• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኢሕአፓ በአዲስ አበባ በርካታ ቦታዎች በህቡዕ ወረቀት በተነ

June 13, 2013 12:01 am by Editor 1 Comment

በስውር የሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያ ህዝብ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)አባላት በአዲስ አበባ በርካታ ቦታዎች ረቡዕ ሌሊት ሰኔ 5/2005 ዓ.ም. /June 12, 2013/  “ተነሥ“  በሚል ርዕስ የተዘጋጁ ቀስቃሽ ፅሑፎችን የበተኑ ሲሆን በዋናነት በቦሌ፣በካዛንቺስ፣በአራት ኪሎ፣በሽሮ ሜዳ፣በቄራ፣በፈረንሳይ ለጋሲዪን፣በሜክሲኮ፣በፒያሳ፣በመገናኛ፣በኮልፌ፣በመርካቶ፣በጎፋ እና በመሳሰሉት ዋና ዋና የከተማዋ ክፍል በሚገኙ የማስታወቂ ቦርዶች ላይ ተለጥፈው የታዩ ሲሆን በተለይ ሐሙስ ሰኔ 6/2005 ዓ.ም. በርካታ ነዋሪዎች ጽሑፉን ማንበብ ችለዋል።ይሁን እንጂ ይህ ዜና የደረሳቸው የገዢው ፓርቲ አመራሮች ወዲያው የፌደራል ፖሊሶችን እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላትን በማሰማራት በዋና ዋና ቦታዎች ላይ የሚገኙትን ያነሱ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢ ግን ጽሑፎቹ እስከ ቀትር ሳይነሱ በበርካታ ሰዎች መነበብ ችለዋል።

የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በ5ለ1 አደረጃጀት ጠርንፎ እንደያዘ የሚነገርለት ኢህአዴግ ይህ አይነቱ ድንገተኛ ክስተት ዛሬም ድረስ ከህዝብ ጋር ሆድ እና ጀርባ እንደሆነ የሚያሳይ ነው ሲሉ አንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች ትዝብታቸውን የገለፁ ሲሆን የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የአዲስ አበባ ጽ/ቤት እና የአዲስ አበባ የወጣቶች ሊግ አመራሮች አስቸኳይ ስብሰባ ሐሙስ ዕለት እንደተቀመጡ ከስፍራው መረዳት ተችሏል።

“ተነሥ“  በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የዚህ ጽሑፍ ይዘት የሚከተለው ነው፦ “እጅግ የተከበርከው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ፦ የአኩሪ ታሪክ ባለቤት፤ይልቁንም ለጥቁር ህዝቦች የነፃነት ጮራን የፈነጠቅህ ፋና ወጊ የነፃነት አርበኛ መሆንህ የአደባባይ ምስጢር ነው።ይሁን እንጂ የዚህ ሁሉ ጥንካሬህ መሠረት የሆነው አንድነትህ በጎጠኛው የወያኔ ቡድን የዘውጌ አስተዳደር ተሸርሽሮ ዛሬ በሀገርህ ተንቀሳቅሰህ የመስራት መብትህ ተገድቦ፣ከችሎታህና ከግለሰባዊ ክህሎትህ ይልቅ በዘር ማንነትህ እየተመዘንክ የኢኮኖሚ መገለል እየደረሰብህ ህይወት ብርቱ ሠልፍ ሆናብህ ሀገርህን ጥለህ እንድትሰደድ በተሰላ ስሌት በመኖርና ባለመኖር ቅርቃር ውስጥ እንድትባዝን ተደርገህ፣ሰብዓዊና ዴሞክራሲዊ መብትህ ተገፎ የመናገርና ሃሳብህን በነፃነት የማራመድ መብትህን ከመነጠቅህ ባሻገር በአጠቃላይ ህልውናህ በወያኔ የግፍ መዳፍ ውስጥ ወድቋል።ስለሆነም እንደመዥገር በላይህ ላይ ተጣብቆ በደምህ የሰባውን ይህን ዘረኛ ቡድን ከጫንቃህ ላይ አራግፈህ በፍትህ አደባባይ የምታቆምበት ጊዜው አሁን ነው።ሀገርህንና ራስህን ለማዳን ተነሥ!!!”

By: Beyene Mesfin

Filed Under: Opinions

Reader Interactions

Comments

  1. Tenager says

    June 22, 2013 04:03 pm at 4:03 pm

    Dear brothers,

    It is good to hear this information!!! But, we should think over and over not to repeat the previous weakness and loss of life. This means a very systematic care must be taken for the safety of participants’ life of within the country. If I were them, I really don’t know what to decide in taking such kind of action where everything is very tight. I always praise our heroes who usually determined to do such things. When I say this, I am not sending the spirit of fear for the truth, but this is just to remind you on what action should be taken to be very successful. Lets learn from our past weakness.

    God bless Ethiopia!!!

    Tenager

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
Copyright © 2026 · Goolgule