• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አደራዳሪ የሌለው ድርድር፥ ሐኪም የሌለው ሆስፒታል ነው

April 1, 2017 01:01 am by Editor 2 Comments

አገራችን ባለፈው ዓመት ካለፈችበት ህዝባዊ ተቃውሞዎች አንፃር ኢሕአዴግ ከህጋዊ አገራዊ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ድርድር ማድረግ እንደሚፈልግ መግለፁ ለብዙዎቻችን ትንሽ የተስፋ ጭላንጭል ነበር።

ሆኖም በቅድመ ድርድር ሂደቱ ወቅት ኢሕአዴግ ያሳየው አካሄድ ሚጠቁመው ከድርጅቱ አመራር ውስጥ አንዳንዶቹ አገራችን ያለችበትን አደገኛ ሁኔታና ሂደት በአግባቡ ያላጤኑ ፥ አደጋውን አለባብሰው ማለፍ የመረጡ ፥ ብቃትና አቅም የሌላቸው ፅንፈኛ ጥቂቶች የድርድር ተስፋውን እያጨለሙት መሆኑን ነው።

ኢሕአዴግ ከደርግና ከአፄው ስርዓት ያልተማረው ዋና ቁምነገር ሁሉን ተቆጣጥሮ ሁልጊዜ እያለባበሱ ማለፍ እንደማይቻል ነው። እስከ መጨረሻው ሰጥቶ መቀበልን ያልፈለገው ደርግ ዛሬ የታሪክ አመድ ሆኗል። በፍጥነት ተሃድሶ ማድረግ ያልፈለገው የአፄው ስርዓት ዛሬ የሚገኘው በጥቂት አረጋውያን ትዝታ ውስጥ ብቻ ነው።

ኢሕአዴግና አባላቶቹ ሊያስተውሉት ሚገባው፥ በአገሪቱ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ምልክት እንጂ መንስዔ እንዳልሆነ ነው። እሳት ላይ የተጣደ የጀበና ውሃ እሳቱ እስካለ ድረስ መፍላቱንና መንተክተኩን ይቀጥላል።

ገዢው ፓርቲ በተፈበረኩ የስራ ዕድል ቁጥሮች ፕሮፓጋንዳ፥ በጅምላ እስራትና በ”አይደገምም” የአስገድዶ ቃልኪዳን ማስገባት ከስሩ የተቀጣጠለውን እሳት በቋሚነት ማስቆም አይችልም። እሳቱ እሳካለ ድረስ ውሃው ደጋግሞ ይገነፍላል።

ለዚህ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ግልፅ፣ አሳታፊ፣ ሚዛናዊና በገለልተኛ አካላት የሚመራ ድርድር ማድረግ ብቻ ነው።

ገዢው ፓርቲ ድርድሩ ያለአደራዳሪ ይደረግ ማለቱ የሚያሳየው አንዳንድ የኢሕአዴግ አመራሮች ድርድሩን እንደለመዱት ለፓለቲካ ፍጆታ ለመጠቀም ማሰባቸውን ከመሆኑም በላይ ባለፉት 25 ዓመታት የታየውን የኢሕአዴግን ‘የኔ መንገድ ብቻ’ አፍራሽና ፀረ-ዴሞክራሲያዊ አካሄድ ነው።

ይህ የኢሕአዴግ አንዳንድ ፅንፈኛ መሪዎች አኪያሄድ በፓለቲካ ድርጅት ያልታቀፉ፣ ለአገር የሚያስቡ ቅንና የመደራደር ዋጋና ትርጉም የተገነዘቡ ዜጎች ኢትዮጵያ የሏትም ከሚል አስተሳሰብ የተነሳ ሲሆን ይህ አስተሳሰብ በህዝብ ላይ አመኔታን ካለመጣልና ህዝብን ከመናቅ የመነጨ ነው።

አደራዳሪ የሌለው ድርድር ማለት ሐኪም የሌለው ሆስፒታል ማለት ነው። ውጤቱ ኪሳራ ነው። አገራችን ያለችበት አደጋ የሚታያቸው አስተዋይና አርቆ አሳቢ የኢሕአዴግ መሪዎችና አባላት የራሳቸውንም ሆነ የድርጅቱን ህልውና ማስከበርና ማስቀጠል ሚችሉት ድርድሩን በገለልተኛ አደራዳሪዎች እንዲመራ በማድረግ ብቻ ነው።

ድርድሩ ከፓለቲካ ፍጆታ ያላለፈ ከሆነ ግን በሌሎች አገሮች ያየነውን የህዝብ ሰቆቃ ለመድገም ጥቂቶች የቆረጡ መሆናቸውንና በኢሕአዴግ ውስጥ ይሄው አፍራሽ አስተሳሰብ የበላይነቱን ይዞ ገዢው ፓርቲ ሌሎች ቀደምት ስርዓቶች የተጎናፀፉትን ውድቀት እየተጠባበቀ መሆኑን ያመላክታል።

