• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከእሁድ እስከ እሁድ

June 17, 2013 06:49 am by Editor Leave a Comment

ኢትዮጵያ ከመለስ ሞት በኋላ!!

አቶ መለስ ከሞቱ በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የፖለቲካ ሁኔታ የአሜሪካ ኮንግረስ የውጪ ጉዳዮች ኮሚቴ የተለያዩ ተናጋሪዎችን ጋብዟል። እኤአ ሰኔ 20፤2013 ቀን በሚካሄደው የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ የሚሰማበት ውይይት ከኢትዮጵያ ሁለት ተናጋሪዎች ተጋብዘዋል።

ታዋቂው የመብት ተሟጋች፣ በከፍተኛ ደረጃ የኢትዮጵያዊያንን ድጋፍ እያገኙ ያሉትና   በውጭው ዓለም የዲፕሎማሲና የፖለቲካ መስመር ተሰሚነታቸው እያደገ የመጣው የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ፣ እንዲሁም በበክኔል ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በዕለቱ ተናጋሪ መሆናቸውን ስብሰባውን ያዘጋጁት ክፍሎች ይፋ አድርገዋል።

ከሁለቱ ኢትዮጵያዊያን በተጨማሪ  ቀደም ሲል በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሳደር የነበሩትና በአሁኑ ወቅት የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ተጠባባቂ  ጸሐፊ ሆነው እየሰሩ ያሉት ዶናልድ ያማማቶ፣  የአሜሪካ የዓለምአቀፍ የልማት ተራድዖ የአፍሪካ ቢሮ ረዳት አስተዳዳሪ ኤሪል ጋስትና የማይክል አንሳሪ የአፍሪካ ተቋም ዳይሬክተር ዶ/ር ፒተር ፓሃም ንግግር ያቀርባሉ። ምክከሩ በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፍ ሲሆን የውይይቱ ዋና ጉዳይ ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታና ከመለስ ሞት በበኋላ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት አያያዝና የዲሞክራሲ አተገባበር ዙሪያ ጭብጥ የሚያዝበት ነው። (የጥሪው ደብዳቤ መሉ ቃል እንዲህ ይነበባል)

SUBCOMMITTEE HEARING NOTICE

COMMITTEE ON FOREIGN AFFAIRS

Subcommittee on Africa, Global Health, Global Human Rights, and International Organizations Christopher H. Smith (R-NJ), Chairman

TO: MEMBERS OF THE COMMITTEE ON FOREIGN AFFAIRS

You are respectfully requested to attend an OPEN hearing of the Committee on Foreign Affairs, to be held by the Subcommittee on Africa, Global Health, Global Human Rights, and International Organizations in Room 2172 of the

Rayburn House Office Building (and available live on the Committee website at www.foreignaffairs.house.gov):

DATE: Thursday, June 20, 2013

TIME: 10:00 a.m.

SUBJECT: Ethiopia After Meles: The Future of Democracy and Human Rights

WITNESSES: Panel I

The Honorable Donald Y. Yamamoto

Acting Assistant Secretary of State

Bureau of African Affairs

U.S. Department of State

The Honorable Earl W. Gast

Assistant Administrator

Bureau for Africa

U.S. Agency for International Development

Panel II

 Berhanu Nega, Ph.D.

Associate Professor of Economics

Bucknell University

 J. Peter Pham, Ph.D.

Director

Michael S. Ansari Africa Center

Atlantic Council

Mr. Obang Metho

Executive Director

Solidarity Movement for a New Ethiopia

ግብፅ የያዘችው አቋም ተቀባይነት የለውም

ግብፅ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ጉዳይ ለውስጥ የፖለቲካ ችግሯ መፍቻነት እያዋለችው መሆኑን የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትር  በረከት ስምኦን ገለፁ፡፡ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አቶ አለማየሁ ተገኑ በበኩላቸው ግብፅ የግድቡን የሃይል ማመንጨት አቅም መቀነስ እንደመፍትሔ ማቅረቧ ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡

የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትርና የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ፅ/ቤት ዳይሬክተር አቶ በረከት ስሞኦን ግብፅ ለውስጥ የፖለቲካ ችግሯ መፍቻነት እያዋለችው መሆኑን ተናግረዋል፡፡abay1

