
ቅዳሜ መጋቢት 2 ቀን 2009 ዓ.ም. ከምሽቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ በአዲስ አበባ ደቡብ ምዕራብ ክፍል በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ በተለምዶ “ቆሼ ሠፈር” እየተባለ በሚጠራው ቆሻሻ ማጠራቀሚያ በደረሰው የመሬት መናድ አሳዛኝ አደጋ፣ የሕዝብ እልቂት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን ከ“አንድ ሀገር! አንድ ሕዝብ! ኢትዮጵያችን ሕዝባዊ ንቅናቄ” እንገልጻለን።
የወያኔ አገዛዝ ሕዝባችንን ለኅሊና በሚዘገንን አኳያ በረሃብ እየቀጣ መሆኑ በተደጋጋሚ የተገለፀ ጉዳይ ነው። በመዲናችን አዲስ አበባ ህብረተሰቡ የዕለት ጉርሱን እንዳያገኝ በተለያየ መልኩ ይቀጣል። በየቤቱ ያለውን ረሃብተኛ ቤት ይቁጠረው። በቀን አንዴ ለመመገብ ያለውን እሩጫ የሚፈጋው ያውቀዋል። ወያኔ በተለይ ከ1997 ዓ.ም. የምርጫ ክስረት በኋላ የ“አዲስ አበባን ሕዝብ እንቀጣዋለን” እንዳለው አንዱ ጅራፉ ረሃብ ነው። ሆን ተብሎ እጅግ ባሻቀበው የኑሮ ውድነት ሕዝቡ እንዲገላታ ተደርጓል። የወያኔንና የባለፀጎችን ትርፍራፊ ከቆሻሻ መጣያ እንዲለቅሙ የተገደዱ ቤተሰቦች ቁጥር ቀላል አይደለም።
በሀገራችን በተለምዶ ስለ እግዚሃብሔር ብሎ ለመጣ የኔብጤ እንኳ ትርፍራፊ አይሰጥም። ዛሬ ግና ትርፍራፊን በጉርሻ የሚነግዱ ተበራክተርዋል። ከጉርሻ ሽያጭ ያመለጠው ደግሞ ከሚጣልበት ቆሻሻ ይለቀማል። ዛሬ በዘመነ ወያኔ የሰው ልጆች ከአሞራና ውሻ ጋር የሚበላ ሲሻሙ ማየት እውን እድገት ነውን? እውን ሕፃናትና ወጣቶች የሚላስ ሚቀመስ ለማግኘት ቁሻሻ ውስጥ ሲተራመሱ ማየት ለአንድ መንግስት የኅሊና እርካታ ሊሰጥ ይገባልን? አዎ! ለወያኔ ዓይነት በሀገር፣ በሕዝብ፣ በሰንደቅ ዓላማችን፣ በታሪካችን፣ በክብራችን ለመጣ ግፈኛ አገዛዝ እንደ “ድል ፍሬ” ያስፈነድቃል፤ ያስጨፍራል። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply