋ እንድፈራ አድርገውኛልና ፈራሁ! ልቤ እንቢ እያለኝ ጥረቴን ገፋሁበት . . . ” (ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል)
Mammo says
ሰላምታ ይድረስ ነብዩ ሲራክ በርግጥ ብዙ ብዙ ሊታዩና ሊታረሙ የሚገባ ብዙ እርማቶች ኣሉ ኣንዳንዴ ሳስበው በመንግስት ሆነ በተቃዋሚ ግሩፕ ያለውን እልክ ስመለከት እንኳን 93 ሚሊዮን ህዝብን ሰፈርን ለማስተዳደር ብቃት ያንሳቸዋል በርግጥ ሃገር የምታድገው ለማነው ለመጪው ትውልድ መልካምን ነገር ትቶ ለማለፍ ኣይደለምን? እስቲ ለ 50 ኣመት ምን ታቀደ ብለን ብንጠይቅ መልስ በርግጠኝነት ኣናገኝም. ይህን ያስባለኝ ዛሬ ላይ ለውስን ሰዎች ኪስ ማሙያ ተብሎ ንዑህ ዜጎቻችን ለኣረብ ግርድና ተዳርገዋል እየተዳረጉም ነው ያለው በቅርቡ በወጣው ለቤት ፈላጊዎት መስፈርት ከውስጥ ኣዋቂ እዳገኘውት መረጃ በ አረብ ሀገር በተለይ ኩዌት የ ኢትዮጵያ ኢንባሲ ለዜጎቹ ምንም ኣይነት እርዳታ የማያደርግ ከመሆኑም ኣልፎ በስቃይ ያሉት ወደ ኢምባሲ መጥተው የይድረሱልኝ ጩኧት ሲያሰሙ ሜዳ ላይ እያደሩ እንደዜጋ ሳይሆን በጥላቻ በማመናጨቅ ከግቢ እያባረረ ዛሬ ላይ ግን ውሽቱን አዲስ አበባ ላይ ቤት ታገኛላችው በማለት መስፈርቱን የማያሙዋሉ ፡ የአዲስ አበባ ነዋሪ ያልሆኑትን ጭምር ለኮንደሚኒየም በማለት ከያንዳንዱ ወደ 45 ሲባዛ 2.50 ዶልላር 112.50 USD ከንዚህ ሚስኪን ድሃ ወገን ላይ በመውሰድ ላይ ይገኛል እኔ ባለሁበት አካባቢ እንደሰማሁት ለ ዲያስፖራ 40/60 ገና እንደሆነ ነው በዚህ ዙርያ ይበልጥ የምታውቅ ከሆነ ያላግባብ ድሃው ወገን አንዳይዘረፍ ማሳሰብ ኣልብን በማለት ዕሁፈን ልቋጭ ችር ይግጠመን
Atse Tewodros says
ከ ጉያችን የዎጣው ትልቁ ጠላታችን ዎያኔ፥ በየመንግስት መስሪያ ቤቱ የራሱን ቡችሎች እያሰማራ ብዙሃን የተማሩ ዎጣቶችን ለ ጎዳና አና ለስደት መዳረጉን ያቁም፥