ነገሩ ሁሉ ከድጡ ወደማጡ በሆነባት ሀገራችን በየጊዜው የሚፈራረቁት ሰቆቃዎች ልብን በሀዘን ካራ ማድማታቸውን እንደቀጠሉ ነው። ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ ከደረሱብን መዓቶች ጥቂቱን ብናነሳ፤ በረኃብ አለንጋ እየተገረፉ ደጃፋቸው ላይ ድፍት ብለው የቀሩትን፣ መብታቸውን ለመጠየቅ ሲጮሁ የጥይት ራት የሆኑትን፣ የኢሬቻን በዓል ለማክበር አምረው ደምቀው እንደወጡ ገደል ሰብስቦ ያስቀራቸውን፣ እንዲሁም በቅርቡ በቆሻሻ ናዳ ታፍነው እስከወዲያኛው ያንቀላፉትን ወገኖቻችንን በቁጭትና በመሪር ሀዘን እናስባለን። እነዚህን አደጋዎች ይበልጥ አሳዛኝና አስከፊ የሚያደርጋቸው ደግሞ በሀገሪቱ የተንሰራፉት አምባገነንነት፣ ዘረኝነት፣ ምዝበራ፣ ራስወዳድነትና ግድየለሽነት ውጤት መሆናቸው ነው። በአስራዎች በመቶ እድገት ሽምጥ ስለሚጋልበው ኢኮኖሚዋ ነጋ ጠባ የሚዘመርላት የወያኔዋ ኢትዮጵያ ዘራፊዎቿ ከቪላ ቪላ … [Read more...] about ከቆሻሻ ኑሮና ሞት ለመላቀቅ ቆሻሻውን ስርዐት ማስወገድ
Opinions
የኔ ሃሳብ
አደራዳሪ የሌለው ድርድር፥ ሐኪም የሌለው ሆስፒታል ነው
አገራችን ባለፈው ዓመት ካለፈችበት ህዝባዊ ተቃውሞዎች አንፃር ኢሕአዴግ ከህጋዊ አገራዊ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ድርድር ማድረግ እንደሚፈልግ መግለፁ ለብዙዎቻችን ትንሽ የተስፋ ጭላንጭል ነበር። ሆኖም በቅድመ ድርድር ሂደቱ ወቅት ኢሕአዴግ ያሳየው አካሄድ ሚጠቁመው ከድርጅቱ አመራር ውስጥ አንዳንዶቹ አገራችን ያለችበትን አደገኛ ሁኔታና ሂደት በአግባቡ ያላጤኑ ፥ አደጋውን አለባብሰው ማለፍ የመረጡ ፥ ብቃትና አቅም የሌላቸው ፅንፈኛ ጥቂቶች የድርድር ተስፋውን እያጨለሙት መሆኑን ነው። ኢሕአዴግ ከደርግና ከአፄው ስርዓት ያልተማረው ዋና ቁምነገር ሁሉን ተቆጣጥሮ ሁልጊዜ እያለባበሱ ማለፍ እንደማይቻል ነው። እስከ መጨረሻው ሰጥቶ መቀበልን ያልፈለገው ደርግ ዛሬ የታሪክ አመድ ሆኗል። በፍጥነት ተሃድሶ ማድረግ ያልፈለገው የአፄው ስርዓት ዛሬ የሚገኘው በጥቂት አረጋውያን ትዝታ ውስጥ ብቻ … [Read more...] about አደራዳሪ የሌለው ድርድር፥ ሐኪም የሌለው ሆስፒታል ነው
ከሩስያ በአሜሪካ የፖለቲካ ሂደት ጣልቃ ገብነት ምን እናነባለን?
አሜሪካ ለሩስያ የፖለቲካ ተቀናቃኝ ናት። የአሜሪካ ርዕዮተ ዓለም ከሩስያ ርዕዮተ ዓለም የተለየ ነው። በአሜሪካ፤ ከሀገሪቱ የግለሰብ የሃሳብ የነፃነት የተነሳ፤ ከሀገራቸው ይልቅ ራሳቸውን የሚያስቀድሙ ሰዎችም በመንግሥት መዋቅርም ይሁን በንድግ ተግባሩ ውስጥ በኃላፊነት የሚገኙ አሉ። ይህ የግል አመለካከታቸው፣ የራሳቸው ከመሆኑም በላይ፤ በማንም ግለሰብ፤ የበላይ አለቃቸውም ሆነ ለነሱ ተጠያቂ በሆኑ ግለሰቦች ዘንድ፤ አያስገምታቸውም። በአንጻሩ፤ እንደሩስይ ባሉ የአምባገነኖችን የበላይነት በሚያመቻቹና በሚያሞግሱ ሀገራት፤ (ይህ አብዛኛውን በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን ያጠቃልላል። የኢትዮጵያውን የትግሬዎች ወገንተኛ ወራሪ ቡድንንም ይጨምራል።) ነዋሪዎቹ፤ ግለስብ ግለሰብነቱን አጥቶ፤ በገዥዎቹ ፍላጎት የሚተረጎም ማንነትን እንዲቀበሉ ስለሚገደዱ፤ የገዥዎቻቸው አገልጋዮች ናቸው ማለት ይቻላል። … [Read more...] about ከሩስያ በአሜሪካ የፖለቲካ ሂደት ጣልቃ ገብነት ምን እናነባለን?
