• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የዶ/ር መሠረት ቸኮል አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ

June 13, 2013 08:05 am by Editor Leave a Comment

በቅርቡ ያረፉት ዶ/ር መሠረት ቸኮል ላለፉት 8 ዓመታት ሲለፉባት የነበረውና የኢትዮጵያን የ100 የፕሬስ ታሪክ የሚያሳይ መጽሐፍ ለገበያ መቅረቡን ቤተሰቦቹ ገለጹ። ጥልቀት ባላቸው ትንታኔዎቹና ቀላል አቀራረቡ የሚታቀው ጋዜጠኛና መምህር ዶ/ር መሠረት ቸኮል የጻፈው ታሪካዊው መጽሐፍ “The Quest for Press Freedom: One Hundred Years of History of the Media in Ethiopia” የሚሰኝ ሲሆን በamazon.com እንዲሁም በባርነስ ኤንድ ኖብል የመጽሐፍት መሸጫ መደብሮች እንደሚገኙ ቤተሰቦቹ ገልጸዋል።

ይህ መጽሐፍ ለማስተማሪያነት ሁሉ ታስቦ እንደተጻፈ የገለጹት የዶ/ር መሠረት ባለቤት ወ/ሮ በልዩ ወደፊት መጽሐፉን በአማርኛ ለማሳተም እንደተዘጋጁም ገልጸዋል። “ዶ/ር መሠረት ይህን መጽሐፍ በአማርኛም ጀምሮት ነበር። ሆኖም ግን በድንገት ሳጨርሰው በማረፉ ወደፊት አስተርጉመን ለማቅረብ እንሞክራለን” ያሉት ወ/ሮ በልዩ ይህን መጽሐፍ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንዲያነቡት ጋብዘዋል።

የዶ/ር መሠረት ቸኮልን መጽሐፍ ከኢንተርኔት ላይ ለመግዛት እዚህ ይጫኑ በመጽሐፉ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ ለምትፈልጉ ወ/ሮ በልዩን በስልክ ቁጥር 651-983-2052 በመደወል ማነጋገር ትችላላችሁ።

ዶ/ር መሠረት ቸኮል ማን ነበር?

ከአባቱ ከአቶ ቸኮል ረታ እና ከ እናቱ ወ/ሮ የእናት ፋንታ አስረስ በ1950 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ ከተማ ተወለደ። በአምስተኛው ዓመቱ በፈንጣጣ በሽታ ተጠቂ በመሆኑ በተደረገለት ህክምና ሕይወቱን ለማትረፍ ቢቻልም የዓይን ብርሃኑን የማጣት አደጋ በስምንት ዓመት ዕድሜው ደረሰበት። በሰበታ የዓይነ ስውራን ትምህርት ቤት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ተከታትሏል። በተማሪነት ዘመኑ ለመዝሙርና ለሙዚቃ እንዲሁም ለመጽሐፍ የነበረው ፍቅር ከፍተኛ ነበር። በዕድገት በህብረት ዘመቻ በባህር ዳር ከተማ በመምህርነት ተመድቦ ግዴታውን ለመውጣት ችሏል። በ1971 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋዎች ጥናት ኢንስቲቱት በ እንግሊሽ ዲፓርትመንት ገብቶ በ1974 ዓ.ም ከጠቅላላው ተማሪ በላቀ ውጤት የዓመቱ ኮከብ ተማሪ ሆኖ ከወቅቱ የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት እጅ የወርቅ ተሸላሚ በሆን የመጀመሪያውን ዲግሪ አገኘ።

ከዚያም Ethiopian External Service ተብሎ በሚታወቀው መስሪያ ቤት በጋዜጠኝነት ተቀጥሮ በሪድዮ ጣቢያው በየሳምንቱ የሚደረገውን የባህልና የሙዚቃ እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦች የሚጋበዙበት የውይይት ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ በመሆን ያገለገለ ሲሆን ማዘር ትሬዛን በፕሮግራሙ ላይ ለማቅረብ የቻለ፤ በአነባበቡ፣ በፕሮግራሙ ጥልቀት፣ ታማናዊ በሆነ አቀራቡ የብዙ አድማጮችን ቀልብ የሳበ ነበር። በተለያዩ ሃጉሮች የተለያዩ ስልጠናዎችን ያገኘ ሲሆን ከቀይ ጨረቃ አፍሪካ አቀፍ የሬድዮ ፕሮግራም አምስት ጊዜ እውቅና አግኝቷል።

በ1982 ዓ.ም ከባለቤቱ ወ/ሮ በልዩ በላይ ጋር ህጋዊ ጋብቻ በመፈጸም በ1983 ዓ.ም የትምህርት ዕድል በማግኘቱ ወደ ሜኔሶታ በማቅናት የማስትሬት ዲግሪውን ጀምሮ በ1986ና በ1989 ዓ.ም የኮምዩኒከሽንና በፖለቲካል ሳይንስ የማስተርስ ዲግሪውን፣ በ1991 እንዲሁም የዶክትሬት ዲግሪውን (PHD) በመገናኛ ብዙሃን ትምህርት ከዩኒቨሪሲቲ ሚኒሶታ አግኝቷል።

ትምህርቱን ከጨረሰ በኋላ በከፍተኛ ተምህርት ተቋሞች በማስተማር ሥራ ተሰማርቶ በዩኒቨርሲቲ ሚኒሶታ፣ በዊስካንሰን ሪቨል ፎል ዩኒቨርሲቲ፣ በኦሃዮ በሚገኘው አሽላንድ ዩኒቨርስቲቲ፣ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሚቺጋን ከመምህርነት እስከ ተባባሪ ፕሮፌሰርነት አገልግሏል።

ከማስተማሩና ከምርምሩ ተጨማሪ የተለያየ ኮሚቴዎች አባልና ስብሳቢ በመሆን ሙያዊ ግልጋሎት ሰጥቷል። በተጨማሪም በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፊችን በተለያዩ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች አቅርቧል። እንዲሁም ከአካዳሚ ጋር ያልተያያዙ ሁለት መፅፎችን ለአንባብያን አበርክቷል።

The quest for press freedom በኢትዮጵያ የ100 ዓመታት ሜዲያ ታሪክ ላይ ያተኮረ መጽሐፍ አዘጋጅቶ ሰጥቷል። ይህ መጽሐፉ በቅርብ ጊዜ በገበያ ላይ እንደሚውል ሕይወቱ ከማለፉ በፉት ለጓደኞቹና ለዘመድ አዝማድ አብስሯል። እንዲሁም ሁለት ለመጨረስ ያልታደላቸው ያሬድ ገብረሚካኤልና የዛሪኤይቱ ኢትዮጵያ ጽሁፎችን ለ Encyclopedia Aethiopica Vol.5 አዘጋጅቶ እንደነበር ይታወቃል።

ዶክተር መሠረት ከመምህርነትና ከምርምር ሥራዎቹ ባልተናነሰ መልኩ የሚታወቀው በሰባዊ መብት ተሟጋችነቱ፤ ለሃገሩ ባለው ቅናቂ አስተሳሰብና በተለይም ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ በሚሰጠው ትንታኔ ነበር። በዚህ በሚኒሶታ የሚገኘው የኢትዮጵያ ድምጽ ሬድዮ የ እንግሊዘኛ ዜና በማዘጋጀት፤ በአሜሪካ ሬድዮ ጣቢአ የዘወትር ተባባሪ በመሆን፤ በ1995 ምርጫ ዘመን ድምጽ ላጡ ድምጽ በመሆን ጊዜውን፣ ገንዘቡን፣ ዕውቀቱን በመለገስ፣በተለይዩ ከተሞች በተናጋሪነት በመጋበዝ አስተዋጽሆ አድርጓል።
በ2007 በሜሪላንድ ተቀማጭ የሆነ የታዋቂ ግልሰቦችን ታሪክ የሚያጠናቅር ድርጅት በማቁቋምና የድርጅቱም ሊቀመንበር በመሆን አገልግሏል። በሕይወት ዘመኑ ብዙ ልጆችን የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ አድርጓል።

መሠረት በሥራው ላይ የማይኩራራ፣ ይህን አደረኩ ብሎ የማይናገር፣ እራሱን ዝቅ አድርጎ ከማንኛውም ሰው ጋር ተግባብቶ የሚኖር፣ ለ እውነት ራሱን አሳልፎ የሚሰጥ እንደነበር በቅርብ የሚያውቁት ጓደኞቹ ይናገራሉ።

ባለፉት ሁለት ወራት የጉበት ካንሰር በሽተኛ መሆኑን ካወቀ በኋላ ከእራሱ ይቅል ለወገኖቹ በማሰብ ሌሎች ተገቢውን ምርመራ እንዲያከናውኑ ያሳስብ ነበር። ዶ/ር መሠረት ቸኮል በተወለደ 55 ዓመቱ ቅዳሜ ሕዳር ስምንት ቀን 2005 ከጠዋቱ 5am ላይ ህክምና ሲደረግለት በነበረው በፓርክ ኒክለት ሜተዲስት ሆስፒታል ባለቤቱን ወ/ሮ በልዩ በላይን፣ ልጁን ኤደን መሠረትን፣ ቤተሰቡን እና ጓደኞቹን በመለየት ከዚህ ዓለም አልፏል። (ፎቶ: በአሁኑ ወቅት የጋዜጠኝነት ትምህርቷን እየተከታተለች የምትገኘው የዶ/ር መሠረት ቸኮል ልጅ ኤዶን የአባቷን መጽሐፍ ይዛ)

Filed Under: Literature Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule