• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሰው ገድለው አንገታቸው ሊቀላና ሊያሳዝኑን የነበሩት በነጻ ተለቅቁ!

March 22, 2017 12:34 am by Editor Leave a Comment

  • ሟች – ሊደፍራቸው የመጣ ሳውዲ ወጣት
  • ገዳይ – ሚስትና ቤቱን የተከላከለ ጎልማሳ
  • ፍርድ ሰጭ – ከፍተኛው የሸሪአ ፍርድ ቤት የወንጀል ችሎት
  • እነ ሁሴን እንደገና አልተወለዱ ይሆን?

ልክ የዛሬ 3 ዓመት ገደማ ሳውዲ አረቢያ ጅዳ “ሀበሾች ሳውዲ ገደሉ!” ተባለ፣ መረጃውን የሰማሁት እኔም በእስር ላይ እያለሁ ነበር። እንዴት ገደሉ ብየ ስጠይቅ ቤታቸውን ሊዘርፉና የሀበሻውን አባወራ ቤት ሊዘርፉ የገቡ ሳውዲ ወጣቶች ሴቶችን ሊደፍሩ በተነሳ አምባጓሮ መሆኑን በደፈናው ሰማሁ። ከዚያም የቀረውን ተባራሪ የእስር ቤት መረጃ የማጣራበት መንገዱ ዝግ በሆነበት የጨለማ ወቅት ገደሉ የተባሉት ወደሚታጎሩበትና እኔ ወዳለሁበት ወህኒ እስኪመጡ የታሳሪውን ተባራሪ የማያጠግብ መረጃ ሳነፈንፍና ስኮመኩም ከረምኩ። ከሶስት ወር በኋላ  እኔ ከወህኒ እስክወጣ ወደ ማዕከላዊው የብሪማን እስር ቤት ሳይመጡ ቀሩ፣  እኔም ጉዳይ ተጣርቶ ለእስር ወጣሁ . . .

ከእስር ከወጣሁ በኋላ ጉዳዩን ከገዳዮች አንደበት የመስማት እድሉ ገጠመኝ “ከንጋቱ ላይ የኢድ በዓልን ልናከብር ስንዘገጃጅ ቤታችን ተንኳኳ፣ ማነው? ስል ፖሊሶች ነን አሉኝ፣ ከፈትኩላቸው። ግብተው ሴትና ወንድ ብለው ለያይተው አስቀመጡን ፣ ዘረፋ ጀመሩ፣ ዝም አልን፣ ቆዩና ሴቶቻችን ለመድፈር ሲሞክሩ የባለቤቴን ጩኸት ሰማሁ ፣ ዘልዬ ከተዘጋው ክፍል ወጣሁና ከወጣቶች ጋር ግብግብ ያዝን፣ …ሟች ሳውዲ ስለት ይዞ ሊወጋኝ ሲሰነዝር የያዘውን ስለት ቀኝቸ ደረቱ ላይ ወጋሁትና ከቤቴ በር ገፍቸ አስወጣሁት፣ ጓደኞቹ ተረባርበው ወሰዱት፣ ፖሊስ ጠርተው ነበርና በፖሊስ ተከበን ተያዝን …ሚስቴን ሊደፍር ስከላከል ብወጋውም ይሞታል አላልኩም ነበር፣ መሞቱን ሰማሁ፣ አዘንኩ …” ይህን ምስክርነት የሰጠኝ የወንጀሉ ተጠያቂ ገዳይ ወንድም ሁሴን ሃሰን ነበር! ታዲያ ያኔ በሞት ፍርደኞች መካከል የጨለማ ህይወትን ሲገፋ በነበረበት በጭንቋ ሰአት ሆን ብየ ነፍስ አላጠፋሁምና ስለፍትህ ድምጻችን አሰማልን ብሎ ተማጽኖኝ ነበር!

ከዚያ ወዲህ ባሉት ጊዜያት የወንደም ሁሴንን ወንድምና የሁለት ጓደኞቹን የፍርድ ሂደት በቅርብ ተከታትተዋለሁ ፣ መረጃም በሰፊው አቀርብበት ነበር። ሳውዲ መተዳደሪያ ባደባደረጋቸው የሸሪአው ህግ “የገደለ ይገድላል” ቢባልም እንኳ የራሱ ስርአትና ደንብ ስለመኖሩ ይህ ውሳኔ ማሳያ ይመስለኛል፣ ግፍ ሲፈጸምበት ራሱን ሲል ገደለ ትበሎ ይገደል እንደማይባል ትልቅ ማሳያ በመሆኑ ብቻ ሳይሆን በስራ ላይ ውሎ በእኛ ዜጎች ላይ ስላየሁት ደስ ብሎኛል። ለዜጎች መብት የምናስብ ከሆነም ይህ አስተማሪ ነው።

የሳውዲ ህግ አያሰራንም ከሚለው ተራ ቱማታ መውጣት ከቻልን ብዙዎችን መታደግ እንደምንችል ምልክት ነው። ይህን እውነት ተከትለን በህግ አግባብ ፍትህ ማግኘት ስላለባቸው የሞት ፍርደኞች መብት ማስከበር ዙሪያ ተወካዮቻችን እንዳለባቸው ጠቋሚ ነው።

እንደ ቀደሙት አመታት በየስብስባው “የሳውዲ ህግ ለመብት ጥበቃው አይመችም” የሚል ስንካላ ምክንያት ከተወካዮቻችን ሲቀርብ መስማት አንሻም። በተለይ በአረብ ሃገራት ያሉ የመንግሰት ተወካዮቻችን ከዚህ ፍርድ ተነስተው ምን እየሰራን ነው ብለው ራሳቸውን መመርመር ይገባቸዋል! ልብ ያለው ልብ ይበል! የጎዳን የሳውዲ ህግ ሳይሆን ህጉን ተከትሎ መብታችን የሚያስከብር ሁነኛ የመንግሰት ተወካይ ነው፣ ደረቅ እውነቱ ይህ ነው። ዛሬ ከምንም በላይ የዘገየው ፍትህ ርትዕ እንዲህ ተከብሮ በማየት ደስ ብሎኛል፣ ነገም ግፍ ተፈጽሞባቸው የታሰሩት ዜጎቻችን ነጻ የሚወጡበት ተስፋ እንዳለ በሚያነላክተው የፍርድ ውሳኔ እርካታ ተስምቶኛል፣ ተደስቻለሁ!

ሁሉንም በወጉ ከነጻ ከተፈቱት ከእነ ሁሴን ጋር ቁጭ ብለን እናዎጋለን፣ ደስታቸውን እንጋራለን፣ የሞት ፍርደኞችን ህይወት ያለ ተስፋ የሚገፋበትን የጨለማውን የእስር ቤት የአመታት ውሎ አዳር በጨረፍታ ማውጋታችን አይቀርም! በእነ ሁሴን ዙሪያ መረጃ ስንለዋወጥ ትብብራችሁ ላልተለየኝ፣ በጸሎት ለረዳችኋቸው ሁሉ እኔም እነሆ Mission Accomplished እያልኩ በደስታ ምስጋናዬን አቀርባለሁ!

በዝርዝር እስክመለስ ወንድም ሁሴንና ጓደኛ፣ ቤተሰቦቹ እንኳን ደስ አላችሁ፣ እንኳን ደስ አለን!

ዛሬም ዜጎቻችን በደል ደርሶባቸው በየወህኒው ይገኛሉ፣ ስለተበደሉት ድምጻችን እናሰማ!

ቸር ያሰማን!
ነቢዩ ሲራክ
መጋቢት 13 ቀን 2009 ዓም

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule