• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ኢያዬ ደበርሳ” – ጩኸቴን አስተላልፍ፤ የሚመራው ህዝባዊ ዓመጽ

December 20, 2015 12:37 pm by Editor Leave a Comment

አሁን በተለይ በኦሮሚያ የተቀጣጠለው ዓመጽ ከጀርባው አቀጣጣይ ኃይላት እንዳሉበት ህወሃት እየሰበከ ነው። “ጥቂት ጸረ ሰላም ሃይሎች” በማለት ብዙ አካላትን እየከሰሰም ነው። የትኛውን ኦነግ ወይም ኦነጎችን እንደሆነ ባይታወቅም እንዲያው በደፈናው “ኦነግ”ን ይከስሳል። አርበኞች ግንቦት ፯ እና አገር ቤት ያሉ ሰላማዊ ተቀናቃኞችም የአመጹ አቀጣጣይ ተደርገው ተፈርጀዋል። በተገንጣይ ስም አገር የሚገዛው የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ፍረጃውን ለሚያካሂደው ጭፍጨፋ ህጋዊ ሽፋን ሊያውለው ሆን ብሎ የሚያደርገው እንደሆነ ቢታመንም “እመኑኝ” ሲሉ ኦቦ ቃሉ Oboo Qaalluu የሚሉት ሌላ ነው።

ኦቦ ቃሉ ከ25 ዓመት በላይ ኦነግን ያገለገሉና አሁን በስደት አውስትራሊያ የሚኖሩ ናቸው። በቅርቡ ውህደቱን  ይፋ ያደርጋል ተብሎ የሚገመተው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር [ዩናይትድ] አካል ሆነው እየሰሩ ነው። እርሳቸው እንደሚሉት ኦነግ ብዙ ነው። ብዙ አመራር አለው። ብዙ ቅርንጫፍ አለው። “ዩናይትድ” የሚል ቅጽል ስም ያለው ኦነግ ማን ነው?

በአቶ ቦንሳ ተባ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር [ሸሌ]፣ በአቶ ድሪባ ሆርዶፋ የሚመራው ጊዜያዊ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ህብረት፣ በአቶ አብደታ ኢሸኬ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ታጋዮች ጥምር፣ ከእነ ጀነራል ከማል ገልቹ የተገነጠለውና በአቶ ኑሮ ደደፎ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር [ቼንጅ] የሚባሉት የተለያዩ የኦነግ አካሎች የፈጠሩት ህብረት ነው። ኦነግ ከሚለው መጠሪያው ጎን [ዩናይትድ] በሚል ተቀጽላ ራሱን የሚለየው ኦነግ ኦቦ ነጋ ጃራን ሊቀመንበር፣ ጄኔራል ኃይሉ ጎንፋን ምክትል ሊቀ መንበር አድርጎ ሰይሟል። ኦቦ ቃሉ እንደሚሉት ውህደቱ በቅርቡ ይፋ ይሆናል።

ሰሞኑን “ኦነግ” በሚለው ስያሜ ከየአቅጣጫው የሚወጣው መግለጫ እንደሚያሰረዳው ኦነግ ውስጥ ያለው መከፋፈል ፈርጁ ብዙ ነው። ሕዝባዊ አልኝታነት ግን ከመግለጫና ከቃላት በላይ ሊሆን ይገባል። ኦቦ ቃሉ እንደሚሉት “መግለጫ ማንም ማውጣት ይችላል። ፍርድን ለህዝብ በመተው እስከድል ድረስ እንኳን አንድ ለመሆን አለመቻል ያሳዝናል። ልዩነትን ወደ ጎን በመተው ከመስማማት ውጪ የሚደረገው የመግለጫ ጎርፍ የማስታወቂያ ስራም ይመስላል” በማለት ጊዜው የህብረት ሊሆን እንደሚገባ ያሳስባሉ። በርግጥም ሰሞኑንን ደብዛቸው የጠፋ በርካቶች ከመግለጫቸው ጋር ለትውስታ በቅተዋል። የጠፉት ብቅ የማለታቸው ጉዳይ በቻ ሳይሆን “ታጣቂ ሃይል አለን” የሚሉትስ?

