በድጋሚ ከተመረጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አፍሪካን እየጎበኙ ያሉት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በሴኔጋል ጉብኝት ባደረጉት ወቅት የግብረሰዶማውያን መብት ሊከበር እንደሚገባው አስታወቁ፡፡ የአገራቸው ጠቅላይ ፍርድቤት ሰዶማውያንን የሚደግፍ ውሳኔ ሰሞኑን በማሳለፉ ደስታቸውን ገለጹ፡፡ የሴኔጋሉ አቻቸው ግብረሰዶማውያን እንዳይወነጀሉ ለማድረግ አገራቸው ዝግጁ አለመሆኗን ተናገሩ፡፡ ሰሞኑን በአፍሪካ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ፕሬዚዳንት ኦባማ ጉብኝታቸውን በጀመሩባት ሴኔጋል የግብረሰዶማውያንን መብት በተመለከተ ለአፍሪካውያንና ለመሪዎቻቸው ማብራሪያና “ትምህርት” ሰጥተዋል፡፡ “መንግሥታት ዜጎቻቸውን እንዴት ሊያስተናገዷቸው ይገባል፤ ሕጉስ እንዴት ሊያያቸው ይገባል ለሚለው ጥያቄ መልሱ ሁሉም ሰው በእኩልነት ሊስተናገድ ይገባዋል” በማለት “ግብረሰዶማዊነት ወደፊት” የሚያስብል ንግግር … [Read more...] about ኦባማ – “ዴሞክራሲ ከራባችሁ ኬክ ብሉ”
Archives for June 2013
አንተ ማነህ?
“... እንዲያውም ይህ በሽታ አልበቃ ብሎን ከዚህ በባሰ መልኩ መቀሌ ከተማ ላይ አደዋና መቀሌዎች፣ ባሕርዳር ከተማ ላይ ጎንደሬ፣ ጎጃሜ፣ ወሎዬና ሸዌ፣ናዝሬት ከተማ ላይ የወለጋ፣ የባሌ፣ የአሩሲና የሸዋ ኦሮሞዎች፣ አዋሳ ከተማ ላይ ሀዲያ፣ ከንባታ፣ ወላይታ ሶዶ ወዘተ በማለት የሚታየው የሹመትና የጥቅም ሽኩቻ ዘመነ መሳፍንትን ምስጋና ይግባው የሚያሰኝ ሆኗል (ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል እንዲሉ)፡፡ … “በተቃዋሚው ጎራ የተሰለፉት ፖለቲከኞቻችንም ቢሆኑ የስልጣን እድሉ ቢገጥማቸው ምን ሁኔታ እንደሚፈጠር ለመገመት ነቢይ መሆን አያስፈልግም፡፡ (አብዛኛዎቻችን ከቂም በቀል አዙሪት ገና ያልወጣን በመሆኑ) ይህን ያልኩትም ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ ያሳዩት አሳፋሪ ንትርክና የትዕቢት ባሕሪ በቂ የማንነት መገለጫ ስለሆነ ነው፡፡ … “… (ስለዚህ) ሰው ሆኖ ሰው ያለመሆን ማንነት” አለ ማለት … [Read more...] about አንተ ማነህ?
“ምስጢር ካወጣህ ቤተሰቦችህን እንፈጃቸዋለን”
“የደረሰብኝን ስቃይ ለማንም ብናገር ቤተሰቦቼን በሙሉ እንደሚፈጁ አስጠንቅቀውኛል” ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ በዝዋይ እስር ቤት ለወራት ስቃይ የተፈፀመበት ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ይባላል፤ አርሲ አርባ ጉጉ ተወልዶ አዳማ/ናዝሬት አድጎ፣ በ1998 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሶሲዮሎጂ ተመርቋል፡፡ በ2000 ዓ.ም በባህልና ቱሪዝም ሚ/ር በሲኒየር ካልቸራል ኤክስፐርትነት የስራ መደብ እስከ ሚያዝያ 2003 ሰርቷል፡፡ ሚያዝያ 12 ቀን 2003 ዓ.ም በግልፅ ባልተረዳው ምክንያት የመንግስት ደህንነት ሀይሎች ተያዞ ለ23 ወር በዝዋይ እስር ቤት ከፍተኛ ስቃይ እየተፈፀመበት መቆየቱን ይናገራል፡፡ መጋቢት 26 ቀን 2005 ዓ.ም ከእስራት ሲለቀቅም አንድ ጊዜም እንኳን ፍርድ ቤት እንዳልቀረበ ለፍኖተ ነፃነት አስረድቷል፡፡ ከወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ጋር ያደረግነውን ቆይታ … [Read more...] about “ምስጢር ካወጣህ ቤተሰቦችህን እንፈጃቸዋለን”
አንዲት የኮንትራት ሰራተኛ በጅዳ ቆንስል በር ታንቃ ሞተች
በጅዳ መጠለያ አንዲት የኮንትራት ሰራተኛ በጅዳ ቆንስል በር ታንቃ ሞተች በሪያድ "ኢትዮጵያዊቷ አሰሪዎቿን ለመበቀል የ6 አመት ህጻን ገደለች" የሳውዲ ጋዜጣ ዘገባ ኮንትራት ስራ መጥተው ተፈናቅለው በጅዳ ቆንስል መጠለያ ከሚገኙት ቁጥራቸው ወደ 80 ከሚጠጉት እህቶች መካከል አንዷ እህት ከሁለት ቀናት በፊት እሁድ ጁን 23 ቀን 2013 በጅዳ ቆንስል ግቢ በር ራሷን አንቃ መግደሏ ታውቋል። ጉዳዩን ለማጣራት የዚህችው እህት ሬሳ ከቦታው ሲነሳ በቦታው ነበሩ ወደ ተባሉት በጅዳ ቆንስል የዲያስፖራና ተፈናቃይ ዜጎች ሃላፊ ወደ ሆኑት ቆንሰል ሙንትሃን በስልክ ለማግኘት ያደረግኩት ሙከራ አልተሳካም። ስለተፈጠረው አሳዛኝ ክስተት አካባቢው ከነበሩ የአይን እማኞች ለማጣራት ባደረግኩት ሙከራ ሟች በኮንትራት ስራ ከወሎ ወደ ሳውዲ አረቢያ መጥታ ከአመት በላይ ከሳውዲ አሰሪዎች ቤት ስትሰራ … [Read more...] about አንዲት የኮንትራት ሰራተኛ በጅዳ ቆንስል በር ታንቃ ሞተች
ምነዋ ! ማንዴላችን ? !
ምነዋ ! ማንዴላችን ? ! ድምጽህ ቁርጥ ቁርጥ አለ አመመህ ምነው ደከመህ በማረፊያህ ? አፍሪካን ከአንባገንን ልጆቿ ጸድታ ሳታይ ምነዋ መድከም ማሸለብህ ? የኢትዮጵያን ስርየት ሳይበሰር ምነዋ የመለየት ጉዞን መጀመርህ ኢትዮጵያ ከደዌ ተላቃ ሳትጎበኛት ምነዋ አትቀስቅሱኝ አልክ አንቀላፋህ ? ምነዋ መልአከ ሞት ከበበህ የስንብት መርዶ ጽልማሞት ግርማውን አለበሰህ ምነዋ ጠንካራውን ጉልበትክን ፈተነብህ የእማማን አፍሪካን ድህነት ማየቱ ታከተህ ! ምነዋ ማንዴላ?. . . (ይህ ከግጥሙ ተቀንጭቦ የተወሰደ ሲሆን ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) ነቢዩ ሲራክ … [Read more...] about ምነዋ ! ማንዴላችን ? !