የግንባታ ሂደቱ 22 ነጥብ 5 በመቶ የደረሰውና በተያዘው ዓመት 26 በመቶ ስራው እንደሚጠናቀቅ የሚጠበቀው የህዳሴው ግድብን አስመልክቶ አንዳንድ የተቃዋሚ ፓርቲዎች የያዙት አቋም ትክክል አለመሆኑንም ሚኒስትር በረከት ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትር በረከት አያይዘው እንደገለፁት ግብፅ ጉዳዩን የውስጥ የፖለቲካ ችግሯን ለማርገብ እየተጠቀመችበት መሆኑን ጠቅሰው ሀገሪቱ የጦርነት አማራጭ የተዘጋ አይደለም ትበል እንጂ ወደዚህ ተግባር ትገባለች ተብሎ አይጠበቅም ብለዋል፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር አለማየሁ ተገኑ በበኩላቸው የጦርነት አማራጭ እንደማያዋጣ የተገነዘበ የሚመስለው የግብፅ መንግስት የህዳሴን ግድብ የማመንጨት አቅም፣ የሚይዘውን የውሃ መጠንና ከፍታ እንዲቀንስ የሚያነሳው የመፍትሔ ሃሳብ ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡

የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትርና የታላቁ ህዳሴ ግድብ የህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ፅ/ቤት ዳይሬክተር በረከት ስሞኦን እና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር አለማየሁ ተገኑ በተገኙበት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮና በ ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 በህዳሴው ግድብ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ባተኮረው  የቀጥታ ውይይት ላይ በአገር ውስጥና ውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እያሳዩት ያሉትን ግድቡን የመገንባት ቁርጠኝነትና ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ሃላፊዎቹ ጥሪ አቀርበዋል፡፡ (ምንጭ፤ ኢሬቴድ)

ፓርላማው የቅኝ ግዛት ዘመን ውል የሚተካ አዲስ ህግ አፀደቀ

አሥራ አንዱ የአባይ ተፋሰስ ሃገሮች ሩዋንዳ፣ ቡሩንዲ፣ ኮንጎ ፣ ታንዛኒያ፣ ኬንያ፣ ዩጋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ግብፅ ናቸው፡፡ የተፋሰሱ አገራት በተመለከቱበት ካርታ ላይ ደቡብ ሱዳን አልተካተተችም። ካርታው ሲሰራ ደ/ሱዳን በወቅቱ ነጻ አገር አልነበረችም ነበር።

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ33ተኛው መደበኛ ስብሰባው ከመከረባቸው አምስት ጉዳዮች አንዱ የሆነውን የአባይ ተፋሰስ የትብብር ስምምነት ረቂቅ አዋጅ እንዳፀደቀ የምክር ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አያና ከበደ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

nile_basin_countriesስምምነቱ አባይን በጋራና በፍትሃዊ መንገድ ለመጠቀም በተፋሰሱ አባላት አገሮች ካሁን ቀደም ኢንቴቤ-ዩጋንዳ ውስጥ የተፈረመ መሆኑ ይታወቃል።

ከኢትዮጵያ በስተቀር አምስቱ አገሮች ማለትም የርዋንዳ፣ የታንዛኒያ፣ የዩጋንዳ፣ የኬንያና የቡሩንዲ ፓርላማዎች ቀደም ብለው ውሉን ያፀደቁት መሆኑን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያው ተናግረዋል።

የኢንቴቤ ስምምነት እየተባለ የሚጠራው ውል ቅኝ ገዢ በነበረችው ታላቋ ብሪታኒያ በአውሮፓ የዘመን አቆጣጠር በ1929 ዓ.ም የተረቀቀና በናይል ወንዝ አጠቃቀም ላይ ከተፋሰስ አገሮች ይልቅ ለግብፅ ሙሉ መብት የሚሰጠውን ውል የሚተካ መሆኑ ይታወቃል።

ውሉ ዛሬ በኢትዮጵያ የተወካዮች ምክር ቤት መፅደቁ ሰሞኑን በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል በአባይ ወንዝ አጠቃቀም ዙሪያ ከሚካሄደው ውዝግብ ጋር ግንኙነት እንደሌለው የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያው ተናግረዋል፡፡(ምንጭ የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ)