ጦር ያላቸው ክፍሎች ካሉ ከዚህ የተሻለ አጋጣሚ ስለማያገኙ ህዝብን መቀላቀል ይገባቸው እንደነበር ያመለከቱት ኦቦ ቃሉ “ይህ የተቆጣ ህዝብ፣ ምሬት የፈነቀለው ህዝብ፣ በቃኝ ያለ ህዝብ፣ ትግሉን ከዱላ በዘለለ የሚያግዘው ቢያገኝ ውጤቱ ሊፈጥን በቻለ ነበር” ባይ ናቸው። አያይዘውም “ለመሆኑ መዋጮ ሲሰበሰብለት የኖረው ጦር የት አለ?” ሲሉ ይጠይቃሉ። ብሶትና ጭቆና ባዶ እጁን ደረቱን ለጥይት ሰጥቶ አደባባይ የወጣው ህዝብ በግዳጅ፣ በፈቃደኛነት ለገንዘብ ብሎ ለህወሃት ሰዎች መሳሪያውን በመሸጥ ባዶ እጁን የቀረ ሕዝብ፤ ከወረቀት መግለጫ የዘለለ ድጋፍ እንደሚያሻው ያመላክታሉ። ኢትዮጵያን ነጻ ሊያወጡ የተነሱ ኃይሎች  መቼ ነው አንድ ወረዳ የሚቆጣጠሩት? ጥያቄው የነበረ፣ ያለና የሚኖር ነው።

የህዝባዊ አመጹ ባለቤት ማን ነው?

የኦሮሚያ ሕዝብ እንደ ሌሎች ወገኖቹ ፩ – ፭ በሚባለው አደረጃጀት እስር ቤት ሳይገባ የታሰረ ሕዝብ ነው። መዋቀሩን የሚተገብረው ደግሞ ኦህዴድ ነው። ይህ ህዝብ ሳይፈታ ሊያምጽ አይችልም። የታሰሩትን የሚፈታቸው አሳሪያቸው ብቻ ነው። ስለዚህ የራሱን ሕዝብ ጠርንፎ የነበረው ሃይል ህዝቡን ለቀቀ። ህዝብ ሲፈታ መዋቅር ፈረሰ። ኦቦ ቃሉ ይህን ማብራሪያ ካነሱ በኋላ “አብረው  መስራት ያልተስማሙ ሃይሎች የተቀናጀ አመጽን ጸንሰው፣ አዋልደውና አሳድገው ሊመሩ ይቻላቸዋል?” በማለት ይጠይቃሉ። በዚህ መነሻ አመጹ የህዝብ የመንገፍገፍ ብዛት የወለደው እንደሆነ ይናገራሉ። ብሶት ትግራይ ብቻ ሳይሆን የተበደሉ ባሉበት ቦታ ሁሉ ቀን እየጠበቀ እንደሚነሳ ይጠቁማሉ።

አሁን ኦሮሚያ ላይ የተቀጣጠለውና ህወሃትን የናጠው የህዝብ አመጽ አስመልክቶ አቶ ጃዋር መሃመድ “የኦሮሞ ህዝብ እንደዚህ ሲያመር በታሪክ አይቼ አላውቅም። ከንግዲህ የሚቀረው ህይወቱ ብቻ ነው” በማለት እንደገለጹት ኦቦ ቃሉም “በህወሃትና በኦሮሞ ሕዝብ መካከል የነበረችው የሰለለች ክር ተበጥሳለች። መልሰው እንዳይቀጥሏት ቀድሞውንም የሰለለች ነበረች። ሂደት ነው የበጠሳት። አልቆላታል።” አቶ ጃዋር ለኢሳት እንዳሉት “ደም በፈሰሰ ቁጥር ደም ይግላል። የጋለ ደም አደገኛ ነው … ካሁን በኋላ በቀድሞው መልኩ አይቅጥልም። ሁላችንም ለመሞት ዝግጁ ነን”

የፈነዳው ኦህዴድ

አንዴ በቆረኪ፣ አንዴ በካርታ፣ አንዴ በኪራይ ሰብሳቢነት፣ ወዘተ እየተነረተ፤ በግምገማ ቁም ስቅሉን እያየ ለህወሃት ልእልና የኖረው ኦህዴድ “ፈንድቷል” የሚለው አገላለጽ ተስማሚው ሆኖ ተገኝቷል። ህወሃት ኦህዴድን “ከዳኝ” ይለዋል። ለዚህም ይመስላል የፈነዳው ኦህዴድ ኦሮምያ ላይ የነበረው ውሱን አቅም ተወስዶበታል። ቀድሞውንም ቢሆን ባለሙሉ ሥልጣን ስላልነበር የህወሃት ውሳኔ ገኖ አልወጣም እንጂ ኦሮሚያ ላይ ህወሃት ኩዴታ አካሂዷል። ኦህዴድን ከጨዋታው ውጪ አድርጎታል። ሊጠግኑት ቢሉ እንኳን የሚከብድ ነው።

በቀጣይ ተሃድሶ አካሂዶ ኦህዴድ ላይ ነፍስ መዝራትና እስከ ወረዳና ቀበሌ የተዘረጋውን መዋቀር በቀላሉ አድሶ ማስቀጠል የሚቻል አይሆንም። ኦቦ ቃሉ እንደሚሉት አሁን የተጀመረው የሕዝብ እምቢተኛነት ቢቀዘቅዝ እንኳን ኦህዴድ እንደ ቀድሞው የህወሃት ታማኝ ሆኖ እንዲቀጥል ወደሚያስችለው ደረጃ አይመለስም። ታምቆ የፈነዳና ፍንዳታው ከልሉን ያናወጠ በመሆኑ መዋቀሩ ሙሉ በሙሉ ወደ ህዝባዊ ትስስር ተቀይሯል። ህወሃት እድርና እቁብ የመሳሰሉት ማህበራዊ የመጠርነፊያ መገልገያዎቹን ከስሯል። በበርካታ መመዘኛዎች ኦህዴድ ዲቃላ ሆኖ የመቆም እድሉ ከህወሃት ፍላጎት አንጻር የጠወለገ ነው። እናም ቅድመ ዝግጅት ያስፈልጋል።

ሳይቃጠል በቅጠል

“ይህ ስርዓት አደገኛ ነው። ሲወድቅ ህዝብና አገር ይዞ ይሄዳል። ግንኙነት ያስፈለጋል” በማለት ሰዎች ያሉበት ሁኔታና አቋማቸው ሳይታወቅ አቋም መያዝ እንደማይገባ አቶ ጃዋር ያሳስባሉ። እንደ እሳቸው ገልጻ ሁሉ አሁን አገሪቱ ያለችበት ሁኔታ ያሳሰባቸው ከፍሎች ያገባናል የሚሉ ወገኖች ሁሉ የፖለቲካ መሪ የመፍጠር ስራና፣ አገሪቱ ላይ ህዝብ ያስነሳውን ተቃውሞ አቅጣጫ የማስያዝ ሥራ ሊሰራ እንደሚገባ ያስገነዝባሉ።

ኦሮሚያን አስመልክተው የሚሰሩ ሚዲያዎች ከግለሰብ ማንነትና ድጋፍ ያልተላቀቁ፣ ሚዛናቸው ግለሰብን መደገፍና ማስተዋወቅ እንደሆነ የተናገሩት ኦቦ ቃሉ “ነጻና ከግለሰብ ዝና አቀንቃኝነት የተላቀቀ ሚዲያ ቢኖር ህዝብ ስለ ፖለቲካ መሪዎቹ ጥሩ ስዕል ይኖረው ነበር” ብለዋል። ማናቸውም ሚዲያዎች ሰዎችን የመታደግና የመካብ ስራ ላይ ካተኮሩ ዋና ሚናቸውን ዘንግተዋልና ሊመለሱ ይገባል። አቶ መለስ ሞተውም በሺህ የሚቆጠር ሄክታር መሬት የሚመሩት ሚዲያው እንዲገነባላቸው በተደረገው የሌለ ስብዕናቸው ሳቢያም እንደሆን መረዳት ግድ እንደሚል ተናግረዋል።

“ስለዚህ” ይላሉ አሉ ኦቦ ቃሉ “ስለዚህ ህዝብ በቃኝ ብሎ በቀሰቀሰው ማእበል ውስጥ ገብቶ የማዕበሉ ፈጣሪ ለመሆንና የማስታወቂያ ይዘት ያላቸውን መግለጫዎች ከማተም በመቀራረብ አንድ ላይ መስራት ወደሚቻለበት መንገድ ባስቸኳይ ማምራቱ አንገብጋቢ ነው” ይላሉ፡፡

“አገሪቱ እየተቸበቸበች ነው። በዚህ መልኩ ፭ ዓመት ከቀጠልን ዋጋ የለንም” በማለት አቶ ጃዋር ለሰጡት አስተያየት ኦቦ ቃሉ “የኦሮሞ መሬት ፭ ዓመት የሚቆየ ዕድሜ የለውም” የሚል ማጠናከሪያ አስተያየት ሰጥተዋል።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
Copyright © 2026 · Goolgule