ኦባንግ ከቴላቪቭ ባለስልጣናት ጋር ይመክራሉ
እስራኤል ኢትዮጵያ ውስጥ በህዝብ ፍላጎት የሚመረጥ የተረጋጋ መንግስት እንዲቆም ከመቼውም ጊዜ በላይ የምትንቀሳቀስበት ወቅት ላይ መሆኗን ለማሳሰብ በነገው እለት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር እንደሚመክሩ አቶ ኦባንግ ሜቶ አስታወቁ። የሒብሩ ዩኒቨርስቲ ምሁራንና ማህበረሰብ ለአቶ ኦባንግ መልክት ድጋፍ እንዲያደርጉ የሚጠይቅ ንግግር ያደርጋሉ። በእስራኤል የሚኖሩ ስደተኛ ወገኖችን አስመልክቶ ቃል እንደተገባላቸውም አመልክተዋል። አቶ ሳሙኤል አለባቸው “መኖርና መሞት ስላለ ወደ ህሊናችን ልንመለስ ይገባል" አሉ። የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር የአሜሪካ እንደራሴ (ኮንግረንስማን) ክሪስ ስሚዝ በመሩት የምክክር ሸንጎ ላይ ንግግርና ማብራሪያ ካሰሙ በኋላ ወዲያውኑ በቀጥታ ወደ እስራኤል አምርተው ነበር። ለሁለት ጉዳዮች ወደ እስራኤል ያመሩት አቶ ኦባንግ የኢትዮጵያን … [Read more...] about ኦባንግ ከቴላቪቭ ባለስልጣናት ጋር ይመክራሉ
Africa Institute of South Africa (AISA)
In celebration of the 50th Anniversary of the Organization of African Unity (OAU), the precursor to the African Union, the Africa Institute of South Africa (AISA), the premier South African Science Council that specialises in African Studies presents its flagship publications on African Affairs. (For the list of publications, please click here) … [Read more...] about Africa Institute of South Africa (AISA)
ከአውሮፓ ፌዴሬሽን የተሰጠ መግለጫ
በአውሮፓ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን መግለጫ አውጥቷል፤ ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ … [Read more...] about ከአውሮፓ ፌዴሬሽን የተሰጠ መግለጫ
“አሜሪካ አቋማን የምትፈትሽበት ወቅት ላይ ናት” ክሪስ ስሚዝ
ኢህአዴግ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ስም ከአሜሪካ ጋር የመሰረተውን ግንኙነት አስታክኮ የሚፈጽመው ኢሰብዓዊ ድርጊት ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት የሌለው እንደሆነ ተገለጸ። አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምትከተለውን ፖሊሲ የምትመረምርበት ወቅት ላይ ትገኛለች ተባለ። ኢህአዴግ ጸረሽብርተኝነትን ለአፈናና ለበጀት ማሟያ እየተጠቀመበት እንደማይቀጥል ተመለከተ። አሜሪካና ሌሎች ለሰብአዊ መብት መከበር ዋጋ የሚሰጡ አገሮች በሙሉ በ"አዲስ አበባው" አገዛዝ ላይ ጠንካራ አቋም መያዛቸውን ያለ አንዳች ማወላወል ማሳየት እንደሚገባቸው እንደራሴ (ኮንግረስማን) ክሪስ ስሚዝ ያስታወቁት ሽብርተኛነትን አስመልክቶ ጠንካራ ማሳሰቢያ በማስቀመጥ ነው። እንደራሴ ስሚዝ የኢትዮጵያ ጉዳይ የተደመጠበትን የምክክር ሸንጎ ከዘጉ በኋላ በተለይ ለጀርመን ድምጽ ሬዲዮ በሰጡት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት "አሜሪካ በኢህአዴግ ላይ … [Read more...] about “አሜሪካ አቋማን የምትፈትሽበት ወቅት ላይ ናት” ክሪስ ስሚዝ
እኔ አማልሰጣችሁ ፣ እናንተ እማትወስዱት….
ያለስም፣ ስም - ስጡኝ ቅጡኝ፣ አስቀጡኝ፤ አግዙኝ፣ ወርውሩኝ፣ ... በማጎሪያችሁ እሰሩት… እጀን፣ … በካቴናችሁ ‘ጠንዙት’ እግሬን፣ …. በእግር ብረታችሁ ቸንክሩት፣ ገንዙት፣ ... ይደንዝዝላችሁ ሽባ ሆኘ ልቅር፣ ‘’ልሰንከልላችሁ’’:: ... እንካችሁ …. ጀርባዬን መጫሚያ፣ መዳፌን፤ ግረፉት፣ አቃጥሉት፣ …. በኮረንቲ ገመድ የሰራ አከላቴ፣ ይክሰል፣ ይሁን ዓመድ:: … ዝረፉት … ሀብቴን ቤትና ንብረቴን፣ በምድር ያለኝን፤ ሰብስቡ፣ አከማቹት፣ ለዓለም ይሁናችሁ ለማይጠረቃው፣ ለከርስ ዓላማችሁ ለማፍረስ፣ ለመናድ፣ ለጥፋት ግባችሁ:: … እንካችሁ…… ደረቴን እንካችሁ…… ግ’ባሬን፤ ለታንክ፣ ለመትረጊስ፣ ለጥይታችሁ አፍስሱት ደሜን፣……. እስኪከረፋችሁ አድቅቁት አጥንቴን፣……. … [Read more...] about እኔ አማልሰጣችሁ ፣ እናንተ እማትወስዱት….