በአባይ ግድብ ዙሪያ ከፍተኛ ጥበቃ ማድረግ ተጀመረ

ለኢሳት የደረሰው የደህንነት መረጃ እንዳመለከተው ከፍተኛ ወጪ የወጣባቸው ቻይና እና ሩሲያ ሰራሽ ራዳሮች ሰሞኑን በአካባቢው ተተክለዋል።

መንግስት ማንኛውንም አይነት ድንገተኛ የአየር ወይም የሰርጎ ገቦች ጥቃት ለመከላከል ዘመናዊ ራዳሮችን ከመትከል በተጨማሪ የተወሰኑ የአጋዚ ክፍለ ጦር አባላት በአስችኳይ ወደ አካባቢው እንዲንቀሳቀሱ አድርጓል። በፌደራል ፖሊስ ሲደረግ የነበረው ጥበቃ በመከላከያ ሰራዊት አባላት እንዲጠናከር ያደረገው መንግስት ፣ በሻለቃ አበራ ወረታው አዛዥነት የሚመራውradar የምእራብ እዝ የ44ኛ ዳሎል ክፍለ ጦር አራተኛ ሪጂመንት በቤንሻንጉል እንዲቀመጥ ተወስናል።

በደቡብ ሱዳን ያለው ጦር የአቅም ግንባታ ስልጠና እንዲያገኝም አብዩታዊ ዴሞክራሲ እና ወታደራዊ አመራር የሚል ርእስ ያዘለ የመወያያ ጽሁፍ ተዘጋጅቶ በ ስልጠና ዋና መምሪያ ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ የሚመራ ቡድን ወደ አብየ አቅንቷል፡፡

ኢሳት የደረሱትን ሙሉ ወታደራዊ የደህንነት መረጃዎች ለአገር ደህንነት ሲባል ይፋ ከማውጣት መቆጠቡን ለመግለጽ ይወዳል። የኮሚኒኬሽን ሚኒስትሩ አቶ በረከት ስምኦን ኢትዮጵያ ምንም አይነት ወታደራዊ ዝግጅት እያደረገች አይደለም በማለት ሰሞኑን መግለጫ ቢሰጡም፣ ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ ግን ኢትዮጵያ ግድቡን ከጥቃት ለመከላከል እንቅስቃሴዎችን ጀምራለች።

በሌላ ዜና ደግሞ የግብጽ መንግስት ኢትዮጵያ በግድቡ ላይ የማሸሻያ እርምጃ እንድታደርግ መጠየቁ ታውቋል። የግብጽ መንግስት ያቀረበው ጥያቄ የግድቡ ከፍታ ከነበረበት 145 ሜትር ወደ 100 ሜትር ዝቅ እንዲል፣ 74 ቢሊዩን ሜትር ኩብ ውሃ እንደሚይዝ የሚጠበቀው አዲሱ ሀይቅ   ከ 32 እስከ   40 ቢሊዩን ሜትር ኩብ ውሀ እንዲቀንስ መጠየቁን የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ የሀይል አቅርቦቱም ወደ 3000 ሜጋ ዋት እንዲቀንስ የግብጽ መንግስት ጥያቄ አቅርቧል። (ምንጭ፤ ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና)

ለአማራው መፈናቀል ተጠያቂ የተባሉ 2 የቤኒሻንጉል ም/ቤት አባላት ያለመከሰስ መብት ተነሳ

የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ምክር ቤት ትናት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ በክልሉ ነባር የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆች መፈናቀል ምክንያት ናቸው ያላቸውን 2 የምክር ቤት አባላትን ያለ መከሰስ መብት አነሳ።

benishangulያለ መከሰስ መብታቸው ተነስቶ በቁጥጥር ስር ውለው በህግ እንዲጠየቁ የተደረገው በክልሉ ከማሺ ዞን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መለተጊ ቦጋለና የመንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ሃላፊው አቶ ገርቢ በጊዜው ናቸው።

እነዚህ አመራሮች የክልሉ መንግስትና ፓርቲው በማያውቀው ሁኔታ በዞኑ ያሶ ወረዳ ነባር የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆችን እንዲፈናቀሉ ማድረጋቸው በመረጃ በመረጋገጡ ነው እርምጃው የተወሰደባቸው።

በዚህ የማፈናቀሉ ተግባር ተሰማርተዋል ተብለው የተጠረጠሩ 18 የሚደርሱ ከቀበሌ እስከ ዞን የሚገኙ አመራሮች ጉዳያቸው እየተጣራም ይገኛል።

የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ይስሀቅ አብዱልቃድር ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት ፥ የክልሉ መንግስት ጉዳዩን በማጣራት ባአሁኑ ጊዜ ተፈናቃዮች ተረጋግተው ወደቀያቸው ተመልሰው መደበኛ ኑሮዋቸውን እያከናወኑ ነው። አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8 ፣ 2005 (ኤፍ.ቢ.ሲ)

“ዋነኛው የእንግልት ሰለባ አህያው ነው”

ፖሊስና እርምጃው በግንቦት 30 እትሙ በምስራቅ ሸዋ መቂ ከተማ ውስጥ አንድ ግለሰብ ጅብ አጥምዶ ፤ ከማጥመዱም በአህያ በሚጎተት ጋሪ ጭኖ ሲዘዋወር በመገኘቱ ‹‹እንሰሳትን በማንገላታት›› ክስ መታሰሩን ነግሮናል፡፡

ሰውየው ‹‹ጅቡን ከነነፍሱ ያጠመድኩት እየተፋፋመ ያለውን የፀረ ሙስና ትግል መቀላቀሌን ለማሳየት ነው›› ካላለ በስተቀር ትንሽ በቁጥጥር ስር ሳይቆይ አይቀርም፡፡donkey

‹‹እንሰሳትን በማንገላታት›› የሚለው ክስ እንግልቱ በየትኛው እንሰሳ ላይ እንደተፈፀመ አጥርቶ ባይገልፅም፤ እንደኔ በዚህ ጉዳይ ዋነኛው የእንግልት ሰለባ አህያው ነው፡፡

መደበኛ የሸክም እንግልቱን ተዉት፡፡ ይህ አህያ ታሪካዊ አዳኙን/ ጠላቱን ከነነፍሱ ተሸክሞ ሲዞር ‹‹ካሁን አሁን ዘነጠለኝ›› እያለ መሳቀቁ ብቻ ከባድ የስነልቦና እንግልት አይደለም?

ይህን ጅቦችን ተሸክመው ሲሄዱ የኖሩ ምስኪን አህዮች ሁሉ ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡

ወጣም ወረደ፤ ክሱ ጅቡን የእንግልቱ ተጠቂ አድርጎ ያቀረበ መሆኑን ከሰማን ‹፣ድሮም የኛ ሕግ ለጅቦች ያዳላል›› ማለታችን የማይቀር ነው፡፡

(ምንጭ፤ ነቆራ እና ሌሎችም ወጎች ከሕይወት እምሻው ጋር – Hiwot Emishaw)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm
  • በዓባይ ግድብ ምረቃ፡ የሕዝብ ደስታ፣ የቴድሮስ ካሳሁን ዝምታ September 14, 2025 04:27 am
  • ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው  August 29, 2025 11:46 pm
  • መከላከያ በፋኖ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ፤ ዘመነ በ“አንድ ማንኪያ ቅንነት” አንድ እንሁን አለ August 23, 2025 12:35 am
  • ፋኖን በፋይናንስና በሎጂስቲክስ የሚደግፉ የጎጃም ባለሃብቶች ከስደት ሊመለሱ ነው August 14, 2025 12:42 am
  • የበቀለ ገርባ የአሜሪካ ጥገኝነት ማመልከቻ ውድቅ ተደረገ August 13, 2025 12:16 pm
  • ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ August 13, 2025 12:58 am
  • የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?  August 5, 2025 09:18 pm
  • የባከነ የስደት ሕይወት ከደባርቅ እስከ ኖርዌይ July 29, 2025 05:44 pm
  • “በዚህ ዓመት መጨረሻ ትግራይን እንቆጣጠራለን”፤ ቲፒኤፍ July 22, 2025 01:28 am
  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm
  • የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ May 14, 2025 11:07 pm
  • ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች መገደላቸው ተነገረ May 6, 2025 10:40 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule