ከተጀመረ ወራትን ያስቆጠረውና ከሁለት መቶ በላይ ሰዎች በጭካኔ ለመገደላቸው መረጃ የሚቀርብበት ሕዝባዊ ንቅናቄ አሁንም በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ቀጥሎዋል። ኢህአዴግ በአፈቀላጤዎቹ አማካኝነት "ሰልፍ የወጣ የለም፣ ከተማችን ሰላም ነው፣ የተገደለ የለም፣ . . ." በማለት የማስተባበያ ሙከራው በራሱ ሹሞች ሲጨናገፍ በተደጋጋሚ ይስተዋላል። በሌላ በኩል በፌዴራልና በአግአዚ መራር ሰቆቃ እየደረሰበት ያለው ሕዝብ "ባርነት በቃን፣ ግድያው ይቁም፣ የታሰሩት ይፈቱ፣ . . ." የሚሉ መፈክሮችን እያነገበ ሰላማዊ ተቃውሞውን ቀጥሎዋል። የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ባለፉት ሦስት ቀናት የተከሰተውን ያቀረበው ዘገባ ከዚህ በታች ይገኛል። ባለፈው ሐምሌ ወር ከአምቦ ወደ አዲስ አበባ ተወስዶ ታስሮ እንደነበርና ታሞ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ህክምና ላይ ሳለ ህይወቱ እንዳለፈ የተነገረው ተማሪ አብደታ … [Read more...] about በኦሮሚያ ከተሞች የሚካሄድ ተቃዉሞ ቀጥሏል
News
ዜና
በልማት ስም የሚካሄዱ እርምጃዎች ይቁሙ
ተቃዋሚው ሕብረት የኢትዮጵያ ፌድራላዊ አንድነት መድረክ፤ በአገሪቱ እየታየ ያለውን ቀውስና ሌሎች ነባር ችግሮች አስመልክቶ አሳስበውኛል፤ ባላቸው ጉዳዮች ዙሪያ በትላንትናው ዕለት ለጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ግልጽ ደብዳቤ ጽፏል። “የሕዝቦቻችንን ጥቅሞች ማዕከል ያላደረጉና ሕዝብን ያላሳተፉ በልማት ስም የሚካሄዱ እርምጃዎች በአስቸኳይ እንዲቆሙና የሃገሪቱ ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌዎች እንዲጠበቁ እንጠይቃለን።” መድረክ። መድረክ መፍትሔ ያላቸውን ባለ አምስት ነጥብ ደብዳቤ መነሻነት የድርጅቱ ሊቀ መንበር ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ከዚህ ያድምጡ። … [Read more...] about በልማት ስም የሚካሄዱ እርምጃዎች ይቁሙ
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የደረሰው ጥቃት
የጎልጉል እማኝ ዘጋቢ (ireporter) የሆኑ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የደረሰውን ጥቃት ከፎቶ ጋር አያይዘው ልከውልናል፡፡ ዘጋቢው እንዳሉት ከሆነ እዚያው ተማሪ ሲሆኑ የደረሰውን ሁኔታ በዚህ መልኩ ይገልጹታል፡- “ከትላንት ወዲያ (ማክሰኞ) ማታ ካፌ ተማሪዎች ተቃውሞ ሊያሰሙ ሲሞክሩ ፌዴራሎች በዱላ ጀመሩ፤ ከዚያም ዶርም ገባን፤ ሁላችንንም ዶርም እየገቡ በሩን እየሰበሩ እያወጡን አዳሩን ሲደበድቡን አደሩ፤ እስካሁን የሆነ ብሎክ መግባትም አይቻልም፤ የሞተ ሰው አለ እየተባለ ነው፤ እዚያም መግባት አይቻልም፤ ሌላ ብሎክ ደግሞ እሣት ተያይዞ ነበር፤ ማታ እሣት አደጋ መጥቶ አጠፋው … ወዴት እንሂድ? ወደ አገራችን እንዳንሄድ መንገድ ተዘግቷል፤ ኬላ በሙሉ (ተዘግቷል)፤ ወደ ጊቢም እንዴት እንግባ? ያገኙትን ነው የሚቀጠቅጡት፤ … ” በማለት በዚያ የደረሰውን ጥቃት እንድናሰማላቸው ከፎቶዎች ጋር … [Read more...] about ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የደረሰው ጥቃት
“ለድለላ” ሕወሃት ከፍተኛ የጦር አዛዥነት ሹመት ሊስጥ ነው!
ሕወሃት የከፍተኛ መኮንኖች “የመደለያ” ሹመት ለመስጠት ማቀዱ ተሰማ። አባይ ጸሃዬ ለህዝባዊ ተቃውሞው የተሰጠው መልስ የተለሳለሰ ነው አሉ። ህዝባዊ አመጹ ከቁጥጥሩ ውጭ መሆኑን ኢህአዴግ ይፋ አደረገ። ግርፋት፣ ግድያ፣ እስር፣ እንግልትና ስደት ያሳሰባቸው ስጋታቸውን እየገለጹ ነው። የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ የመከላከያ መረጃ አቀባዮቹን ጠቅሶ እንዳመለከተው፣ በመከላከያ ሠራዊት ውስጥ አለመግባባቱና መቃቃሩ ከሯል። በሠራዊቱ ውስጥ የአንድ ብሔረሰብ አባላት ፈላጭ ቆራጭነት የፈጠረው ልዩነት መባባሱ አሁን ከተቀጣጠለው ህዝባዊ ቁጣ ጋር ህወሃትን አሳስቦታል። አርዶታል። እንደ ዘጋቢያችን ገለጻ ኢትዮጵያን በተገንጣይ ስም እየመራ ያለው የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር (ሕወሃት) አሁን በኦሮሚያ ክልል የተነሳው ህዝባዊ እምቢተኛነት ወደ ሌላ ክልል እንዳይዛመት ሰግቷል። ለዚህም አንዱ የስጋት … [Read more...] about “ለድለላ” ሕወሃት ከፍተኛ የጦር አዛዥነት ሹመት ሊስጥ ነው!
“ኢያዬ ደበርሳ” – ጩኸቴን አስተላልፍ፤ የሚመራው ህዝባዊ ዓመጽ
አሁን በተለይ በኦሮሚያ የተቀጣጠለው ዓመጽ ከጀርባው አቀጣጣይ ኃይላት እንዳሉበት ህወሃት እየሰበከ ነው። “ጥቂት ጸረ ሰላም ሃይሎች” በማለት ብዙ አካላትን እየከሰሰም ነው። የትኛውን ኦነግ ወይም ኦነጎችን እንደሆነ ባይታወቅም እንዲያው በደፈናው “ኦነግ”ን ይከስሳል። አርበኞች ግንቦት ፯ እና አገር ቤት ያሉ ሰላማዊ ተቀናቃኞችም የአመጹ አቀጣጣይ ተደርገው ተፈርጀዋል። በተገንጣይ ስም አገር የሚገዛው የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ፍረጃውን ለሚያካሂደው ጭፍጨፋ ህጋዊ ሽፋን ሊያውለው ሆን ብሎ የሚያደርገው እንደሆነ ቢታመንም “እመኑኝ” ሲሉ ኦቦ ቃሉ Oboo Qaalluu የሚሉት ሌላ ነው። ኦቦ ቃሉ ከ25 ዓመት በላይ ኦነግን ያገለገሉና አሁን በስደት አውስትራሊያ የሚኖሩ ናቸው። በቅርቡ ውህደቱን ይፋ ያደርጋል ተብሎ የሚገመተው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር [ዩናይትድ] አካል ሆነው እየሰሩ ነው። … [Read more...] about “ኢያዬ ደበርሳ” – ጩኸቴን አስተላልፍ፤ የሚመራው ህዝባዊ ዓመጽ
ኦህዴድ ኢህአዴግን ከዳ
በበርካታ የኦሮሚያ ከተሞች የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ንቅናቄ የኦህዴድን መክዳት የሚያሳይ መሆኑ ተጠቆመ፡፡ ከንቅናቄው ጋር በተያያዘ ህወሃት/ኢህአዴግ ጥቅሙን ለማስከበር የትግራይ ወጣቶችን ለ“ብሔራዊ” ውትድርና እየጠራ መሆኑ ተሰማ፡፡ ሳምንታት ያስቆጠረውና የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን ምክንያት በማድረግ የተነሳው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በመጠኑም ሆነ በዓይነቱ ልዩ እየሆነ መሄዱ ኦህዴድ ኢህአዴግን የመክዳቱ ማስረጃ ነው ሲሉ በኦሮሚያ ጉዳዮች ላይ ለጎልጉል መረጃ የሚያቀብሉ አመራር አስታውቀዋል፡፡ በኢህአዴግ የአንድ ለአምስት ጥርነፋ፤ ስለላ፤ ሕዝባዊ አደረጃጀት፤ ቁጥጥር፤ … መዋቅሮችን ሁሉ አልፎ ይህንን ያህል ሕዝብ ያለአንዳች ከልካይ መውጣቱ አገዛዙ ሕዝቡን ለመጠርነፍ የተጠቀመበት አሠራር መልሶ ራሱን እየጠረነፈው እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡ ታማኝ ተብሎ የተቀመጠው ካድሬም ሆነ የጥርነፋው … [Read more...] about ኦህዴድ ኢህአዴግን ከዳ
“አንከፋፈልም!” የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
መንግስት ህዝብ ሳያምንበት ማስተር ፕላኑን ተግባራዊ አደርጋለሁ በማለቱ ተቃውሟቸውን ያሰሙት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንደማይከፋፈሉና በአንድነት እንደሚቆሙ በሰላማዊ ሰልፍ ገለፁ፡፡ ተማሪዎቹ ዛሬ ታህሳስ 8/2008 ዓ.ም ዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ ‹‹ለአንድነት እንቆማለን፣ አማራን እንወዳለን፣ ጉራጌን እንወዳለን፣… አንከፋፈልም…..›› ሲሉ ከሌሎች ጋር ግጭት ውስጥ እንደማይገቡና በአንድነት እንደሚቆሙ አሳውቀዋል፡፡ ከማስተር ፕላኑ ጋር በተያያዘ በተነሳው ሰፊ ተቃውሞ ጭንቀት ውስጥ የገባው መንግስት ተቃውሞው ‹‹የብሄር ግጭት›› እንዳስነሳ በተደጋጋሚ የገለፀ ሲሆን ይህ የመንግስት ክስ ተቃውሞውን ለማኮላሸት የተወጠነ እንደሆነ ሲገለፅ ቆይቷል፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም መንግስት ተቃውሞውን ለማኮላሸት ያቀረበው ክስ መሆኑን በመግለፅ ለአንድነት … [Read more...] about “አንከፋፈልም!” የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
መንገድ ሲዘጋ የኖረው ህወሃት/ኢህአዴግ መንገድ እየተዘጋበት ነው
ላለፉት ሦስት ሳምንታት የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት ተማሪዎች የአዲስ አበባ እና የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ተግባራዊ ይደረጋል መባሉን ሲቃወሙ ሰንብተዋል። የተቃውሞውን ጅምር የሚያትተውን የማርታ ፋን ደር ቮልፍ የአዲስ አበባ ዘገባ ጨምራ፤ ጽዮን ግርማ የዛሬዉን የተቃውሞ ሰልፍ ውሎ የተመለከት ርእሶችን ይዛለች፡፡ (የዜና ዘገባው ያሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ነው) የተቃውሞው መነሻ "ያለ ተገቢ የገንዘብ ክፍያ ገበሬዎችን የሚያፈናቅል የመሬት ቅርምት ነዉ" የሚል መኾኑ ሲዘገብ ቆይቷል። የጸጥታ ኃይሎች ሰልፈኞቹ ላይ በወሰዱት ርምጃ ቢያንስ አምስት ሰዎች እንደተገደሉ መንግሥት አምኗል። የተቃዋሚ ድርጅት መሪዎች በበኩላቸው የተገደለዉ ሰዉ ቁጥር ስልሳ እንደሚደርስ ተናግረዋል፡፡ የጸጥታ አስከባሪዎች ሕይወት ማለፉም ተገልጿል። የኦሮምኛ ቋንቋ ዝግጅት ክፍል … [Read more...] about መንገድ ሲዘጋ የኖረው ህወሃት/ኢህአዴግ መንገድ እየተዘጋበት ነው
“ህጋዊና ተመጣጣኝ እርምጃ ይወሰዳል” ህወሃት
ላለፉት 25 ዓመታት ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ግምባር ሲገዛ የኖረው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር በአገሪቱ በተለያዩ ቦታዎች የተከፈተውን የተማሪዎች ሰላማዊ ተቃውሞ “የሽብር ቡድን እንቅስቃሴ” በማለት በኢትዮጵያ ስም በተሰየመው የቴሌቪዥን ፕሮግራም መግለጫ አውጥቷል፡፡ በ1997 ምርጫ ሽንፈት ለመቀበል ጥቂት የቀረው ህወሃት ሞት በወሰዳቸው መለስ ቀጥተኛ ትዕዛዝ አማካኝነት የአዲስ አበባን ፖሊስ በፌዴራል ሥር ይሆናል በማለት በቀጥታ የህወሃት ታዛዥ በማድረግ በ197 ንጹኃን ዜጎች ላይ በአልሞ ተኳሾች ደረትና ግምባራቸውን በማለት እንደገደለ አሁንም “ህጋዊና ተመጣጣኝ እርምጃ ይወሰዳል” በማለት በተማሪና ነዋሪዎች ላይ ለመውሰድ ያቀደውን ፍጹም ኢሰብዓዊ እርምጃ ይፋ አድርጓል፡፡ ከህወሃት የጭከና ታሪክ አንጻር የመግለጫው ትርጉም ለመቀጣጫ እንዲሆን ኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ የመግደያው ጊዜ … [Read more...] about “ህጋዊና ተመጣጣኝ እርምጃ ይወሰዳል” ህወሃት
ድሆች በደሃ ወገኖቻቸው ላይ ዘመቱ!!
“…. የመከላከያ ሰራዊት አባላት የተገነባው በደሃ ልጆች ነው። እባካችሁን እንደናንተው የድሃ ልጆች ወገኖቻቹህን አትግደሉ። ተንደላቃችሁ የምትኖሩም ለዚህ ህዝብ ራሩለት። ለራሳችሁ ጥቅም ስትሉ ይህን ህዝብ አታስፈጁት…” ሲሉ አቶ በቀለ ገርባ ለኢህአዴግ የመከላከያ ሰራዊትና ለህወሃት ታማኝ አገልጋይ ሹመኞች ጥሪ አስተላለፉ። አሁን በተያዘው መንገድ ከተቀጠለ ለማንም አይበጅም ሲሉ በግልም ሆነ በጋራ ህዝብን የሚያከብር ታሪካዊ ውሳኔ እንዲወስኑ ተማጸኑ። አቶ ኦባንግ ሜቶና አርቲስት ታማኝ በየነ “የሞቱት ዜጎች ሞት የሁላችንም ሞት ነው” ሲሉ ሁሉም ያገባኛል በሚል ስሜት ድጋፍ እንዲሰጥ ጥሪ አቀረቡ። አቶ በቀለ በዲሰምበር ፩፫ ቀን ፳፩፮ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት፣ መከላከያ ሰራዊት ማለት ህዝቡን ከአምባገነኖች የሚታደግ እንጂ የራሱን ህዝብ የሚገድል ባዕድ ሃይል … [Read more...] about ድሆች በደሃ ወገኖቻቸው ላይ ዘመቱ!!