የኢትዮጵያ ጉዳይ መጽሔት
መጋቢት 2009 ዓ.ም ሦስተኛ ዓመት ቁጥር ፪ ዕትም የወያኔ አገዛዝና የካድሬዎቹ አስከፊ ተግባሮች ተገሎ የማያልቀው የአማራ ሕዝብ ስቃይና መከራ የዚህ ዘመን ኢትዮጵያዊነት የጎሳ ፖለቲካና መዘዙ በኢትዮጵያ ትርፍ የሌለው ልፋት ዴሞክራሲ የውሃ ሽታ የሆነባት አገር አመፅ በተግባር ሲተረጎም ሕገ-መንግሥቱ የተፃፈው ለማን ነው? ወዘተ ርዕሰጉዳዮችን በአማርኛና በእንግሊዝኛ በማካተት ታትሟል፤ መጽሔቱን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። … [Read more...] about የኢትዮጵያ ጉዳይ መጽሔት
SILENCE IN THE FACE OF EVIL IS ITSELF EVIL
"Silence in the face of evil is itself evil. God will not hold us guiltless. Not to speak is to speak. Not to act is to act." The quote is taken from Dietrich Bonhoeffer, a German Lutheran Pastor who participated in the resistance against Nazism;he was clearly saying do not sit back and tolerate evil. We believe the quote is timely for all Ethiopians facing government-sponsored terrorism,especially during the current martial law. It has been six months since Ethiopians have been subjected to … [Read more...] about SILENCE IN THE FACE OF EVIL IS ITSELF EVIL
African Journal of Science, Technology, Innovation and Development (AJSTID)
Call for Papers: Mathematical Modelling: Concepts and Applications for Sustainable Development Deadline: 15 August, 2017 Background The challenge in mathematical modelling is “. . . not to produce the most comprehensive descriptive model but to produce the simplest possible model that incorporates the major features of the phenomenon of interest.” -Howard Emmons Mathematical modelling essentially involves utilizing mathematical principles and concepts to describe real world phenomena. The … [Read more...] about African Journal of Science, Technology, Innovation and Development (AJSTID)
80ኛው ዓመት የየካቲት 12 የሰማእታት ቀን ዝክረ-በዓል
ጋዜጣዊ መግለጫ በ1929 ዓ/ም ፋሺሽት ኢጣልያ 30000 ኢትዮጵያውያንን በአዲስ አበባ ከተማ በሶስት ቀኖች ውስጥ የጨፈጨፈችበት 80ኛ የየካቲት 12 ቀን ዝክረ-በዓል በዓለም-አቀፍ ደረጃ ተከብሯል። እስካሁን ለድርጅታችን በደረሰው ዜና መሠረት፤ በዓሉ በአዲስ አበባ፤ በዳላስ፤ በአትላንታ፤ በማያሚ፤ በኒውዮርክ፤ በዋሺንግተን ዲ.ሲ.፤ በሮም፤ በኮሎኝ፤ በአውሮራ፤ በቫንኩቨር፤ በቶሮንቶ፤ በሲያትል፤ በፕሪቶሪያና በስቶክሆልም ተከብሯል። የአከባበሩም ዘዴ በአብዛኛው በጸሎት ሲሆን፤ እንደ ዳላስ፤ ኒውዮርክ፤ ፕሪቶሪያና ሮም ባሉ ከተሞች በጉባኤ፤ እንዲሁም በዋሺንግተን ዲ.ሲ. በሰላማዊ ሰልፍ ተከናውኗል። ካጋጠሙት እጅግ የሚያበረታቱ ክስተቶች ውስጥ፤ ከፍ ያለ ምሥጋና የሚገባቸው የመገናኛ ብዙኃን ስለ ሰማእታቱ ቀን ሰፊ ግንዛቤ እንዲገኝ ያበረከቱት አስተዋጽኦ ነው። እነዚህም ቪ.ኦ.ኤ. … [Read more...] about 80ኛው ዓመት የየካቲት 12 የሰማእታት ቀን ዝክረ-በዓል
የዳዊት ጠጠር!
ሰዉ በሀገሩ እንደ ዜጋ እኩል ተወዳድሮ ለመኖር ከአንድ ብሔር መወለድ ወይንም በጥብቅ መዛመድ የቅድሚያ መመዘኛ ሲሆንበት፤ ወዶ ያላመጣዉ፣ ፈቅዶ ያልተዛመደዉ ብሄሩ የተፈጥሮ ዉበቱ ሳይሆን እርግማን ሲሆንበት፤ ተምሮ ማወቅ አዉቆ መጠየቁ፣ ለሀገሩ መቆርቆሩ በቅን ሳይታይለት ቀርቶ መጨረሻዉ እድለኛ ከሆነ ማዕከላዊ አለያም ቅሊንጦ መግባትና ሰዉሰራሽ ሲኦልን ማየት ማሳረግያዉ ሲሆን በለስ ያልቀናዉ ደግሞ በዚች ምድር የመኖርያ ቀኑ በአንባገነኑ ስርዓት ሲወሰንለት፤ አፈር ገፍቶ ለፍቶ ግሮ ጥሮ ሳይማር ያስተማረዉን ማህበረሰብ በዉቀቱ ለማገልገል በአምስት ለአንድ መጠርነፍ ግዴታ ሲሆንበት፤ በተወለደበት ሀገር እንደ ሁለተኛ ዜጋ መታየት፣ በገዛ ሃገሩ ባዕድ መሆንን፣ ተወዳድሮ ማሸነፍ ሳይቻል ሲቀር ስደትን አማራጭ የሌለዉ መፍትሄ አድርጎ ለመዉሰድ ይገደዳል ይሰደዳልም፡፡ እውነተኛ መግቢያ ባታገኝም … [Read more...] about የዳዊት ጠጠር!
በአድዋ ጦርነት ኤርትራውያን ለምን ከጣልያን ጎን ተሰለፉ?
አጼ ዮሓንስ ብቻ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ኤርትራውያንን ጨፍጭፈው ነበር- የታሪክ ማስረጃዎች የዘንድሮው የአድዋ በዓል አከባበር ከፍተኛ ጽንፍ የታየበት ነበር። ከፊሉ በዓሉን በድምቀት ሲያከብር ከፊሉ ደግሞ ሲያወግዝ ውሏል። የተለያዩ አመለካከቶች በማህበራዊ ሚድያዊ ቢታዩም፣ የዘንድሮው የአድዋ በዓል አከባበር ለየት ያለና በርካታ ውይይቶች የተካሄዱበት ነበር። በተለያዩ ወገኖች ሲነሳ የነበረው አንዱ ነጥብ "የኤርትራውያን ከጣልያን ሰራዊት ጎን በተለይም ከጀነራል አልበርቶኒ ጦር ጋር አብሮ ኢትዮጵያን መውጋት” የሚለው ምክንያት የጎደለው ሀሳብ ነበር። እርግጥ ነው ኤርትራውያን ከጣልያን ሰራዊት ጋር አብረው ነበር። ግን ለምን? መልሱ የህልውና ጥያቄ የመኖርና ያለመኖር ጥያቄ ስለነበር ነበር። እንዲህ ላብራራው የኣጼ ዮሓንስና የራስ አሉላ ግፍ (genocide) በኤርትራውያን ላይ በቀድሞ … [Read more...] about በአድዋ ጦርነት ኤርትራውያን ለምን ከጣልያን ጎን ተሰለፉ?
ሰው ገድለው አንገታቸው ሊቀላና ሊያሳዝኑን የነበሩት በነጻ ተለቅቁ!
ሟች - ሊደፍራቸው የመጣ ሳውዲ ወጣት ገዳይ - ሚስትና ቤቱን የተከላከለ ጎልማሳ ፍርድ ሰጭ - ከፍተኛው የሸሪአ ፍርድ ቤት የወንጀል ችሎት እነ ሁሴን እንደገና አልተወለዱ ይሆን? ልክ የዛሬ 3 ዓመት ገደማ ሳውዲ አረቢያ ጅዳ "ሀበሾች ሳውዲ ገደሉ!" ተባለ፣ መረጃውን የሰማሁት እኔም በእስር ላይ እያለሁ ነበር። እንዴት ገደሉ ብየ ስጠይቅ ቤታቸውን ሊዘርፉና የሀበሻውን አባወራ ቤት ሊዘርፉ የገቡ ሳውዲ ወጣቶች ሴቶችን ሊደፍሩ በተነሳ አምባጓሮ መሆኑን በደፈናው ሰማሁ። ከዚያም የቀረውን ተባራሪ የእስር ቤት መረጃ የማጣራበት መንገዱ ዝግ በሆነበት የጨለማ ወቅት ገደሉ የተባሉት ወደሚታጎሩበትና እኔ ወዳለሁበት ወህኒ እስኪመጡ የታሳሪውን ተባራሪ የማያጠግብ መረጃ ሳነፈንፍና ስኮመኩም ከረምኩ። ከሶስት ወር በኋላ እኔ ከወህኒ እስክወጣ ወደ ማዕከላዊው የብሪማን እስር ቤት … [Read more...] about ሰው ገድለው አንገታቸው ሊቀላና ሊያሳዝኑን የነበሩት በነጻ ተለቅቁ!










