በቅርቡ በሚከበረው 50ኛው ዓመት የአፍሪካ ኅብረት ክብረበዓል ላይ በተጋባዥነት ለሚገኙት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር ኦባንግ ሜቶ በፋክስ የሚደርስ ቀጥታ ደብዳቤ ላኩ፡፡ በደብዳቤው ላይ አቶ ኦባንግ ሰሞኑን በአፍሪካ ህብረት አካባቢ ለተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ድርጅታቸው ድጋፍ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡ በበርካታ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ለሚ/ር ኬሪ በደብዳቤያቸው ላይ ማሳሰቢያ የሰጡት ኦባንግ የአፍሪካ ኅብረት ሲቋቋም ቅኝ አገዛዝን መታገል፣ የህግ የበላይነትን ማስከበርና የዜጎችን መብት ማስጠበቅ ዋንኛ ዓላማው የነበረ ቢሆንም የያኔዎቹ መስራች መሪዎች አሁን በህይወት ቢኖሩና የዛሬዪቱን አፍሪካ ቢመለከቱ ምን ይሉ ይሆን በማለት ጠይቀዋል፡፡ በመላ አፍሪካ በዘመናችን ያለውን የሰብዓዊ መብት መጣስ፣ የሙስና መስፋፋት፣ … [Read more...] about ኦባንግ ለኬሪ የጥሪ ደብዳቤ ላኩ!
Archives for May 2013
በጥቁር ገበያ የዶላር ዋጋ በሰላሳ ሳንቲም መቀነሱ አነጋጋሪ እየሆነ ነው
በአዲስ አበባ የሚገኙ የጥቁር ገበያ ባለድርሻዎች በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ታዋቂ ነጋዴዎች ከሙስና ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በመታሰራቸው በተፈጠረ መደናገጥ መነሻ ከፍተኛ የሆነ ኪሳራ እያጋጠማቸው መሆኑን ገልፀው፣ የዶላር ምንዛሪ በታሪኩ የሰላሳ ሳንቲም ቅናሽ አሳይቷል። የከፍተኛ ባለስልጣናቱ በወንጀል የመጠርጠር ዜና ከመሰማቱ በፊት ሃያ ብር ከአርባ ሳንቲም የነበረው የዶላር ምንዛሪ ወደ ሃያ ብር ከአስር ሳንቲም በሳምንት ውስጥ ቀንሷል። በዚህ ቅናሽ ውስጥ አስደንጋጭ የሆነው ክስተት በማንኛውም አይነት ምንዛሪ መጠን ዶላር ወደላይ ሲጨምር ሆነ ሲቀንስ በሰላሳ ሳንቲም የልዩነት ምንዛሪ ውስጥ ወድቆ አለማወቁ መሆኑን ከስፍራው ያገኘነው መረጃዎች ያሳያሉ። በሙስና ከተጠረጠሩ ባለስልጣናት እና ነጋዴዎች ጋር በተያያዘ ይህ ልዩነት መፈጠሩ አብዛኛው የጥቁር ገበያ የዶላር ምንዛሪ … [Read more...] about በጥቁር ገበያ የዶላር ዋጋ በሰላሳ ሳንቲም መቀነሱ አነጋጋሪ እየሆነ ነው
Bahr Dar and the wonderful art of silence
Last Sunday May 12 a Federal police officer opened fire and murdered twelve or eighteen people depending on who is doing the counting in the City of Bahr Dar by the shores of Lake Tana. It was a random killing and the only reason he stooped shooting was because he run out of bullets. What makes this crime unique is that it was committed by some one that is trained to protect and serve. At least in most places that is what we think of the armed officers that move around with loaded guns amongst … [Read more...] about Bahr Dar and the wonderful art of silence
የለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤ/ክ ጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤ የአቋም መግለጫ
የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤ የአቋም መግለጫ ግንቦት ፲፩/ ፪ሺ፭ (19th May 2013) የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤ፤ ከእዚህ በፊት የቤተ ክርስቲያኗን አስተዳደር አቋም፣ የውስጥ መተዳደሪያ ደንብና ትረስት ዲድ በሚመለከት ያሳለፋቸው ውሳኔዎችና መግለጫዎች ሙሉ በሙሉ እንደተጠበቁ ሆነው፤ የቤተ ክርስቲያናችንን ችግር ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የተከሰቱ፣ የተሳሳቱ መረጃዎችንና መግለጫዎችን ለማስተካከል፤ ጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤው የሚከተለውን የአቋም መግለጫና ማብራሪያ አውጥቷል። 1) የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን … [Read more...] about የለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤ/ክ ጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤ የአቋም መግለጫ
ወ/ሮ ትዕግስት ከታገቱበት ሲና ተለቀቁ!!
የሱዳን፣ የኤርትራና የግብጽ ዜግነት ባላቸው ራሻይዳዎች ታፍነው ወደ ሲና በረሃ የተወሰዱት ወ/ሮ ትዕግስት ገብሬ ካይሮ መግባታቸው ታወቀ። ወ/ሮ ትዕግስት ቅዳሜ ረፋዱ ላይ ካይሮ የገቡት አጋቾቹ እንዲሰጣቸው ከጠየቁት 25 ሺህ ዶላር በድርድር 15 ሺህ ዶላር ተከፍሏቸው ነው። ዜናውን በሰሙ ማግስት “የወ/ሮ ትግስት የርዳታ እጆች” በማለት ተሰባስበው የነፍስ አድን ዘመቻውን ከጀመሩት መካከል አንዷ የሆኑት ወ/ሮ ሰብለ ደምሴ በተለይ ለጎልጉል እንደተናገሩት ወ/ሮ ትዕግስት ከአሰቃቂው የሲና በረሃ ወጥተው ካይሮ የገቡት ከአራት ወራት በኋላ ነው። አጋቾቹ ወ/ሮ ትዕግስትን በ10 ሺህ ዶላር እንደገዙ በመግለጽ 25 ሺህ ብር ካልተከፈላቸው እንደማይለቁና የሰውነት ክፍላቸውን በመሸጥ ያወጡትን ወጪ እንደሚሸፍኑ ይደራደሩ እንደነበር የገለጹት ወ/ሮ ገነት “አስቀድመን 10 ሺህ ዶላር ከፈልን። … [Read more...] about ወ/ሮ ትዕግስት ከታገቱበት ሲና ተለቀቁ!!
አወይ አማሪካን …
ቢሄዱት... ቢሄዱት... ቢሄዱት... ቢሄዱት... አያልቅ ሽቅቦሹ፥ አይቆም ቆልቁሎሹ መንገድ እየሄዱ መንገድ እየበሉ መንገዱ እየጠጡ አያልቅም ቢሄዱት፥ አያልቅም ቢጠግቡት፤ አወይ አማሪካን... አወይ የሰው አገር የበላን ያላየ፥ የዋጠን ያልሰማ አወይ አማሪካን፥ ሰው በላብ ያደማ፤ ቢሄዱት ቢሄዱት፥ እረፍትን ማን አውቆት እዚማ ከሆኑ… እንቅልፍ ለምኔን፥ ለብሶ ነዪ መኛት፤ አወይ አማሪካን፥ አገረ ማራቶን አገረ እሩጫ ለማምለጥ መፏደድ፥ ቢል ከሚሉ ጡጫ መኖር አለመኖር፥ ካንድ ራስ ፍጥጫ፤ አወይ አማሪካን... ቢሄዱት... ቢሄዱት... ቢሄዱት አያልቅ መንገድ እንደ ጅማት የሚላግበት አወይ አማሪካን ሕልም ያጠጠበት እንቅልፍ ለምኔን የሚያነቡበት_ እንቅልፍ ለምኔን የሚገምጡበት_ እንቅልፍ … [Read more...] about አወይ አማሪካን …
Tower in the sky (የሰማይ ላይ ግንብ)
የመፅሐፉ ርዕስ፡- Tower in the Sky (የሰማይ ላይ ግንብ) ደራሲ፡- ህይወት ተፈራ አሳታሚ፡- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ የገፅ ብዛት፡- 437 የታተመበት ዘመን፡- እ.አ.አ. 2012 የመሸጫ ዋጋ፡- 74ብር በሰለሞን ኃይለማርያም ይህንን መፅሐፍ ሳነብ በልጅነቴ በአንድ ዕለት ሰንበት እናቴ እጄን ይዛ ወደ ቤ/ክርስቲያን ስትወስደኝ የተመለከትኩትን ልክ እንደፊልም ወደኋላ ወስዶ እንዳስታውስ አደረገኝ፡፡ (ሙሉውን ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል) … [Read more...] about Tower in the sky (የሰማይ ላይ ግንብ)
ሀቁን መናገር ወይስ ሀቁን ለመፈለግ መጣር!
በጽሁፉ የተዳሰሱ ርዕሶች (ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል) ሀቁን መናገር ወይስ ሀቁን ለመፈለግ መጣር ! ክፍል ፩ ሀቁን መናገር ወይስ ሀቁን ለመፈለግ መጣር! ጥያቄ የመጠየቅና የአሰራር ስልት ጉዳይ! ሶስት የጥያቄ አቀራረብና የምርመራ አጻጻፍ መንገዶች! የወያኔን ባህርይና የተፈጠረበትን ህብረተሰብ የመረዳት ችግር! ወያኔና የምዕራቡ ዓለም በተለይም የአሜሪካን ፖለቲካ! ዋናው ችግራችን ! ሃቁን መፈለግና መናገር ያለመቻል ! ሀቁን መፈለግ ወይስ ሀቁን መናገር-ከአምልኮ አስተሳሰብ ወደ አርቆ-አሳቢነትና ወደ ሳይንሳዊ አመለካከት ክፍል ፪ ዕውነትን ወይም ሀቅን መፈለግ ማለት ምን ማለት ነው? የአፍሪቃ ምሁራን ችግር- ዕውነትን በመፈለግና በዕውነተኛው ዕውቀት መሀከል ያለውን መተሳሰር ያለመረዳት ! ዕውነትን መፈለግና የባህል ጉዳይ! ዕውነት … [Read more...] about ሀቁን መናገር ወይስ ሀቁን ለመፈለግ መጣር!
የ“ቀዩ መስመር” ሰላባዎች?
መለስ ህይወታቸው እንዳለፈ ከተሰጡት አስተያየቶችና ትንቢቶች መካከል ቀዳሚው የመለስ ሞት ለህወሃት ጊዜውን ጠብቆ የሚፈነዳ ፈንጂ መሆኑ ነበር። በዚሁ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በስልጣን ላይ ያሉ የኢህአዴግ ዲፕሎማት "መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ" በሚል ርዕስ በሰጡት ቃለ ምልልስ ይህ እንደሚከሰት ቁልጭ አድርገው ተናግረው ነበር። መለስ አፍነው የያዟቸው የፖለቲካ ችግሮች ጊዜያቸውን እየጠበቁ የሚፈነዱና በመጨረሻም ፓርቲውን እንደሚፈረካክሰው የተገለጸው በየደረጃ የሚፈነዱት ችግሮች እየበረከቱ በመሄዳቸው ነበር። መለስ አፍነው የያዟቸው ችግሮች የእርስ በርስ መበላላት ደረጃ እንደሚያደርሱ በርካታ ወገኖችና መገናኛዎች ጎልጉልን ጨምሮ አመላክተዋል። አሁን አሁን ትንቢቱ የፍጻሜው ጅማሬ ላይ እንደሚገኝ የሚናገሩም አሉ። የፖለቲካ አቋም ልዩነት ሳይኖር የአስተሳሰብ ልዩነት ማራመድ በህወሃት ዘንድ … [Read more...] about የ“ቀዩ መስመር” ሰላባዎች?
“መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ…”
ይህንን ቃለምልልስ ያደረግነው ለበርካታ ዓመታት ለኢህአዴግ ሲሰራ ከነበረና በአሁኑ ወቅት ለከፍተኛ ትምህርት ውጪ አገር ከሚገኝ ኢትዮጵያዊ ጋር ነው፡፡ ለደኅንነት ሲባል ስሙን ከመጥቀስ ተቆጥበናል፡፡ ጎልጉል ፦ የጠ/ሚኒስትር መለስ መታመም ድንገተኛ ነው የሚሉ አሉ፤ አሟሟታቸውም ድንገት ነው የሚሉ አሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ አጋጣሚው መልካም እንደሆነ የሚጠቁሙ አሉ አንተ ከየትኛው ወገን ነህ? መልስ፦ ቅድሚያ አቶ መለስ ድንገት አልታመሙም። በሽታቸው የቆየ እንደሆነ ይታወቃል። ምስጢርም አይደለም። ለዚሁ እኮ ነው ቤተ መንግስት ውስጥ በአዋጅ የተፈቀደላቸውን ቤት አሰርተው በቅርብ ርቀት እየተቆጣጠሩ ለመኖር ቅድመ ዝግጅት ሲያደርጉ የነበረው። በዚህ ቢስተካከል ለማለት ነው። መለስ ለኢህአዴግ አጋር ድርጅቶች ሁሉ የጋራ ነጠብ ናቸው። በድልድይም ይመሰላሉ። በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች፣ በተለይም … [Read more...] about “መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ…”