ለተተኪው ትውልድ መግባባትን እናውርስ።

ፎረም 65
#Ethiopia #Forum65 (info@65percent.org)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. በለው! says

    April 5, 2017 12:42 pm at 12:42 pm

    > በመደርደር እና በመደራደር ወይንም ውይይት መካከል ብዙ ልዩነት አለ።
    መደርደር….አጋር..ደጋፊ/ተደጋፊ…ሶስተተኛ አማራጭ በመሞጋገስና መደናነቅ ላይ የተመሠረተ ሊሆን ይችላል።
    መደራደር…የሥልጣን፡ የገንዝብ፡ የዕውቀት፡ ኅይል..እኩሌታ መሆንን ማካተት አለበት።
    መወያየት…ያለውን ለማስቀጠል፡በቀረው ላይ ሐሳብ ለመጨመር፡አዲስ ሀሳብ አፍልቆ ለማጋራት፡ ቀጥልበት ግፋ በርታ ለማለት ነው።
    » አዳሜ የቁጥር መሙሊያ እንጂ እንደቁጥር ሳትቆጠር ነው እስረኛ ካልተፈታ ወይ ፍንክች!ውይይት፡ ድርድር እያለች የዲያስፐር መመሪያ የምትቀበለው? ይህ ሁሉ ተደርዳሪ…
    (፩)የፖለቲካ ፓርቲዎች ደረጃውን የጠበቀ ቤት በኪራይ ማግኘት ያልቻሉ ቢያንስ አንድ የተሟላ የፓርቲ ፅ/ቤት የላቸውም።
    (፪)የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሚያደርጉት የአዳራሽ ስብሰባ ከማስፈቀደና ማሳወቅ ባሻገር የሚያከራያቸውም የለም።
    (፫)የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያቀርቡትን ማንኛውንም የህትመት አገልግሎት የሚያትምና የሚያቀርብላቸው የለም።
    (፬)የፓርቲ አባላት የፓርቲውን ሰነዶች (የድምፅ፣ የምስል፣ የህትመት፣ ወዘተ) በሚያሰራጩበት በፖሊስ፡በደህንነትና ካድሬዎች ሆነ ልዩ አካል ጫናና ወከባ ይደርስባቸዋል።
    __”ተቃዋሚዎች አብዛኞቹ ምንም ለህዝብ የሚጠቅም የፖለቲካ ፍላጎት የላቸውም፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ለመኖር የሚያስፈልጋቸውን ምንዳ ከኢህአዴግ እንዴት እንደሚሰፈርላቸው መጠበቅ ብቻ ነው፡፡”
    __”ጥቂቶቹ ተቃዋሚዎች፤ በተለያየ የውስጥና የውጭ ጫና ተጠልፈው፤ ከውይይቱ ምን ማግኘት እንዳለባቸው ሳይሆን በውይይቱ ወቅት የህዝብ ግንኙነት ስራ በመስራት የውስጥና የውጭ ጫናውን ለማለዘብ እና ለህዝብ ቋሚ ተጠሪ መሆናቸውን ለማሳየት የሚውተረተሩ ናቸው፡፡”ሲሉ አቶ ግርማ ሰይፉ እንደገልጹት
    ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
    ***ዳግም መርዶ አይሁን እና አቶ በረከት “፹ ከመቶ የፓርቲያችን አባልና አጋር ገበሬው ነው። የገበሬውን ጥያቄ ከኢአዴግ ወዲያ የሚያውቅልኝ ማንም የለም ብሎ ተቀምጧል ለዚህ ነው ተቃዋሚው ቦታ የሌለው” ሲሉ በውይይቱም ላይ ተደጋግሞ የሚወሳው ኢህአዴግ ብዙ ለውጥ አምጥቷል ያልተሰራበት ወደታች ሕጻናት ት/ቤት ገብተን ሥራችንን ማስረጽ(ማናወጥ) ብቻ ነው የጎደለን ሲሉ የአሁኑ መደርደር ለፎቶ ነው እንዴ? ዘይገርም!
