እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ማርች ፩፯ ፳፩፯ በኢትዮሚድያ ድህረ ገፅ ላይ በወጣ ፅሁፍ ላይ ወለላዬ ከስዊድን የተባሉት ፀሀፊ “እምዬ ምኒልክ ወላዋይ ነበሩ ወይ?” ሲሉ አበክረው ይጠይቃሉ። በፅሁፉ መሃልም ወለላዬ ጋዜጠኞችና ተመራማሪዎች የትናቹ፤ ዝም አትበሉ ሲሉ ይማፀናሉ። የጥሪያቸው ምክንያትም የስዊድን ሶሻል ዴሞክራት ተቀጥላ የሆነው የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራት ማኅበር የአድዋን ድል በዓል ምክንያት በማድረግ ማርች ፭ ቀን ፳፩፯ ባዘጋጀው ዝግጅት ላይ የመጨረሻው ተናጋሪ ያደረጉት ንግግር ነበር። እኝህ ሶስተኛ ተናጋሪ ፕሮፌሰር ተከስተ ነጋሽ ይባላሉ። በድህረ ገፅ ላይ የሚገኝ መረጃ እንደሚያሳየው ፕሮፌሰር ተከስተ አስመራ ኤርትራ የተወለዱ ብዙውን ዘመናቸውን ደግሞ ስዊድን ውስጥ በታሪክ መምህርነትና ፀሀፊነት የሰሩ ሰው ናቸው። ብዙዎቹ የጥናት ፅሁፎቻቸውም በኤርትራ የቅኝ ግዛት ታሪክ ላይ … [Read more...] about ስለአደዋ ስለምኒልክ በስዊድን
Opinions
የኔ ሃሳብ
እምዬ ምኒልክ ወላዋይ ነበሩ ወይ?
የአድዋን በዓል አከብራለሁ ብዬ ሄጄ፤ አፄ ምኒልክ ሲሰደቡ ሰምቼ ተመለስኩ ምሁር ባልባልም በቃ! አልጸጸትም፣ ፊደል ቢሸከሙት አያደርስም የትም። አሮጌ ልብስ ነው አስቀያሚ ኮተት፣ ማስተዋል ካነሰው ቢከመርም ዕውቀት። (የረቡዕ ግጥም ፫ኛ ዓመት፣ ወለላዬ) የስዊድን ሶሻል ዴሞክራት ተቀጥላ የሆነው የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራት ማኅበር የአድዋን ድል በዓል ምክንያት በማድረግ ዝግጅት አድርጎ ነበር፤ እሁድ ማርች 5 ቀን 2017። በዝግጅቱ ላይ እንድገኝ ጥሪ ደርሶኝ ከተካፈሉት ጥቂት ሰዎች መካከል አንዱ ነበርኩ። ዝግጅቱ በቪድዮ ክሊፕ እንድናዳምጣቸው የተመረጡልን ሰዎች ሲኖሩት፣ በአካል የተገኙ እንግዳም ነበሩ። ክሊፑን በስክሪን እያየን ካዳመጥናቸው አንዱ “The Battle of Adwa” የተባለውን መጽሐፍ የጻፉት ፕሮፌሰር ዮናስ ሬይሞንድ ሲሆኑ፣ ስለ መጽሐፋቸው ከኢጣሊያ የታሪክ … [Read more...] about እምዬ ምኒልክ ወላዋይ ነበሩ ወይ?
የሕይወት ዋጋ – “አጥንታቸውን እሾህ ያርገው”
በ2009 ዓ.ም. ቆሼ የሚባል ሰፈር ወይም መንደር ተፈጠረ፤ ቆሼ ማለት ቆሻሻን ማቆላመጫ ነው፤ ቆሻሽዬ ማለት ነው፤ ቆሼ የቆሻሻ ተራራ ነው፤ በዚያ የቆሻሻ ተራራ ዙሪያ መሄጃ የሌላቸው ሰፈሩበት፤ ጥንት ሴትዮዋ እንዳለችው፡- እሾህ ብቻ ሆነ እግሬን ብዳብሰው እንዴት መራመጃ መሄጃ ያጣል ሰው! ሴትዮዋ ይህንን ያንጎራጎረችው ከብዙ ትውልዶች በፊት ነው፤ ጉልበተኞች የኢትዮጵያን ሰዓት ሰንገው ስለያዙት አይነቀነቅም! ባለህበት ሂድ! ነው፤ ዛሬም መሄጃ የለም፤ ቆሻሻንም የሙጢኝ ቢሉ ማምለጥ አይቻልም፡፡ እነዚህ አንድ መቶ አሥራ ሦስት ሟቾች በርግጥ ሰዎች ናቸው? በርግጥ ኢትዮጵያን ናቸው? የምናገረው ጠፍቶኛልና ጥያቄዎች ብቻ ልጠይቅ፡-- ቤታቸውን ጉልበተኞች አፍርሰውባቸው፣ መሬታቸውን ሰማይ-ጠቀስ ወይም መንገድ ለመሥራት መሬታቸውን ወስደውባቸው የሚደርሱበት አጥተው፣ ባዶ ቦታ ፈልገው … [Read more...] about የሕይወት ዋጋ – “አጥንታቸውን እሾህ ያርገው”
ድንቄም ሀዘን!
ሲሉ ሰምታ ዶሮ ሞተች ከቋት ገብታ ይሉ ነበር ሳይማሩ የተማሩት ጠቢባን የሆኑ ቀደምት እናትና አባቶቻችን። ድህነት ዛዝላውን ጭኖባቸው የመከራ ኑሮ የነበሩ ወገኖቻችንን መንግስት የቆለለው የቆሻሻ ምርት ተጭኗቸው ሲያልቁ መንግስት የሶስት ቀን ሀዘን ተቀመጠ የሚል አስቂኝ ወሬ በሰማሁ ጊዜ ነበር የጠቀስኩት የዶሮዋ ምሳሌ ትዝ ያለኝ። ሀገር አለን ብለው እንደወግና ስርአታቸው አደባባይ ሊውሉ የወጡ ወገኖቻችንን ባልተደበቀ ሸር በቢሸፍቱ ከተማ እንደወጡ ያስቀረው መንግስት በወቅቱ የሶስት ቀን ሀዘን በማወጅ በሙታንም ህያዋንም ላይ ቀልዶ ነበር። እነሆ አሁን ደግሞ በከመረው ቆሻሻ ህፃናትና ስቶችን ጨፍልቆ ከፈጀ በኋላ ሳቂታውን ፓርላማ ሰብስቦ በሉ አሁን ደግሞ የሀዘን ሰአት ነው አለ አሉ። እንዴት ያለ ቀልደኛ መንግስት ነው ጃል? ለገደለው ህዝብ ሆዱ የሚባባ ሩሩህ መንግስት! የዚህ አይነቱ ቀልድስ … [Read more...] about ድንቄም ሀዘን!
ሕዝባዊ ናዳ ሊውጠው የሚገባ አገዛዝ
ቅዳሜ መጋቢት 2 ቀን 2009 ዓ.ም. ከምሽቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ በአዲስ አበባ ደቡብ ምዕራብ ክፍል በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ በተለምዶ “ቆሼ ሠፈር” እየተባለ በሚጠራው ቆሻሻ ማጠራቀሚያ በደረሰው የመሬት መናድ አሳዛኝ አደጋ፣ የሕዝብ እልቂት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን ከ“አንድ ሀገር! አንድ ሕዝብ! ኢትዮጵያችን ሕዝባዊ ንቅናቄ” እንገልጻለን። የወያኔ አገዛዝ ሕዝባችንን ለኅሊና በሚዘገንን አኳያ በረሃብ እየቀጣ መሆኑ በተደጋጋሚ የተገለፀ ጉዳይ ነው። በመዲናችን አዲስ አበባ ህብረተሰቡ የዕለት ጉርሱን እንዳያገኝ በተለያየ መልኩ ይቀጣል። በየቤቱ ያለውን ረሃብተኛ ቤት ይቁጠረው። በቀን አንዴ ለመመገብ ያለውን እሩጫ የሚፈጋው ያውቀዋል። ወያኔ በተለይ ከ1997 ዓ.ም. የምርጫ ክስረት በኋላ የ“አዲስ አበባን ሕዝብ እንቀጣዋለን” እንዳለው አንዱ ጅራፉ ረሃብ ነው። ሆን ተብሎ … [Read more...] about ሕዝባዊ ናዳ ሊውጠው የሚገባ አገዛዝ
የማህበረሰብ ጠንቅነት ዝንባሌን እንዴት ማወቅና መጠንቀቅ እንችላለን?
ላለፉት በርካታ አመታት እኛ በውጭና በሀገር ዉስጥ የምንገኝ ኢትዮጵያውያንና ትዉልደ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያውያ ዉስጥ የተሻለ መንግሥታዊ አስተዳደር እንዲመጣና ባጠቃላይ ፍትህ እንዲሰፍን ያላሰለሰ ጥረት ስናደርግ ቆይተዋል። ይሁን አንጂ በተለያዩ ተቆጥረዉ በማያልቁ ምክንያቶች፣ አብዛኞቹ ደግሞ እራሳችን በፈጠርናቸዉ ድክመቶች እስካሁን የከፈልናቸዉ መሥዋቶች፣ ድካማችንና ልፋታችን የታለሙለትን ያህል ግብ ሊመቱና ፍሬያማ ሊሆኑ አልቻሉም። በዚህም የተነሳ ብዙዎቻችን በመሰላቸትና በምሬት ይመስላል፣ ከዋናዉ ጠላታችን ከወያኔ ጋር ከመታገል ይልቅ ምሬትና ብስጭታችንን ስርዓቱን በሚደግፉ የዉጭ ሃያላን መንግሥታትና ባመዛኙ ደግሞ ኃይላችንን እርስ በርሳችን በመነታረክ ላይ እያባከንን እንገኛለም (ተጠምደናል)። ከዚህ በፊት ስንጓዝበት ከነበረዉ የተሳሳተ ጉዞ ሳንማር አሁንም የቀድሞ ስተታችንን … [Read more...] about የማህበረሰብ ጠንቅነት ዝንባሌን እንዴት ማወቅና መጠንቀቅ እንችላለን?
የዓለም ሴቶች ማኅበርን በተመለከተ የእቴጌ መነን ቃል
ግርማዊት እቴጌ መነን ይህንን ቃል የተናገሩት ከዛሬ 80 ዓመት በፊት ሲሆን መግለጫውን ብርሃንና ሰላም ጋዜጣ አውጥቶታል። (Copied from an Amharic Chrestomathy by Edward Ullendorff page 37) መረጃውን ያደረሱን Getachew Selassie; gashaselassie@gmail.com … [Read more...] about የዓለም ሴቶች ማኅበርን በተመለከተ የእቴጌ መነን ቃል
Is There Connection Between Corruption and Democracy?
“Democracy must be built through open societies that share information. When there is information, there is enlightenment. When there is debate, there are solutions. When there is no sharing of power, no rule of law, no accountability, there is abuse, corruption, subjugation and indignation.” Atifete Jahjaga Introduction EPRDF has been making deafening noise about its fight against corruption. Does it mean it? We will find out. One thing is clear. That is the government is admitting that … [Read more...] about Is There Connection Between Corruption and Democracy?
የሂወት ውል /Hewett Treaty/
የሂወት ውል በ1876 ዓ.ም (1884) አጼ ዮሐንስ ከእንግሊዝና ግብጽ ጋር ውል የገቡበት ሲሆን ንጉሱ በሰሩት የፓለቲካ ቀመር ስህተት የኢትዮጵያን ጥቅምና ሙብት አሳልፈው ለወራሪዎች የሰጡበት፣ ከጎረቤት ደርቡሾች ጋር ጠላትነት በመፍጠር ለጎንደር መተማ መውደም (በደርቡሾች መቃጠልና መዘረፍ) እንዲሁም ለራሳቸው ለዮሐንስም ህይወት መጥፋት ምክንያት የሆነ፣ ኢትዮጵያን እርስ በርሱ ተያያዥነት ወዳለው ችግር ውስጥ የከተተ አስጠቂ ውል ነው። ይህንን ውል ተከትሎ እንግሊዝ ምጽዋን ተፈጥሯዊና ታሪካዊ ባለቤት ለሆነችው ለኢትዮጵያ ማስረከብ ሲገባት ለጣሊያን አሳልፋ ሰጠቻት። ጣሊያን ሳትለፋና ሳትደክም እንደ ገና ስጦታ ከእንግሊዝ ከተበረከተላት ከምጽዋ ወደብ በመነሳት ወደ ውስጥ ሃገር ቀስ በቀስ መስፋፋት ጀመረች። ጣሊያን ኢትዮጵያን ለመውረር ምጽዋ ላይ ስትደራጅ ብሎም ያለማቋረጥ ወደ ውስጥ … [Read more...] about የሂወት ውል /Hewett Treaty/
ከቅራኔ ወደ መግባባት (“የት ነበርሽ?”)
ቅራኔ ምንድን ነው? ቅራኔ ለምን ይፈጠራል? እንዴት ይገለፃል? ቅራኔን ለመፍታት መነጋገር ጥቅሙ ምንድን ነው? በሚሉና በሌሎች ከቅራኔ ጋር የተያያዙ ነጥቦች ላይ ለመወያየት እንግዳችን የቅራኔ አፈታት ባለሙያ (Conflict Resolution Expert) ዶ/ር ብርሃኑ መንግስቱ ናቸው። ዶ/ር ብርሃኑ በኦልድ ዶሚኒዮን ዩኒቨርሲቲ የፐብሊክ አድሚንስትሬሽን ፕሮፌሰር ሲሆኑ፡ የ"መንግባባትን ገንቢ የኢትዮጵያውያን መድረክ" ሰብሳቢ ናቸው። … [Read more...] about ከቅራኔ ወደ መግባባት (“የት ነበርሽ?”)