    ** ፳፪ ፓርቲዎች የሚያደርጉት ውይይት ዓላማው ከ፪፲፻፰ዓም ኅዳር ወር ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል ተቀስቅሶ ወደ አማራ ክልል በተዛመተው ህዝባዊ ተቃውሞ (አንዳንዶች ቁጣ ይሉታል ኢህአዴግ ደግሞ ልማቱ ያመጣው ተቃውሞ ሲል ይጠራዋል)
    ኢህአዴግ ልማቱ ያመጣው ተቃውሞ ብሎ ከጠራው ሕዝቡ ልማት ጠሊታ ፓርቲዎች ልማት ወዳድ ናቸው ማለት ነው?
    ሌሎች ቁጣ የሚሉት ልማት ለምን መጣ ብለው ነው ወይንስ የልማት ተጠቃሚ አደለንም ልማቱም የጥቂት ጥቅማጥቅምኞችና ክልላዊ ሙሰኞች ነው አሉ ይሁን? ስለዚህ ‘ሌሎችም’ ‘ፓርቲዎችም’ ‘ኢህአዴግም’ አልተግባብቶም!
    ፩) ዶ/ር ጫኔ ከበደ “በኢህአዴግ ከቀረበው ሀሳበ ላይ የሚሻሻሉ ህጎች ካሉ ማሻሻል የሚል ይገኝበታል። እኛም ይህን ሀሳብ ስንመለከተው መሻሻል ያለባቸው ህጎች እንዲሻሻሉ ተብሎ ይስተካከል እንጂ “ካሉ” የሚለው ቃል የገባው ለማደናገር ካለሆነ በስተቀር ህጎች እንዲሻሻሉ እኮ ነው የተሰበሰብነው ብለን አቋማችንን ገልጸናል። በእኛ በኩል የቀረበውንና ኢህአዴግ ሃሳብ የሰጠበት ደግሞ አሳሪ የሆኑ ህጎቸ ሁሉ ይሻሻሉ የሚለውን ሲሆን አሳሪ የሚለውን ገላጭ ቃል መጠቀማችን ገና ወደ ድርድር ከመግባታቸሁ በፊት አቋመ እየወሰዳችሁ ይመስላል ሲል ተከራክሯል። በሌላ በኩል ደግሞ የብሔራዊ መግባባት እውን እንዲሆን የሚለው ሀረግ ላይ “እውን መሆን” በሚለው ሀሳብ ዙሪያ ሰፊ ውይይትና ንግግር አካሂደንበታል”
    ፪)“በመሰረቱ አሁን የመጣውን የውይይት ክርክርና ድርድር የሚል ርዕስ ኢህአዴግ ለማደናገር ያመጣው እንጂ አነሳሱ ለድርድር ነበር። የተወሰኑ ፓርቲዎች ድርድር እንጂ ክርክርም ሆነ ውይይት የማንቀበል መሆናችንን ገልጸናል።”ይላሉ
    *************!
    ___መጀመሪያ የተጠሩበት ዓላማና ግብ ሲኖረው (ውይይት)ያስፈልገዋል፡ የቀረቡ ሀገራዊ ሓሳቦች ከነበረው ለተሻለ አሠራርና የሕዝብ ሰላምና ደህንነት ሲባል ግልጽ (ክርክር) ተደርጎባቸው ለፓርቲ አመራርና አባላት ብቻ ሳይሆን ለጠቅላላ የሀገሪቱ ዜጋ ተሳታፊነት ሊቀርብ የግድ ይላል፡ ይህ ከውይይት ወደ ክርክር ያለፈ ሐሳብ በአብዛኛው በአብላጫ ድምጽ የሚያልፍ ሲሆን የተወሰነ ነጥብ ግን ሙሉ በሙሉ የሚያሻር፡ የሚሰረዝ፡ የሚቀየር ሆኖ ካልተገኘ ግን (ድርድር)ውስጥ ያስገባል።
    __ ግን አሁን ፓርቲዎቹ የሚወያዩት፡የሚከራከሩና የሚደራደሩት በሕልውናቸው ላይ ስለሆነ የሀገርና ሕዝብ ጉዳይ መች ተነካና!? አሁን ያለው ጉዳይ በፓረቲ አመራር ሳይሆን እጅግ ብዙ ውስብስብና አደገኛ አዝማሚያ ላይ የከተተን ሙስና መር ኢኮኖሚና ጥቅማጥቅም የጎጣኛ ወታቦ (ክልል) የብዙ ምሁራን የባለድርሻ አካላት ሊሳተፉበት የግድ ነው አለዚያ የፉክክርና የውድድር ‘ትግል’ ሳይሆን እንደተለመደው የእርስ በእርስ (የጎንዮሽ) ‘ልፊያ’ ሆነ በለው!

    Reply
  2. በለው! says

    April 5, 2017 01:10 pm at 1:10 pm

    …”ህውሐት/ኢህአዴግ ፹ ከመቶ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በእኛ የተፈጠሩ: ለእኛ የሚኖሩ: ያለ እኛ የሚበታተኑና የሚጠፉ ይላቸዋል ። ምርጫ የላቸውም ይመርጡናል ይላቸዋል ።በእርግጥም ሲደገስም ሲጨፈርም ሲለቀስሞ ተጋፍተው ተገፋትረው ይገኛሉ ።ጥቅማጥቅም አለቻ!በቦታው ያልተገኙ የአጋርነት የትብብር ትግል ይሉና የጎንዮሽ ልፊያን አጧጡፈውታል ። አዲስ አበቤውን ወራሪና መጤ ተብሎ በማኒፌስቶ የተፃፈውን በሙሉ ልብ የሚደነፉትም :አዲስ አበቤው ምሕረት እንዲደረግለት ለመኖር ፍቃድ የሚጠቁትና የሚለመኑትም እነኝሁ የህወሓት ኢህአዴግ ምልምሎች ፎረም ፷፭ ላይ ነው ።
    — “እሳት ላይ የተጣደ የጀበና ውሃ እሳቱ እስካለ ድረስ መፍላቱንና መንተክተኩን ይቀጥላል።”
    * አላግባብ ቆስቁሰው ውሃው ገንፍሎ እሳቱን ያጠፋው እኮ ” ደምህን ደሜ ነው!” ያሉትን ጅግኖች “አንድነት የለም! አንድ አደለንም! ኢትዮጵያዊ ማንነት የለም!እኛ ልዩ ነን ባሕልና ቋቋንችንን እንዳትበክሉ አትድረሱብን ያሉትና አርጩሜ: አለንጋ: ጅራፍ:ለህወሓት/ኢህአዴግ ያቀበሉት ቻርተርና ኮማንድ ፖስት አዘጋጂዎቹ የእናንተው ምሁር ተብዬዎች ዲያስፖራው(ፈላሽ) የፀጋይ አራርሳ :ጀዋሪው መሀመድ ቃለመጠይቅ ደግማችሁ አድምጡ ።
    —- “ለዚህ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ግልፅ ፣ አሳታፊ ፣ ሚዛናዊና በገለልተኛ አካላት የሚመራ ድርድር ማድረግ ብቻ ነው።” * መቼም እነኝሁ ሽማግሌዎች ይሁንልን እንዳትሉን !? መድረክ የግልገል ነፍጠኛ የአማራ ልጅ ልጆች እንዳያንሰራሩ የጎንዮሽ እየታገልኩ ስላለ አንድነት ፡መኢአድ፡ ሰማያዊውን በመበተን የተሰጠውን ተግባር አጠናቀቀ አሁን በተራው ህወሓት/ኢህአዴግ ተፋው።የበየነ ጴጥሮስን የዲሲ የአዳራሽ ፉከራም ማድመጥ ነው። ማኒፌስቷቸው አንድ ነው ተደረደሩ እንጂ አይደራደሩም። ሥልጣን ሊጋሩ ነው ?
    — ፹ከመቶ ድሃ ማይም ገበሬ ፷፭ ከመቶ ዴሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት (ተከልሎና ተከልክሎና) መኖርን ተግቶ ያደረገ ከሜንጫ አብዮት (አንገት መቅላት) የኢኮኖሚ አብዮት(ከቂጥ ቆርጦ ለአፍ)
    “ድርድሩ ከፓለቲካ ፍጆታ ያላለፈ ከሆነ ግን በሌሎች አገሮች ያየነውን የህዝብ ሰቆቃ ለመድገም ጥቂቶች የቆረጡ መሆናቸውንና ፡ በኢሕአዴግ ውስጥ ይሄው አፍራሽ አስተሳሰብ የበላይነቱን ይዞ ገዢው ፓርቲ ሌሎች ቀደምት ስርዓቶች የተጎናፀፉትን ውድቀት እየተጠባበቀ መሆኑን ያመላክታል።፡ለሀገርና ሕዝብ ውይይት:ድርድር:ክርክር: በሚስጥር የሆነው ለምን ይሆን? ህወአት/ኢህአዴግ ሀሳብ አዋጡ ይላቸዋል እኔ እፈፅመዋለሁ ብሎ በካልቾ እየለጋ ያበራቸዋል ወይንም በአድመኝነት ሁሉንም ቃሊቲ ያጉራቸዋል። ልብ የለም እንጂ በረከትና ቲንክ ታንኩ ለተደረደሩት ቀድመው ነግረዋቸዋል “ምንም ለውጥ የለም! አይኖርም ! አትጠብቁ! ድክመታችን ዓላማና ሥራዎቻችንን ለ፷፭ ከመቶው ሕዝብ ላይ መጫን/ማስረፅ ብቻ ነው ” ሲባል አላጨበጨባችሁምን? የነብርን ጭራ አይዙም ከያዙም አይደራደሩም አላልንም! ? አደለም እንዴ? ዋ…

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule